መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ፌብርዋሪ 20/2025

ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህርነት ሶስት የመጨረሻ እጩዎች ተመርጠዋል

ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2025–2026 የአመቱ ምርጥ መምህርነት ሶስት መምህራን በመጨረሻ እጩነት ተሰይመዋል። እነዚህም፥ ሜሬዲዝ ሉተር/Meredith Luther፣ በሮክ ክሪክ ፎረስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመዋዕለ ሕፃናት መምህርት፣ ሜጋን ካምፕቤል/Megan Campbell፣ በፓርክላንድ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሙዚቃ መሳሪያ መምህርት፣ እና ፔት ቢች/Pete Beach፣ በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማህበራዊ ጥናት (ሶሻል ስተዲስ) መምህርት። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ


MCPS ፌብሩዋሪ 12 ለነበረው የበረዶ ቀን MSDE እንዲቀር ይጠይቃል

እሮብ፣ ፌብሩዋሪ 12 በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ተዘግተው እንደነበር ይታወሳል። ይህ 2024-2025 የትምህርት አመት በአስቸኳይ የአየር ሁኔታ ምክንያት የተዘጋበት ቀን ተጨማሪ የማካካሻ ትምህርት ቀን ሊያስፈልግ ይችላል። MCPS በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት ከተደነገገው 180 የትምህርት ቀናት እንዲቀነስ እየጠየቀ ነው። ይህ በ 2024-2025 የትምህርት ካለንደር ላይ እንዴት ተፅእኖ እንደሚኖረው በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እናጋራለን። 


የአንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኦንላይን ጨረታ ከፌብሩዋሪ 21 እስከ 28 ይካሄዳል።

በሪጅኑ ውስጥ ካሉት ትላልቅ የማህበረሰብ ጨረታዎች አንዱን የአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት PTSA የሚያስተናግድ ሲሆን ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ክፍት ነው። ከፌብሩዋሪ 21 እስከ 28 ለልጆች፣ ለወጣቶች፣ እና ለአዋቂዎች ወደ 300 የሚጠጉ እቃዎች በጨረታ ይቀርባሉ። ዕቃዎቹ የቤት ውስጥ እና የውጭ እንቅስቃሴዎችን፣ የሠመር ካምፖችን፣ የልጆች ፓርቲዎችን፣ የአካል ብቃት ትምህርቶችን፣ የተለያዩ ትምህርቶችን፣ የሙዚየም መግቢያዎችን፣ የቲያትር ቲኬቶችን፣እና የምግብ ቤት የስጦታ ካርዶችን ያካትታሉ። የአካባቢው የካውንቲ ቢዝነሶች ሙያዊ አገልግሎቶችን ለግሰዋል፣ ትክክለኛ፣ በራስ የተቀረጸ የአርጀንቲና እግር ኳስ ሊዮ ሜሲ ፎቶም ይኖራል። ገቢው ለአንስታይን መምህራን ትንሽ ስጦታዎችን፣ የተማሪ ፕሮግራሚንግ፣ እና የምግብ አቅርቦትን ይደግፋል። ጥያቄ ካለዎት ኢሜል ይላኩ። 


በምረቃ ወቅት ተማሪዎችን ለማበረታታት WOW ዝግጅት ይመዝገቡ

ወርክሶርስ ሞንትጎመሪ/WorkSource Montgomery ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ (MC) ጋር በመተባበር ማርች 17፣ 18 እና 20 በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ሮክቪል ካምፓስ ለሚካሄደው "Worlds of Work (WOW)" ዝግጅት ላይ 150 የሚሆኑ አሰሪዎችን እና የኢንዱስትሪ መሪዎችን ለማሳተፍ ይፈልጋል።

WOW በዚህ የሙከራ/ፓይለት ፕሮግራም፣ ከስምንት መለስተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ጋር በሚደረጉ መስተጋብራዊ ተሞክሮዎች ላይ እንዲሳተፉ ያደርጋል። ግቡ ተማሪዎች በሚመለከቷቸው ሙያዎች እንዲደሰቱ ማድረግ እና ስለ ሙያ ምርጫዎቻቸው እና ዝንባሌአቸው በሚመቻቸው የኮርስ ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ መርዳት ነው። የኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽኖቹ በኤክስካቫተር መስራትን፣ የማከፋፈያ መስመር መዘርጋትን፣ በመጠነኛ ገንዘብ ንግድ/ቢዝነስ መጀመር፣ የህዝብ ጤና አጠባበቅ መሳሪያዎችን መሞከር ወይም የታካሚውን የደም ግፊት ለመለካት ቨርቹዋል የጆሮ ማዳመጫ መጠቀምን ያካትታሉ።

ቀጣሪዎች በዚህ ዝግጅት ላይ በነጻ የመሳተፍ እድል አላቸው። ቀጣሪዎች/አሠሪዎች በአንድ፣ በሁለት፣ ወይም በሦስቱም ቀናት ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ 1:30 p.m. ለመሳተፍ መምረጥ ይችላሉ።

ተጨማሪ ዝርዝር በዚህ Employer Toolkit ላይ ይገኛል። ይመዝገቡ/Register. ጥያቄዎችን እዚህያቅርቡ። 


የዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የትግል ውድድር ተሳታፊ/Wrestler አልፎ አልፎ በመምራት ላይ ትገኛለች።

የዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪ Jabea Ewane ሁል ጊዜ በትግል ውድድር ፕሮግራም ውስጥ ካሉት ሁለት ሴት ልጆች አንዷ ነች፣ ነገር ግን ይህንን እንደ ተግዳሮት አይታ አታውቅም። እርሷ በውድድሩ ላይ አልፎ አልፎ መሪ ስትሆን ከእኩዮቿ፣ ከአሰልጣኞቿ እና በካውንቲው ካሉ ተፎካካሪዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ፈጥራለች። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በሪጅን እና በስቴት ከመወዳደሯ በፊት በዚህ ቅዳሜና እሁድ በካውንቲው የቫርሲቲ ትግል ትወዳደራለች። ይበልጥ ያንብቡ።


ለህዝብ ትምህርት ልዩ አገልግሎት ያበረከቱ እጩዎችን ለ 2025 ሽልማት ለመጠቆም ክፍት ነው።

የትምህርት ቦርድ ለህዝብ ትምህርት የተለየ አገልግሎት ሽልማት የእጩዎችን ጥቆማ እየተቀበለ ነው። ሽልማቶቹ በካውንቲው የትምህርት እንቅስቃሴ ላይ ዘላቂ አወንታዊ ተጽእኖ ያደረጉ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን፣ እና የንግድ ተቋም ሥራዎችን የማክበር እውቅና ይሰጣሉ። ሽልማቶቹ የሚቀርቡት በሚከተሉት ምድቦች ነው።

ተጠቋሚዎች የሚከተሉትን ያከናወኑ መሆን አለባቸው፦

የተማሪ አገልግሎት ሽልማት እነዚህን ሁነቶች ማህበረሰብን በማገልገል ላበረከቱ የ MCPS ተማሪዎች ይሰጣል።

የእጩዎች ጥቆማ ከሰኞ፣ ማርች 3 በፊት መድረስ አለበት። የበለጠ ግንዛቤ ይውሰዱ እና ጥቆማ ያቅርቡ


ማሳሰቢያዎች፦

መጪዎቹ የሊተርሲ ሥርዓተ ትምህርት ምሽቶች፡የሥርዓተ ትምህርት ምሽቶች ቤተሰቦችን ከአዲሱ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ሊተርሲ ሥርዓተ ትምህርት፣ የእውቀት ምንጭ የቋንቋ ስነጥበብን ማጉላት (CKLA)/Amplify Core Knowledge Language Arts (CKLA) እና ልጅዎ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (5ኛ ክፍል) ወደ መካከለኛ ደረጃ (6ኛ ክፍል) ሲሸጋገር/ስትሸጋገር በንበብ እንዴት መደገፍ እንደሚችሉ ለመወያየት የሥርዓተ ትምህርት ምሽቶች ይካሄዳሉ። የበለጠ መረጃ እና ምዝገባ/RSVP

ማርች 1 የሚካሄድ የቤተሰብ መድረክ፦ የአዕምሮ ጤንነት እና የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀምን መከላከል ላይ ያተኮረ የቤተሰብ ውይይት መድረክ ቅዳሜ፣ ማርች 1 ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ እኩለ ቀን ድረስ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይካሄዳል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች፣ ለሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት በነፃ ለመሳተፍ ክፍት ነው። አውደጥናቱ የሚካሄደው በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች ነው። ይመዝገቡ/RSVP.


SkillsUSA ሪጅናል ውድድር ተማሪዎች በትልቁ አሸንፈዋል

በደርዘን የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ፌብሩዋሪ 13 በቶማስ ኤዲሰን ሁለተኛ ደረጃ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት በተካሄደው SkillsUSA ውድድር ላይ ክህሎታቸውን እና እውቀታቸውን በከፍተኛ ደረጃ አሳይተዋል። ሁሉም ከአካባቢያቸው ውድድር በአሸናፊነት ያለፉ ሲሆን አሸናፊዎቹ በማርች ወር በስቴት ደረጃ ለመወዳደር ይዘጋጃሉ። MCPS ከ10 ውድድሮች በዘጠኙ አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ እና ሶስተኛ ደረጃ አሸንፏል። 

SkillsUSA ተማሪዎች በቴክኒክ፣ በክህሎት፣ እና በአገልግሎት ሰጪነት ሙያዎች እንዲዘጋጁ የሚያግዝ ብሄራዊ የሥራ ግብረሃይል ልማት ድርጅት ነው። በተቀናጀ ሥርዓተ-ትምህርት እና ከኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር፣ተማሪዎች በሰለጠነ ሙያ፣ ለሙያ ሥራ ዝግጁ የሆኑ መሪዎች እና ኃላፊነት የሚሰማቸው የማህበረሰብ አባላት እንዲሆኑ እውቀት ተሰጥቷቸዋል። የፎቶ ክምችቱን ይመልከቱ እና ተጨማሪ ያንብቡ


ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ… 

የ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች በት/ቤት አካባቢ መከባበርን፣ ደግነትን፣ እና አቃፊነትን ለማጎልበት በየቀኑ አብረው ይሰራሉ።ይህን የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ይመልከቱ፡ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጥላቻ አመለካከትን እና ጉልበተኝነትን መጋፈጥ


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)