የትምህርት ቦርድ የ 2025 ሽልማት ለመስጠት በህዝብ ትምህርት የታወቀ አገልግሎት ያበረከቱ እጩዎችን ጥቆማ ይፈልጋል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለላቀ የህዝብ ትምህርት አገልግሎት ሽልማትየሚጠቆሙ እጩዎችን እየተቀበለ ነው። ሽልማቶቹ በካውንቲው የትምህርት እንቅስቃሴ ላይ ዘላቂ አወንታዊ ተጽእኖ ያደረጉ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን፣ እና የንግድ ተቋም ሥራዎችን የማክበር እውቅና ይሰጣሉ። ሽልማቶቹ የሚቀርቡት በሚከተሉት ምድቦች ነው።
ተጠቋሚዎች የሚከተሉትን ያከናወኑ መሆን አለባቸው፦
የተማሪ አገልግሎት ሽልማት እነዚህን ሁነቶች ማህበረሰብን በማገልገል ላበረከቱ የ MCPS ተማሪዎች ይሰጣል።
ጥቆማዎችን እስከ ሰኞ፣ ማርች 3 ድረስ ማቅረብ ይቻላል። የበለጠ ግንዛቤ ይውሰዱ እና ጥቆማ ያቅርቡ።
የጥቁሮች ታሪክ በሚዘከርበት ወር፡ ብሬንዳ ዎልፍ ባደረገችው አስተዋጽኦ ላይ ትኩረት ይደረጋል
MCPS የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበትን ወር የጥቁሮችን ታሪክ፣ ባህል፣ እና ስኬቶችን በኩራት ያከብራል። በፌብሩዋሪ ወር ውስጥ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና ማህበረሰቡ የጥቁር መሪዎችን አስተዋጾ የሚያጎሉ ትርጉም ያላቸው ተግባራትን ያከናውናሉ። በዚህ ወር የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ክብረ በዓል አካል በመሆኑ ዲስትሪክት 5 ወክለው የትምህርት ቦርድ አባል ከሆኑት ብሬንዳ ዎልፍ/Brenda Wolff ጋር የሚደረግ የጥያቄ እና መልስ ዝግጅት እንዳያመልጥዎት። መገለጫውን ያንብቡ።
ለአመቱ R.A.I.S.E ምርጥ ሻምፒዮና ሽልማት እጩዎችን ለመጠቆም ክፍት ናቸው።
እጩዎች አሁን ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት R.A.I.S.E የዓመቱ ሻምፒዮን ሽልማት ክፍት ናቸው። ይኼውም፦ R.A.I.S.E. ዋና እሴቶች መሠረት ያደረገ 2024-2025 የትምህርት ዘመን ምሳሌነት ያለው የመሪነት ሚና ለተጫወተ(ች) ግለሰብ ነው። ሁሉም የ MCPS የአትሌቲክስ ስፔሻሊስቶች፣ የአትሌቲክስ አስተባባሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ የስፖርት ዳይሬክተሮች፣ የዲስትሪክት ተወካዮች፣ የተማሪ-አትሌቶች፣ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለተጠቋሚነት ብቁ ናቸው። በእጩነት ጥቆማ ለማቅረብ የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ፌብሩዋሪ 28 እኩለ ቀን ነው።
ለአመቱ ምርጥ R.A.I.S.E. ሻምፒዮን ሽልማት የእጩዎች መጠቆሚያ ቅጽ
ማርች 1 የሚካሄድ የቤተሰብ ውይይት መድረክ/ፎረም ስለተዘጋጀ ለመሣተፍ ቀኑን ይመዝግቡ።
MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት እና Montgomery Goes Purple ጋር በመተባበር የአእምሮ ጤና እና የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀምን መከላከል ላይ ያተኮረ የቤተሰብ ውይይት መድረክ ቅዳሜ፣ ማርች 1 ከጠዋቱ 8፡00 a.m. እስከ ቀትር በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Gaithersburg High School ይካሄዳል። ለሁሉም የ MCPS ቤተሰቦች፣ ሰራተኞች እና ለማህበረሰብ አባላት በነጻ ክፍት ነው። አውደጥናቱ የሚካሄደው በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች ነው። ዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የሚሳተፉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አራት (4) የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያገኛሉ።
ተሳታፊዎች ስለ ፌንታሊን/fentanyl፣ ስለ አልኮል እና ሌሎች አደንዛዥ እና ሱስ የሚያስይዙ ንጥረነገሮች አደገኛነት ይማራሉ፤ የተማሪዎችን ደህንነት ስለመጠበቅ፣ በትምህርት ቤት እና በማህበረሰብ ውስጥ አደገኛ/አደንዛዥ ንጥረ ነገሮችን መጠቀምን መከላከል፣ እና ጉዳቶችን የመቀነስ ሕክምና ተነሳሽነት መረጃዎች ይሰጣሉ። ስለ ናርካን አጠቃቀም ስልጠና ይሰጣል። ዝርዝሮቹ በዝግጅቱ ድረገጽ ላይ ይኖራሉ።
ቁርስ ይቀርባል። ይመዝገቡ/RSVP.
የጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኘው በጌትስበርግ አካባቢ/Gaithersburg High School is located at 101 Education Blvd. ነው /in Gaithersburg።
የሊተርሲ ሥርዓተ ትምህርትን የሚመለከቱ የምሽት ክፍለጊዜ መርሐግብሮች ተዘጋጅተዋል
የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሊተርሲ ቡድኖች ቤተሰቦችን ከአዲሱ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ሊተርሲ ስርአተ ትምህርት፣ አብይ የቋንቋ እውቀት ስነጥበብ (CKLA) ጋር ለማስተዋወቅ እና ልጅዎ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (5ኛ ክፍል) ወደ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (6ኛ ክፍል) ሲሸጋገር/ስትሸጋገር እንዴት ማንበብ እንዳለበ(ባ)ት ለመወያየት ሶስት የስርዓተ ትምህርት ምሽቶችን አዘጋጅተዋል።
ሁለት ክፍለ ጊዜዎች በአካል ይካሄዳሉ— ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 25 እና ረቡዕ፣ ማርች 5 — እና ሶስተኛው ቨርቹዋል ይካሄዳል። በሶስቱም ክፍለ ጊዜዎች ተመሳሳይ መረጃ ይቀርባል። ዝርዝሩ ከዚህ በታች ይገኛል፦
ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 25 ከቀኑ 6፡30-8፡30 ፒ.ኤም
ኪንግስቪው መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፦
Kingsview Middle School, 18909 Kingsview Road, Germantown
ረቡዕ፣ ማርች 5፣ ከቀኑ 6፡30-8፡30 ፒ.ኤም
ጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
John F. Kennedy High School, 1901 Randolph Road, Wheaton
ሐሙስ፣ ማርች 6፣ ቨርቹዋል ክፍለ ጊዜ ከቀኑ 6፡30-8፡10 ፒ.ኤም በዙም ይካሄዳል
ይመዝገቡ/RSVP.
የሊተርሲ ሥርዓተ ትምህርት ምሽቶች፣ 2025
ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
LEAAP ስኮላርሺፕ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) "The League of Educators for Asian American Progress (LEAAP)" ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሚመረቁ እና በትምህርት ሙያ ዘርፍ የማጥናት እቅድ ላላቸው የእስያ እና የፓሲፊክ አሜሪካን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስንየር ተማሪዎች $3,000 ስኮላርሺፕ ይሰጣል። ተጨማሪ መረጃ
የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 1 ነው።
LEAPP ስኮላርሺፕ ወረቀት 2025
አስተማማኝ ደህንነትን መጠበቅ የቪዲዮ ውድድር፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ከ 21 አመት በታች ለሆኑ ወጣቶች አልኮል የመከላከል ጥምረት/The Montgomery County Keeping It Safe Coalition for Under 21 Alcohol Prevention የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ቡድን ከሚከተሉት ርእሶች በአንዱ የ 30 ሰከንድ ቪዲዮ አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
ተማሪዎች የገንዘብ ሽልማቶችን የማሸነፍ እና አምስት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። የውድድር ቪድዎች እስከ እሁድ፣ ማርች 23 መቅረብ አለባቸው። ተጨማሪ መረጃ
የመከባበር ፌስቲቫል፡ ለመለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ስለ ጤናማ ግንኙነት፣ በፍቅር ጓደኝነት የሚፈፀም ጥቃትን መከላከል፣ ስምምነት፣ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ስለሚገኙ ግብዓቶች ለማወቅ ከማርች 30 እስከ ኤፕሪል 6 በሚካሄዱ ዝግጅቶች ላይ ለመሳተፍ የቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ያድርጉ። ይህ ዝግጅት በዊተን የማህበረሰብ መዝናኛ ማእከል/Wheaton Community Recreation Center በአካል በመገኘት እና ቨርቹዋል፤ ወርክሾፖችን ይሰጣል። የበለጠ ለማወቅ እና መረጃ ለማግኘት ይመዝገቡ።
"The Matt Papirmeister Award" ፈዋሽ የወጣቶች ሥዕልበማህበረሰብ ውስጥ ጥሩ ነገር ለሚፈጥሩ፣ለጋሽ፣ እና መልካም ነገር ለሚሰሩ ተማሪ ሠዓሊዎች ሁለት $3,000 ስኮላርሺፕ ሽልማት አዘጋጅቷል። የአሸናፊዎች ሥዕሎች ለታካሚዎች እና ለሚወዷቸው፣ ለጤና አጠባበቅ ሠራተኞች እና የጥበብ ሥራዎቻቸውን ለሚመለከቱ ሁሉ ማጽናኛ፣ ብርታት እና ፈውስ ለመስጠት በጤና አገልግሎት ተንክብካቤ አጋር ሆስፒታል ወይም ክሊኒክ ውስጥ ይለጠፋል። የማስረከቢያው ጊዜ እሁድ፣ ማርች 2 ከቀኑ 11፡59 p.m. ነው ያመልክቱ
FAFSA/MHEC አንድ ማመልከቻ የሚጠናቀቅበት ዝግጅት፡ፌብሩዋሪ 14 ቀን 6–8:30 p.m. በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ለማካሄድ ተዘጋጅቷል። ይህ ዝግጅት ለሁሉምየሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ክፍት ነው። በስፓንሽኛ ቋንቋ አስተርጓሚዎች ይኖራሉ። FAFSA ወይም MHEC One ማመልከቻ እርዳታ ከፈለጉ፣ቀጠሮ ለመያዝ ይመዝገቡ። ያለቀጠሮ ቢመጡም ይስተናገዳሉ። ይህ ዝግጅት የሚካሄደው 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ክፍት ከሆነው ታሪካዊ የጥቁሮች ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች (HBCU) አውደ ርዕይ ዝግጅት ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ነው። ተጨማሪ መረጃ
"Model Railroading Scholarship" የሮክቪል ሞዴል ሬይልሮድ ሶሳይቲ (RMRS) በሞዴል ሬይልሮድ ስራ ላይ ለሚሰማሩ እና በአንዱ STEAM ዘርፍ (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና፣ አርትስ ወይም ሒሳብ) ዲግሪ ለሚማር/ለምትማር ተመራቂ ሲንየር ተማሪዎች $2,500 ስኮላርሺፕ ይሰጣል። እስከ ረቡዕ፣ ኤፕሪል 30 ድረስ ያመልክቱ።
COSA የዝውውር ወቅት ኤፕሪል 1 ያበቃል
MCPS 2025-2026 የትምህርት ቤት ምደባ (COSA) ዝውውር ወቅት ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 1 ያበቃል። COSA የአሠራር ሂደቱ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከተመደቡበት የአካባቢያቸው ትምህርት ቤት (ሆም ስኩል) እንዲዛወሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል።
ተማሪዎች በሚኖሩበት (የአካባቢ ትምህርት ቤት) ወይም ግላዊ የትምህርት መርሃ ግብራቸውን (IEP) በአካባቢያቸው በሚገኝ ት/ቤት ውስጥ መከታተል ይጠበቅባቸዋል። ስለ መስፈርቶቹ በይበልጥ ይወቁ።
ቀደም ብሎ ያልተገመተ ወይም ከኤፕሪል 1 በፊት መገመት ያልተቻለ ድንገተኛ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር ከኤፕሪል 1 በኋላ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
ሁሉም COSA ጥያቄዎች በኦንላይን ParentVue in Synergy ላይ መቅረብ አለባቸው።
COSA ጋር የተያያዘ ዝርዝር መረጃ 2025-2026 COSA መረጃ ቡክሌት ውስጥ ይገኛል። ሌሎች ቋንቋዎች፦
Spanish | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어 | አማርኛ | Portuguese
ጥያቄዎችን ለማቅረብ የተማሪ ፐርሶኔል እና የትምህርት ክትትል አገልግሎት ክፍል 240-740-5620 ይደውሉ።
መልካም ዜና
የቤተዝዳ ቼቪ ቼዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Bethesda-Chevy Chase High School የሙዚቃ ክፍል ከሜሪላንድ ሙዚቃ አስተማሪዎች ማህበር አርአያነት ያለው የሙዚቃ ፕሮግራም ሽልማት አሸንፏል። ትምህርት ቤቱ ጊታር፣ ፒያኖ፣ እና የሙዚቃ ቴክኖሎጂ ትምህርቶችን የላቀ ምደባ እና ኢንተርናሽናል ባካሎሬት ሙዚቃን ጨምሮ በተለያዩ የሙዚቃ ዘርፎች የሚሳተፉ 400 ያህል ተማሪዎች አሉት። ትምህርት ቤቱ ሶስት ባንዶች፣ ሶስት ኦርኬስትራዎች፣ ጃዝ እና ከበሮ ተጫዋቾች እና ሁለት መዘምራን አሉት። ይበልጥ ያንብቡ።
በጄምስ ሁበርት ብሌክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በተካሄደው 11ኛ አመታዊ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የዳንስ ትርኢት ላይ ከዘጠኝ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ትርኢታቸውን አቅርበዋል። ፎተግራፎችን ይመልከቱ።
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ዘገባዎችን MCPS Twitter፣ Facebook እና Instagram ላይ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org