የኮሌጅ አውደ ርዕይ ኤፕሪል 8–9 እየተዘጋጀ ነው፣ ቨርቹዋል አማራጮችም ይኖራሉ።
The National Association for College Admission Counseling (NACAC)፡ ከኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መገናኘት ለሚፈልጉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሁለት አማራጮች አሉት — ይኼውም በአካል በመገኘት እና ቨርቹዋል አማራጮች ናቸው።
የዘንድሮ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮሌጅ አውደ ርዕይ (Montgomery County NACAC ) ኤፕሪል 8 እስከ 9 ከሰዓት በፊት 9፡45 a.m.-1 p.m በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፡ Adventist Healthcare Fieldhouse in Germantown. 11ኛ ክፍል ተማሪዎች ከትምህርት ቤታቸው የመስክ ጉዞ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ በአካል በመገኘት በነፃ መሳተፍ ይችላሉ። በዕለቱ ተማሪዎች ራሳቸው እንዲነዱ አይፈቀድላቸውም። ተማሪዎች በዐውደ ርዕዩ ላይ የሚሳተፉበትን ቀን እና ሰዓት በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኮሌጅ/የስራ መረጃ አስተባባሪ (CCIC) ወይም የት/ቤት ካውንስለር ማነጋገር ይችላሉ። አውደ ርዕዩ ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 8 ከቀኑ 6:30-8 p.m. ከዘጠነኛ እስከ አስራሁለተኛ ክፍል (9-12) ለሚማሩ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ክፍት ይሆናል። የምሽት ዝግጅቱ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ “የኮሌጁ ማመልከቻ ሂደት፡ የጊዜ ማእቀፍ እና ግብዓቶች” የተሰኘ አውደ ጥናት ያካትታል። ተጨማሪ መረጃ
NACAC በዚህ አመት ተማሪዎችን ከፍላጎታቸው፣የካምፓሱ መጠን፣ የማጥናት ዝንባሌአቸው፣ እና ከጂኦግራፊያዊ ርቀት ጋር ከሚዛመዱ ኮሌጆች ጋር ለማገናኘት ሁለት ቨርቹዋል የኮሌጅ አውደርዕዮችን ያስተናግዳል። ተማሪዎች ከተመዘገቡ በኋላ፣ ኮሌጅ የሚቆዩበትን የመጎብኘት፣ አንድ ለአንድ የመነጋገር፣ እና ፊትለፊት የመነጋገር እና ሪኮርድ የተደረጉ ክፍለ ጊዜዎችን የመመልከት እድል ይኖራቸዋል። ከ 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የቨርቹዋል አውደ ርዕይ አማራጭ ክፍት ነው።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች 2025 የምግብ አሰራር ውድድር ላይ እውነተኛ የልጆች ምግብ አሠራር አሳይተዋል።
የሼዲ ግሮቭ እና የታኮማ ፓርክ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች በ 2025 እውነተኛ የልጆች ምግብ ዝግጅት ላይ ተሳትፈዋል። ተማሪዎች የወደፊት የትምህርት ቤት ምሳ የምግብ ዝርዝር ላይ መካተት ያለባቸው ለአትክልት ብቻ ተመጋቢዎች/የቬጀቴሪያን ምግቦችን የማዘጋጀት እድል ነበራቸው። ስለ ሰሩዋቸው የፈጠራ ምግቦች እና ምግቦችን ለእኩዮቻቸው ጣፋጭ እና ገንቢ የማድረግ ፈተናን እንዴት እንደተወጡት ለማወቅ ተጨማሪ ያንብቡ።
ተማሪዎች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ታሪክ በተዘከረበት ቀን ውድድር አድርገዋል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በተካሄደው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ታሪክ ቀን ውድድር ላይ ከ 35 መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ከአምስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 350 በላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ተማሪዎች ተሳትፈዋል። ከእያንዳንዱ ግለሰብ እና ቡድን ከፍተኛ የሚወጡ ፕሮጀክቶች ሁለቱ ፕሮጀክቶች (ዶክመንተሪ፣ ድረ-ገጽ፣ ጽሑፍ፣ ትወና፣ ኤግዚቢት) እውቅና ስላገኙ ቅዳሜ ሜይ 3 በስቴት ደረጃ ለመወዳደር ይሸጋገራሉ። ውጤቶቹን ይመልከቱ
የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ኤፕሪል 3 ይጀመራል።
የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ሐሙስ፣ ኤፕሪል 3 ይጀመራል። በዚህ አመት፣ በኦንላይን ከመመዝገብ ይልቅ፣ የት/ቤት ካውንስለሮች ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው የኮርስ ምክሮችን እየሰጡ ተማሪዎችን ይመዘግባሉ።
የሠመር ትምህርት ቤት የሚካሄድበት ክፍለ ጊዜ ቀናት፡
የሠመር ትምህርት ለተማሪዎች በአካዳሚክ ትምህርት ላይ እንዲያተኩሩ ወይም ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ እድል ይሰጣል። ስለ ክፍያዎች፣ ሌሎች የሠመር ፕሮግራሞች፣ እና የኮርስ ክሬዲት ለማሟላት ያሉትን አማራጮች ዝርዝር ለማግኘት፣ MCPS የሠመር ትምህርት ቤት ድረ ገጽይጎብኙ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የማጓጓዣ/ትራንስፖርት ቡድንን ይቀላቀሉ!
MCPS ሰኞ ማርች 17 ቀን ከጠዋቱ 10:30 a.m.–12:30 p.m. ለአውቶቡስ ሾፌሮች የስራ አውደርዕይ እያዘጋጀ ነው። አውደርዕዩ የሚካሄድበት ቦታ፦ Department of Transportation, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville
የአውቶቡስ ሹፌር ለመሆን መሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች፦
ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች MCPS Careers portal ላይ አስፈላጊ መረጃ የሚሰጥ መገለጫ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል።
በዝግጅቱ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-6080 ይደውሉ።
የስፔሻል ኢጁኬሽን ተማሪ ወላጆች የዳሰሳ ጥናት እንዲሞሉ ተጠይቀዋል
ልዩ ትምህርት የሚሰጣቸው ተማሪዎች ያሏቸው ወላጆች፡የሜሪላንድ ስቴት ትምህርት ክፍል (MSDE) ከእናንተ ለመስማት ይፈልጋል።
MSDE የሜሪላንድ ልዩ ትምህርት ክፍል የወላጆች ተሳትፎ ዳሰሳ የሚደረግበትን መልክት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ልዩ ትምህርት እና ተዛማጅ አገልግሎቶችን የሚያገኙ ተማሪዎች ላሏቸው ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ተልኳል። የዳሰሳ ጥናቱ አላማ የልጅዎ ትምህርት ቤት ምን ያህል ከእርስዎ ጋር አብሮ እየሰራ እንደሆነ ለማወቅ/ለመረዳት ነው። የሚሰጠው መረጃ ስቴቱ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ልዩ ትምህርትና ተዛማጅ አገልግሎቶችን ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።
ወላጆች/ተንከባካቢዎች የዳሰሳ ጥናቱን MSDE ቅድሚያ የተከፈለበት ፖስታ ውስጥ የመመለስ ወይም በኦንላይን ምላሽ የመስጠት አማራጭ አላቸው።
የዳሰሳ ጥናቱ ለማንም ይፋ አይደረግም። አገልግሎቶችን ለሚያገኙ ለእያንዳንዱ ልጅ ወላጆች የዳሰሳ ጥናቱን ለየብቻቸው እንዲሞሉ ይጠየቃሉ። ወላጆች እስከ አርብ፣ ሜይ 30 ድረስ የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው እንዲመልሱ ተጠይቀዋል።
ከተማሪዎች ለትምህርት ቦርድ አባልነት የመጨረሻ እጩዎች ተመርጠዋል
ከግራ ወደ ቀኝ፡ አኑቫ ማሎ፣ የአሁኑ SMOB Praneel Suvarna እና Peter Boyko
Peter Boyko በኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪ እና Anuva Maloo፣ በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጁንየር ተማሪ ለ 48ኛው ከተማሪዎች የሚመረጡ የትምህርት ቦርድ አባልነት (SMOB) የመጨረሻ እጩዎች ናቸው። ለውድድር ከቀረቡት 10 ተማሪዎች መካከል Boyko እና Maloo ከመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ድምጽ በሰጡ 400 በላይ ተወካዮች ተመርጠዋል። ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በሙሉ ክፍት የሆነው ምርጫ ረቡዕ፣ ኤፕሪል 23 ይካሄዳል። መግለጫውን ያንብቡ.
ስለ ሴቶች ታሪክ የሚዘከርበት ወር
ስለ ሴቶች ታሪክ በሚዘከርበት ወር MCPS እንዴት ሴት ተማሪዎችን፣ ሴት ሰራተኞችን፣ እና የቀድሞ ሴት ምሩቃንን አክብሮት እንደሰጠ ያንብቡ፦
ማሳሰቢያዎች
COSA ለውጦች፡የትምህርት ቤት ምደባ ለውጥ (COSA) ሂደት ወላጆች/አሳዳጊዎች በተወሰኑ ሁኔታዎች ልጃቸው ከአካባቢ ት/ቤት ውጭ በሌላ ትምህርት ቤት እንዲማር/እንድትማር መጠየቅ ያስችላቸዋል። በዚህ አመት የተደረጉ አስፈላጊ ለውጦችን ልብ ይበሉ፦
ParentVue እንዴት መጠቀም እንዳለብዎት ለማወቅ ወይም በኦንላይን COSA ጥያቄ ለማቅረብ፣ ልጅዎ የተመደበበትን ትምህርት ቤት ሰራተኛ ያነጋግሩ። ዝርዝር መረጃ 2025-2026 COSA የመረጃ ቡክሌት ላይ ወይም በልጅዎ ትምህርት ቤት ውስጥ ይገኛል።
ጥያቄ ካለዎት፦ Division of Pupil Personnel and Attendance Services በስልክ ቁጥር 240-740-5620 ይደውሉ ወይም ይህን ድረ ገጽ ይጎብኙ።
የሒሳብ ሥርዓተ ትምህርት ምሽቶች፦ ከመዋእለ ህጻናት እስከ አስራሁለተኛ ክፍል (K-12) ኮርሶች ላይ በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የሂሳብ ትምህርት መርጃዎች እና የኮርስ ፕሮግራሞች ላይ ስለተደረጉ ለውጦች፣ የተቀናጀ የሒሳብ ሥርአተ ትምህርትን በሚመለከት በአካል ተገኝተው የሚሳተፉባቸው ክፍለጊዜዎች፦ ስለ "Eureka" ሒሳብ እና "Illustrative Math" ሒሳብ ሥርዓተ-ትምህርት ልምድ ለማጋራት የሒሳብ ትምህርት ባለሙያዎች ይሳተፋሉ። ክፍለ-ጊዜዎቹ የሚከተሉት ናቸው
ሰኞ፣ ኤፕሪል 7 ጀምሮ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የተቀረጹ መረጃዎች ሒሳብ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።
ስለ በጀት ውይይት የሚደረግባቸው መድረኮች፦ 2026 የበጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀትን የሚመለከቱ የውይይት መድረኮች በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ካውንስል ምክትል ፕሬዘዳንት ዊል ጃዋንዶ አማካይነት ይስተናገዳሉ፤ በነዚህ መድረኮች ላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴይለር እና የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ፕሬዘዳንት ዶ/ር Jermaine Williams ይገኛሉ። ይመዝገቡ/RSVP
ዝግጅቶቹ የሚከናወኑት በሚከተሉት ቀናት ነው፦
መጪው KID ሙዚየም ፕሮግራሚንግ
KID ሙዚየም በዚህ ስፕሪንግ ወቅት ለተማሪዎች ከትምህርት ቤት የትምህርት ሠዓት ውጪ የሚከናወን የስፕሪንግ ትምህርት፣ውጪ የትምህርት ቀን፣ እና በስፕሪንግ የዕረፍት ጊዜ ካምፕ ጭምር የትምህርት እድሎችን ይሰጣል። ቀጥሎ የሚከናወኑ፦
የስፕሪንግ ወቅት ድህረ-ት/ቤት ትምህርት፡ ማርች 17 በሚውልበት ሳምንት ይጀመራል።
ቀን ላይ የሚደረግ ካምፕ፦ ሰኞ፣ ማርች 31፣ ከሠዓት በፊት ጀምሮ 9 a.m.- 4 p.m., KID Museum, 3 Bethesda Metro Center, Bethesda ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register
የስፕሪንግ ዕረፍት ካምፕ፦ ሰኞ፣ ኤፕሪል 14 እስከ ሐሙስ፣ ኤፕሪል 17 ከጠዋት 9 a.m.- 4 p.m., KID Museum, 3 Bethesda Metro Center, Bethesda ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register
USG ማርች 29 ኦፕን ሃውስ/Open House ያካሄዳል።
የሼዲ ግሮቭ (USG) ዩኒቨርሲቲዎች የወደፊት ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ስለ USG ካምፓስ እና የዩኒቨርሲቲ አጋሮቹ 2025 የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ኦፕን ሃውስ ስለሚሰጡት የተለያዩ የዲግሪ መርሃ ግብሮች ቅዳሜ ማርች 29 ቀን ከጠዋቱ 10 a.m እስከ ሠዓት በኋላ 2 p.m. በሚካሄደው ፕሮግራም ላይ የበለጠ ግንዛቤ እንዲያገኙ ተጋብዘዋል። ዝግጅቱ የሚካሄድበት ህንጻ፦ Building IV (Biomedical Sciences and Engineering Facility), 9631 Gudelsky Drive, Rockville.
USG የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ አካል እንደመሆኑ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ በአንድ ካምፓስ 80 ያህል የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን በዘጠኝ የስቴት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል። USG የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብሮች የተነደፉት ተማሪዎችን የሶስተኛ እና የአራተኛ አመት ኮርሶችን እንዲሰጡ ወደ አጋር ዩኒቨርሲቲዎች ያሸጋግራል። ወደ ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሞች የሚገቡ ተማሪዎች የመጀመሪያዎቹን ሁለት አመታት በሞንትጎመሪ ኮሌጅ (MC) ወይም ሌላ እውቅና ባለው ተቋም ማጠናቀቅ አለባቸው።
ጎብኚዎች ካምፓሱን መጎብኘት፣ ከመምህራን እና የፕሮግራም ካውንስለሮች ጋር መገናኘት፣ እና ስለ እያንዳንዱ ፕሮግራም የመግቢያ ሂደት ማወቅ ይችላሉ። ተወካዮቹ ስለፕሮግራሞቻቸው፣ ስለ ሙያ ምርጫዎቻቸው፣ እና የገንዘብ ድጋፍ እድሎችን "financial aid" የማዛወር መስፈርቶችን በሚመለከት ለመወያየት ዝግጁ ናቸው። MC ካውንስለሮች USG ፕሮግራሞችን ስለማስተላለፍ መመሪያ ለመስጠት በቦታው ይገኛሉ።
ጥያቄ ካለዎት ኢሜል ያድርጉ። የበለጠ ለመረዳት እና ለመሳተፍ ይመዝገቡ
"Girl Power " ስለ ሴቶች ችሎታና ብቃት የድርሰት ውድድር ለማቅረብ ክፍት ነው
የሴቶች ታሪክ የሚዘከርበትን ወር ለማክበር የሞንጎመሪ ካውንቲ የሴቶች ኮሚሽን እድሜያቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የካውንቲ ነዋሪዎችን በስምንተኛው አመታዊ የሴት ብቃት ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል። ተሳታፊዎች ለቀረበው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ አጭር ልቦለድ፣ ግጥም፣ ወይም የመረጡትን ሚዲያ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ።
የምንጠቀመው ሚዲያ ዝንባሌና ፍላጎትን እና በራስ መተማመንን በመቅረጽ ላይ ትልቅ ሚና ይጫወታል፣ በተለይም ለወጣት ልጃገረዶች እና ሴቶች ያላቸውን አዎንታዊ አርአያነት እውቅና በመስጠት አዳጋች/ተፈታታኝ/የተዛቡ ትርክቶችን የሚያሸንፍ መሆን አለበት። ሴት ልጆችን እና ሴቶችን በማህበረሰቡ ውስጥ ለማበረታታት ምን አይነት ሚዲያ (ቲቪ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ ዩቲዩብ ተከታታይ ፊልሞች፣ ፊልሞች፣ መጽሃፎች/መጽሔቶች) ትፈጥራለህ/ትፈጥሪያለሽ?
መወዳደሪያ ሰነዶችን ማቅረቢያ የጊዜ ገደብ ሰኞ፣ ማርች 31 ከሠዓት በኋላ እስከ 5 p.m. ድረስ ነው። የመወዳደሪያ ጽሑፉ 500 ቃላት መብለጥ የለበትም። መወዳደሪያ ሰነዶቹ ሙሉ ስም፣ እድሜ፣ የክፍል ደረጃ፣ እና የትምህርት ቤት ስም (የሚመለከት ከሆነ)፣ ስልክ ቁጥር፣ እና ኢሜል ማካተት አለባቸው። ከ 18 አመት እድሜ በታች የሆነ ማንኛውም ሰው የሚያቀርበው ሠነድ ከወላጅ ወይም ከአሳዳጊ የጽሁፍ ፍቃድ ያለው/ያላት እና ለአካለ መጠን ያልደረሰ(ች)ው ልጅ የራሱ(ሷ) ስራ መሆን አለበት።
ተጨማሪ ያንብቡ እና የመወዳደሪያ ሠነድ ያቅርቡ። ለጥያቄ፣ 240-777-8300 ይደውሉ ወይምድረገጽ ይጎብኙ
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ዘገባዎችን MCPS Twitter፣ Facebook እና Instagram ላይ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org