መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ፌብርዋሪ 27/2025

የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት ምሽቶች በማርች ወር ይካሄዳሉ

የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ /ቤት የሂሳብ ቡድን ሁለት የስርዓተ ትምህርት ምሽቶችን ያስተናግዳል፣ ይኼውም በሂሳብ ስርአተ ትምህርት ላይ የሚደረጉ ለውጦችን በሚመለከት፥ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) የኮርስ መርሃ ግብር እና ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የተቀናጀ ሂሳብን በተመለከተ ወደፊት የሚደረጉ ለውጦችን ያካትታል። "Eureka Math እና Illustrative Math curricula." ሥርዓተ-ትምህርት ልምድ ለመስጠት የሒሳብ ትምህርት ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።

በአካል የሚደረጉ ስብሰባዎች እንደሚከተለው ይከናወናሉ፦

ሰኞ፣ ኤፕሪል 7 ጀምሮ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የተቀረጹ መረጃዎች ሒሳብ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።

2025 የትምህርት አመት የሒሳብ ሥርዓተ ትምህርት ምሽቶች

ለማስታወስ ያህል፣ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሊተርሲ ቡድኖች ቤተሰቦችን ከአዲሱ የአንደኛ ደረጃ የሊተርሲ ስርአተ ትምህርት " Amplify Core Knowledge Language Arts" ጋር ለማስተዋወቅ የስርአተ ትምህርት ምሽቶችንያካሄዳሉ። መጪዎቹ ክፍለ-ጊዜዎች የሚከተሉት ናቸው፦

ይመዝገቡ/RSVP


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎች ምረቃ መጠን ከፍ ብሏል፣ ነገር ግን ክፍተቶቹ እንዳሉ ናቸው።

በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት መረጃ መሠረት MCPS ከ 2024 የአራት-ዓመት ተማሪዎች 91.8% መመረቃቸው ተመዝግቧል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 2.2 ብልጫ ያለው ከመሆኑም በላይ ከስቴት 87.6% አማካይ ነጥብ 4.3% በመቶ ብልጫ አለው። በተለይም የሂስፓኒክ/ላቲኖ ተማሪዎች የምረቃ መጠን 6.6% በመቶ ጨምሯል እና ሌሎች የብዝሃ ቋንቋ ተማሪዎችም የምረቃ መጠን 12% በመቶ ከፍ ብሏል። አጠቃላይ ግስጋሴው አዎንታዊ ቢሆንም፣ በአንዳንድ የተማሪ ቡድኖች ማሽቆልቆል ታይቷል፣ ከነዚህም ውስጥ በግላዊ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ የትምህርት መርሃ ግብሮች (IEPs) ያሏቸው ተማሪዎች 2.8% በመቶ ቅናሽ፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የዘር ሃረግ ያላቸው ተማሪዎች 2.2% በመቶ ነጥብ እና ነጭ ተማሪዎች 0.6% በመቶ ማሽቆልቆል ተመዝግቧል። ሙሉውን መረጃ ያንብቡ


ካውንስልማን ጃዋንዶን፣ የ MCPS ሱፐርኢንቴንደንትን፣ የሞንትጎመሪ ኮሌጅ (MC) ፕሬዘዳንት ስለ በጀት በሚያቀርቡት መድረኮች ላይ ይሳተፉ፦

የሞንትጎመሪ ካውንስል ምክትል ፕሬዝዳንት ዊል ጃዋንዶ/Will Jawando ስለ በጀት ዓመት 2026 የስራ ማስኬጃ በጀትን በሚመለከት ተከታታይ የውይይት መድረኮችን ያስተናግዳሉ። ጃዋንዶ/Jawando በተጨማሪም የምክር ቤቱ የትምህርት እና የባህል ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን ከ MCPS ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር እና የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጄርሜይን ዊሊያምስ ጋር አብረው ያቀርባሉ። 

ዝግጅቶቹ የሚከናወኑት፦

ይመዝገቡ/RSVP

የስፓንሽኛ እና የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ ትርጉም ይኖራል።


የማግሩደር ቤዝቦል፡ ከስቴት ሻምፒዮና እስከ ስቴት ሀውስ

የ ኮ/ሎ ዛዶክ ማግሩደር/ Col. Zadok Magruder ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቫርሲቲ ወንዶች ቤዝቦል ቡድን የ 2024 3A የስቴት ሻምፒዮና አሸንፏል። ትምህርት ቤቱ በስቴት ሻምፒዮና ጨዋታ የተሳተፈው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ከ 0-3 የውድድር ወቅት በኋላ፣ ኮ/ሎ በተከታታይ 22 ጨዋታዎች ውስጥ 20 ድሎችን አስመዝግበዋል፣ ይሄውም በውድድር አመቱ አምስት ሳምንታት ውስጥ 14 ጨዋታዎችን በአሸናፊነት አጠናቀዋል። 

ለዚህ አስደናቂ ስኬት በቅርቡ በሜሪላንድ ምክር ቤት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። አሁን ቡድኑ በወደፊቱ ላይ ያተኮረ ሲሆን በዚህም ለመጪው የውድድር ዘመን ከፍተኛ ተስፋ ይኖረዋል። ቪዲዮ ይመልከቱ


ቀኑን መዝግበው ይያዙ፡ ኦገስት 25, 2025—የተማሪዎች የሽግግር ቀን ይከበራል

ሰኞ፣ ኦገስት 25, 2025 የ 2025–2026 የትምህርት አመት የመጀመሪያ ቀን፣ የተማሪዎች የሽግግር ቀን የኔ ትምህርት ቤት ነው የሚል ስሜት እና የትምህርት ዝግጁነትን በማጎልበት ወደ አዲስ የት/ቤት ደረጃ ወይም ወደ አዲስ ትምህርት ቤቶች የሚሸጋገሩ ተማሪዎችን ለመደገፍ የተነደፈ ሙሉ ቀን ትምህርት የማይሰጥበት አዲስ ፕሮግራም ነው።

ይህ ሙሉ ቀን ወደ መዋእለ ህጻናት፣ 6ኛ ክፍል፣ እና 9ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎችን እና ለ MCPS ትምህርት ቤቶች አዲስ የሆኑትን በደስታ ለመቀበል የታለመ ሲሆን፣ ይህም ከሰራተኞች እና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር የመጀመሪያ ትውውቅ እና ልምድ ለማግኘት ይጠቅማቸዋል። እያንዳንዳቸው ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ከማህበረሰባቸው ጋር የመቀበል መልእክት ይጋራሉ። ለተማሪዎች የሽግግር ቀን ተጨማሪ ግብአት ለመስጠት ወላጆች እና አሳዳጊዎች ይህን አጭር የዳሰሳ ጥናት እንዲሞሉ እንጠይቃለን።

ማሳሰቢያ፡ የሁሉም ተማሪዎች የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ማክሰኞ ኦገስት 26 ነው።


ልዩ ትምህርትን በሚመለከት ሁለት ቨርቹዋል የወላጆች ወርክሾፖች ይካሄዳሉ

የልዩ ትምህርት ቢሮ ለወላጆች ቨርቹዋል ወርክሾፖችን ያስተናግዳል። ዝርዝሩን ከዚህ በታች ይመልከቱ፡-

ሰኞ፣ ማርች 10 ከሠዓት በፊት ጀምሮ 10 a.m., 1 p.m. እና 6 p.m. የሚካሄድ ሲሆን (ሁሉም ዝግጅቶች አንድ አይነት መረጃ የሚሰጡ ናቸው።)

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ከ "Autism/Intellectual and Developmental Disabilities Unit of the Montgomery County Police, Autism Society of Maryland and local swim schools" ጋር በመተባበር ስለ ውሃ ውስጥ ደህንነት እና በአካባቢ የአካል ጉዳተኛ ልጆችን የሚደግፉ የውሃ ደህንነት ወርክሾፖችን ያቀርባል። ይህ የአንድ ሰአት አውደ ጥናት ቤተሰቦች እና ተንከባካቢዎች የደህንነት አጠባበቅ ምክሮችን ፣በአደጋ ጊዜ እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚችሉ፣ የዋና ትምህርቶችን፣ እና ሌሎች የነፃ ግብዓቶችን እንዲማሩ የታለመ ነው።

ይመዝገቡ
2025 ስለ ውሃ ደህንነት የሚካሄዱ አውደጥናቶች

ማክሰኞ፣ ማርች 11 ከቀኑ 7 p.m."The Black Coalition for Excellence in Education"/ የጥቁሮች ጥምረት ለትምህርት የላቀ ደረጃ አውደ ጥናት እና ልዩ ስብሰባዎችን ከንግግር አቅራቢማርሲ ራቻሚም ጃክሰን/Marcy Rachamim Jackson ጋር እያዘጋጀ ነው። የልዩ ትምህርት አቀንቃኝና ተሟጋች እና Pour the Water፡ Transformative Solutions for Equity & Justice in Special Education ደራሲ ናቸው።

ለተጨማሪ መረጃ እና ምዝገባ

BCEE አውደጥናት ማርች 11, 2025ይካሄዳል።


'Prom Couture Closet' ዝግጅት አዲስ ወይም በመጠኑ የተጠቀሙበት እቃዎችን ይለግሱ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፕሮም የመሣተፍ ህልማቸውን እውን ለማድረግ እየረዳ ነው። ዲፓርትመንቱ በፕሮም ከውቸር ክሎሴት ስጦታ በሚሰበሰብበት ወቅት ተማሪዎች የሚመርጧቸውን በመጠኑ ያገለገሉ እና አዳዲስ አልባሳትን፣ ሸሚዝ፣ ጫማ፣ ክራባት፣ እና ሌሎች ጌጣጌጦችን እየሰበሰበ ነው።

ዝግጅቱ ተማሪዎች በገንዘብ ችግር ምክንያት በፕሮም ላይ የመገኘት እንቅፋቶችን ለማስወገድ የታለመ ነው።

እስከ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 28 ልብሶችን እና ጌጣጌጦችን ማሪሊን ጄ. ፕራይስነር የማህበረሰብ መዝናኛ ማዕከል/Marilyn J. Praisner Community Recreation Center በነዚህ ሠዓቶች (9 a.m.–6 p.m.) መለገስ ይችላሉ። በተጨማሪ ቅዳሜ፣ ማርች 1 ቀን በጀርመንታውን የማህበረሰብ መዝናኛ ማዕከል/Germantown Community Recreation Center, 18905 Kingsview Road in Germantown በዚህ ሠዓት 10 a.m.–3 p.m. መለገስ ይችላሉ።

እንዲሁም ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 5 ከጠዋት 10 a.m.–2 p.m. ከፕሬይስነር የማህበረሰብ መዝናኛ ማዕከል/Praisner Community Recreation Center, 14906 Old Columbia Pike in Burtonsville መታወቂያችውን/I.D በማሳየት ማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ አልባሳትን “ከመደርደሪያ መውሰድ” እና በነጻ መምረጥ ይችላል።


ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች

በቅድሚያ፣ ስለ ቴሌፎን አለመያዝ የቪዲዮ ውድድር/Heads Up, Phones Down Video Contestመወዳደሪያ እስከ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 28 መቅረብ አለበት። ይህ ውድድር በእግር ጉዞ እና መኪና በማሽከርከር ወቅት ትኩረትን የሚያደናቅፉ አደጋዎችን የመከላከል ንቃት ግንዛቤ ለመፍጠር የታለመ ነው።

የሴቶች ታሪክ የሚዘከርበት ወር ዌብናር/Webinarማክሰኞ፣ ማርች 4 ቀን 6:30–8 p.m. በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ላቬንደር ላብ/ University of Maryland’s Lavender Lab ዌቢናር ስለሚካሄድ ይቀላቀሉ።የሚሳተፉ ተማሪዎች ሁለት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያገኛሉ። ይመዝገቡ/Register.

አስተማማኝ ደህንነት/Keeping It Safe የቪዲዮ ውድድር፦ስለዚህ ውድድር የበለጠ ይወቁ፣ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ከ 21 አመት እድሜ በታች አልኮል መጠጣት ስለሚያስከትለው አደጋ እና ስጋት 30 ሰከንድ የሚታይ ቪዲዮ ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። የውድድር ቪድዎች እስከ እሁድ፣ ማርች 23 መቅረብ አለባቸው። ተጨማሪ መረጃ

"The Matt Papirmeister Award" በወጣቶች የሚዘጋጅ ፈዋሽ ሥዕልበማህበረሰብ ውስጥ ጥሩ ነገር ለሚፈጥሩ፣ለጋሽ፣ እና መልካም ነገር ለሚሰሩ ተማሪ ሠዓሊዎች ሁለት የ $3,000 ዶላር ስኮላርሺፕ ሽልማት አዘጋጅቷል። የመወዳደሪያ ግብአቶች እስከ እሁድ፣ ማርች 2 ከሠዓት በፊት 11፡59 p.m. መቅረብ አለባቸው። ያመልክቱ


KID Museum/ኪድ ሙዚየም ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ፕሮግራሞችን ይሰጣል፦

KID Museum/ኪድ ሙዚየም በዚህ ስፕሪንግ ወቅት ለተማሪዎች "Maker Night and spring after-school classes" ለመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች ጭምር የፕሮግራም እድሎችን ይሰጣል። በቀጣይ የሚካሄደው፦

"Middle School Maker Night"፡ አርብ፣ ማርች 7 ከቀኑ 5–7:30 p.m., ከ 6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች፣ 3 Bethesda Metro Center ይካሄዳል። ቲኬት በአንድ ሰው $10 ዶላር ይሸጣል። ፒዛ እና መጠጦች ይቀርባሉ። ይመዝገቡ/Register. ስኮላርሺፕ ይኖራል! ወጪ የሚቸግር ከሆነ፣ እባክዎ ይህንን ቅጽ ይሙሉ፦ Access for Every Maker form

በስፕሪንግ ድህረ-ትምህርት ቤት የሚሰጡ ትምህርቶች/Spring After-School Classes

ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ


አሰልጣኝ ቶም ማርቲን PCA ብሄራዊ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ አሸናፊ ሆነዋል

የዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አገር አቋራጭ እና የትራክ አሰልጣኝ ቶም ማርቲን PCA ከአመቱ ምርጥ 10 አሰልጣኞች ውስጥ ምርጥ የመጨረሻ እጩ ሆነው ተመርጠዋል። 28 ዓመታት ልምድ ያላቸው እና 17 በላይ የስቴት ሻምፒዮናዎች ትሩፋት ያላቸው፣ የማርቲን ተፅእኖ ከድል ያለፈ - ከአትሌቶቹ ጋር ዘላቂ ግንኙነቶችን ገንብተዋል፣ ይህም ጠንክሮ መስራትን ከትራክ ጋር እንዲያገናኙ ረድቷቸዋል። የአሰልጣኙ ፍልስፍና ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ተወዳዳሪዎች እንዴት እንደቀረፀ፣የክብር ሜዳሊያ ካፕቴን የመሣሰሉ አበረታች የቀድሞ አትሌቶችን ጭምር የበለጠ ማወቅ ያስፈልጋል። ፍሎረንት ግሮበርግ/Florent Groberg? ሙሉ ታሪኩን ያንብቡ። 


ማሳሰቢያዎች …

ማርች 1 የሚካሄድ የቤተሰብ መድረክ፦ የአዕምሮ ጤንነት እና የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀምን መከላከል ላይ ያተኮረ የቤተሰብ ውይይት መድረክ ቅዳሜ፣ ማርች 1 ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ እኩለ ቀን ድረስ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይካሄዳል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች፣ ለሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት በነፃ ለመሳተፍ ክፍት ነው። አውደጥናቱ የሚካሄደው በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች ነው። ይመዝገቡ/RSVP.

በትምህርት ላይ ለውጥ ያደረጉትን እናክብራቸው፦ ለህዝብ ትምህርት የተለየ አገልግሎት ሽልማቶችለሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እጩዎችን ለማቅረብ ክፍት ነው፣ ይህም በካውንቲው ውስጥ ባለው የትምህርት ልምድ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ያደረጉ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን እና የንግድ ማህበረሰቦችን ይመለከታል። እጩዎችን የመጠቆሚያ ጊዜ እስከ ማርች 3 ድረስ መጠናቀቅ አለበት። እጩ ለመጠቆም ወይም የበለጠ ለማወቅእዚህ ያንብቡ።

Summer RISE አስተናጋጅ ምዝገባ፦ Summer RISE 2025 ተማሪዎችን ለማስተናገድ የንግድ ተቋማት፣ የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች መመዝገብ ይችላሉ። ይህ የአምስት ሳምንት መርሃ ግብር ለታዳጊ ወጣቶች እና ለሲንየር ተማሪዎች በሙያ ላይ የተመሰረተ የትምህርት ልምዶችን ይሰጣል፤ እና አሰሪዎች ባለተሰጥኦ ዝንባሌ ያላቸውን ለመምረጥ ይረዳቸዋል። Host registration እስከ ማርች 7 ድረስ ክፍት ነው። ጥያቄ ካለዎትDavida Gurstelle ኢሜይል ያድርጉ ወይም 240-740-5599 ይደውሉ።


የላቲን ዳንስ ውድድር ባህልን፣ ግጥሞችን፣ እና ማህበረሰብን ይዘክራል።

ከ 800 በላይ ሰዎች በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አመታዊ የላቲን ዳንስ ጁኒየር ዲቪዚዮን ውድድር ላይ ተገኝተዋል፣ከዘጠኝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 160 በላይተማሪዎች ድንቅ ችሎታቸውን አሳይተዋል። በውድድሩ ላይ በሰባት ምድቦች የተሳተፉ ተማሪዎች ቀርበዋል። ተጨማሪ ያንብቡ፤ ተጨማሪ ፎተግራፎችን ይመልከቱ


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)