መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ማርች 20/2025

ስለ ትምህርት ቤቶች የድንበር ጥናቶች የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ላይ ይቀላቀሉን።

በድንበር ጥናቶች ላይ በቅርቡ የሚደረጉ የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ቻርለስ ደብሊው ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ለመክፈት የተዘጋጁ ናቸው። በነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች ስለ ድንበር የወሰን ጥናት ሂደት እና የወደፊት ተሳትፎ እድሎች ላይ ጠቃሚ ዝርዝሮች ይቀርባሉ።

የቻርለስ ደብልው ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ስለመክፈት የድንበር ጥናት

የክራወን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መክፈቻ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ የወሰን ጥናት

በነዚህ የማህበረሰብ ውይይት ክፍለ ጊዜዎች ስለሚከተሉት ጉዳዮች መረጃዎች ይሰጣሉ፦

ምዝገባ የማያስፈልግ ቢሆንም፣ MCPS ዲስትሪክቱ እንዲዘጋጅ እንዲረዳው የስብሰባ ተሳታፊዎችን መልስ እንዲሰጡ ይጠይቃል።

ማርች 18 የተካሄደውን የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ውይይት ይመልከቱ። 

MCPS የድንበር ጥናቶች ድረ-ገጽ


ኤፕሪል 5 የሚደረገውን የወጣቶች የአየር ንብረት አጠባበቅ ጉባኤ ይቀላቀሉ

የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትኩረት መስጠት አለባቸው! MCPS 4ኛውን ዓመታዊ የወጣቶች የአየር ንብረት ጉባኤ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 5 ከቀኑ 8:30 a.m. to 3:30 p.m. በጁልየስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስተናግዳል። አድራሻው፦ Julius West Middle School, 651 Great Falls Road in Rockville.

ይህ ዝግጅት ተማሪዎችን ስለ አየር ንብረት ለውጥ ለማስተማር እና በማህበረሰባቸው ውስጥ የአየር ንብረት ጥበቃ እርምጃ ፕሮጀክቶችን የመፍጠር መሳሪያዎችን ለማስታጠቅ የተዘጋጀ ነው። የሚሳተፉ ተማሪዎች ስድስት SSL ሰዓቶች ያገኛሉ። ምሳ ይቀርባል፤ እና ከአማካይ ቦታ መጓጓዣ ይኖራል። የሚሳፈሩበት እና የሚወርዱበት ቦታ፦ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ ሴኔካ ቫሊ፣ ኩዊንስ ኦርቻርድ፣ እና ፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው። (ይህ በተማሪዎች የምዝገባ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ ሊቀየር ይችላል።) Montgomery Blair, Seneca Valley, Quince Orchard and Paint Branch high schools (this is subject to change based on student registration) መገኘት የሚፈልጉ ተማሪዎች የተማሪ ምዝገባ ቅጽ መሙላት አለባቸው። ተጨማሪ መረጃ

2025 የወጣቶች የአየር ንብረት ጥበቃ ጉባኤ


በቅርቡ የሚመጣ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ፈጣን እድል "MCPS Opportunity Express"

MCPS የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ፈጣን እድል የሞባይል ምልመላ ሪቨን በመቁረጥ ስነስርዓት እና በቅጥር ዝግጅት እሮብ፣ ኤፕሪል 2 ከሠዓት በፊት 10 a.m. ይጀምራል። የምልመላ ጉዞው የሚጀምረው በዊተን ውድስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። "Opportunity Express"/ኦፖርቹኒቲ ኤክስፕረስ በካውንቲው ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን እና ሌሎች ቦታዎችን ይጎበኛል። ዲስትሪክቱ ለፓራኢጁኬተሮች፣ እና በትራንስፖርት ዘርፍ፣ በምግብ አገልግሎት፣ እና በጥገና እና በኦፕሬሽን ስራዎች ክፍት የስራ ቦታዎች አሉት። ማስታወቂያውን ለጓደኞችዎ እና ለጎረቤቶችዎ ያሰራጩ፣ እና ለአዲስ የስራ እድል ኤፕሪል 2 ይቀላቀሉን። ወደፊት ኦፖርቹኒቲ ኤክስፕረስ የሚከናወኑባቸው የማህበረሰብ ተሳትፎ ዝግጅቶችን ይጠብቁ። 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ፈጣን ዕድል/MCPS Opportunity Express፣ ኤፕሪል 2, 2025


ተከታታይ ነጻ የኮሌጅ እና የስራ ዝግጅት እቅድ ዌብናሮች ይካሄዳሉ

የኮሌጅ መግቢያ አማካሪዎችን/ካውንስለሮች፣ ስለ ኮሌጅዊ መግቢያ መንገድ እና ACT ተከታታይ የኮሌጅ እና የስራ እቅድ ነፃ ቨርቹዋል ዝግጅቶች ላይ ይሳተፉ። የሚቀጥለው በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ለኮሌጅ እና ከዚያም በላይ ለሚሆን ስኬት ረቡዕ፣ ኤፕሪል 16ከሠዓት በኋላ 7:30 p.m. EST ይካሄዳል። እስከ ኦክቶበር ድረስ የተጨማሪ ዌብናሮች መርሐግብር ተይዞላቸዋል። ይመዝገቡ እና የበለጠ ይወቁ

ለኮሌጅ እና ለሙያ ስራ ACT እቅድ 2025


የስፕሪንግ/ፀደይ ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ ኤፕሪል 5 ይካሄዳል 

ከ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ወጣት ወንድ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች የተደረገ ጥሪ! ተማሪዎን ለስፕሪንግ/ፀደይ 2025 የጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ ያስመዝግቡ፤ እና በማበረታታት የስኬት መንገዳቸውን ያቀጣጠሉ። ኮንፈረንሱ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 5 በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ጀርመንታውን ካምፓስ ከቀኑ 8፡00 a.m እስከ ቀትር ይካሄዳል። ይህ ዝግጅት አፍሪካዊ አሜሪካዊ እና ስፓኒክ ለሆኑ ተማሪዎች የተዘጋጀ ቢሆንም፣ ሁሉም እንዲሳተፉ ይበረታታሉ። ተማሪዎች አስቀድመው እዚህ እንዲመዘገቡ ይጠየቃሉ።

የዘንድሮው የስፕሪንግ ኮንፈረንስ ጭብጥ ተማሪዎች እራሳቸውን ብቃት ያላቸው ተፎካካሪ ሆነው እንዲመለከቱ ያበረታታል፣ ጠንክሮ መሥራት፣ ብልህነት እና ጥሩ መጫወት ህልማቸውን እንዲያሳኩ ያደርጋል። የኮንፈረንስ ክፍለ-ጊዜዎቹ የህይወት ክህሎት ተሞክሮዎችን፣ የፓነል ውይይቶችን፣ STEM መሞከር፣ እና የወላጆች የክብ ጠረጴዛ ውይይትን ያካትታሉ። 

ይህ ዝግጅት የሚካሄድበት አድራሻ፦ BioScience Center, 20200 Observation Drive in Germantown

ተጨማሪ መረጃ


PEP ለወላጆች ነፃ ቨርቹዋል ትምህርቶችን ይሰጣል

MCPS እና PEP (የወላጅ ማበረታቻ ፕሮግራም) በዚህ የትምህርት አመት አንድ የመጨረሻ ነጻ PEP የቤተሰብ ፕሮግራም ይሰጣሉ። የስምንት ሣምንት ቨርቹዋል ፕሮግራም ወላጆች እና ተንከባካቢዎች የልጆቻቸውን የአእምሮ ጤንነት ለመደገፍ፣ በራስ የመተማመን ስሜታቸውን ለማሳደግ፣ የቤተሰብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እና በትምህርት ቤት ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ጠቃሚ ምክሮችን ይሰጣል። ያለው ቦታ ውስን ነው። ቢያንስ አምስት ክፍለ ጊዜዎችን ይሳተፉ እና $50 የስጦታ ካርድ ለማግኘት ግምገማውን ያጠናቅቁ። ክፍለ-ጊዜዎቹ የሚካሄዱት ከፀደይ/ስፕሪንግ እረፍት በኋላ ሲሆን ማክሰኞ፣ እሮብ፣ ሐሙስ፣ ወይም እሑድ ከቀኑ 7–8:30 p.m. ይደረጋል። በእንግሊዝኛ፣ ስፓንሽኛ፣ እና በአማርኛ ይካሄዳል (English, Spanish and Amharic) ይመዝገቡ


በቁጥር አናሳ ምሁራን ፕሮግራም 14ኛውን አመታዊ ፕሮግራም አካሂዷል።

ወደ 1,000 የሚጠጉ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በ 14ኛው የካውንቲው በቁጥር አናሳ ምሁራን ፕሮግራም (MSP) ማርች 15 በዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ተሳትፈዋል። MSP ስለ ዘር፣ ስለ ፍትሃዊነት/እኩልነት፣ እና የስኬት እድል ክፍተቶች ዙሪያ ያለውን አመለካከት ለመቀየር በተማሪዎች የሚመራ ተነሳሽነት ነው። MSP በአሁን ወቅት በእያንዳንዱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 30 መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና 12 አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ቅርንጫፎች አሉት።

ሪትሪቱ ያተኮረው ልዩነቶችን በማክበር፣ ዘረኝነትን እና ጥቃትን በመቆጣጠር፣ እና መዋቅራዊ ኢፍትሃዊነትን በመለየት ላይ ወርክሾፖችን አካሄዷል። አውደ ጥናቱን ተማሪዎች አቅደው፣ አመቻችተው፣ እና መርተው አጠናቀዋል። በትምህርት ቤቶች እና በማህበረሰቦች ውስጥ አወንታዊ ለውጥ ለማምጣት በተማሪዎች በተዘጋጁ አንዳንድ የፕሮግራሙ ፀረ-ዘረኝነት የፊልም ፌስቲቫል ዶክመንተሪዎች ላይ ውይይት ተደርጓል። MSP ዝግጅት ላይ የቀድሞ ተማሪዎች እና የዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂ የሆኑት ጆርጅ ሳንቼዝ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። 

የዝግጅቱን የተወሰኑ ፎቶግራፎች ይመልከቱ


ማሳሰቢያ

የሒሳብ ሥርዓተ ትምህርት ምሽት፡ የመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ረቡዕ፣ ማርች 26 ከቀኑ 6፡30–8 ፒ.ኤም በዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Watkins Mill High School, 10301 Apple Ridge Road in Gaithersburg. ተሰብሳቢዎች የሂሳብ ሥርዓተ-ትምህርት መርጃዎችን፣ ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ ክፍል (K-12ኛ) የኮርስ ፕሮግራሚንግ እና ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የተቀናጀ የሒሳብ ትምህርት ለውጦችን ይመረምራሉ። ሰኞ፣ ኤፕሪል 7 ጀምሮ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የተቀረጹ መረጃዎች ሒሳብ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።

የበጀት ውይይት መድረክ፡ 2026 የበጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ የመጨረሻው የውይይት መድረክ ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 1ከቀኑ 6፡30–8 ፒ.ኤም፣ በሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካፍቴሪያ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Rockville High School cafeteria, 2100 Baltimore Road in Rockville መድረኩ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ምክትል ፕሬዘዳንት ዊል ጃዋንዶ የሚመራ ነው፣ በውይይቱ ላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴይለር እና የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጄርሜይን ዊሊያምስ ጋር ይገኛሉ። ይመዝገቡ/RSVP

የተማሪ አገልግሎት ትምህርት፡ ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ በቂ SSL ሰአት ማግኘት አለባቸው። የስፕሪንግ እረፍት ለተማሪዎች SSL ሰአት የሚያገኙበት አመቺ ጊዜ ነው! የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ቨርቹዋል/የርቀት እና/ወይም በአካል SSL እድሎችን ሞንትጎመሪ ካውንቲ የበጎ ፈቃደኞች ማዕከል ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ። ተማሪዎች SSL ቅጾችን፣ መመሪያዎችን፣ ግብዓቶችን፣ እና ሌሎችንም SSL Hub ተማሪዎች/ቤተሰቦች ማግኘት ይችላሉ። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክብር አገልግሎት ሰርተፍኬት (240 ወይም ከዚያ በላይ SSL ሰዓት ያላቸው ሲንየር ተማሪዎች) ወይም የሱፐርኢንተንደንት SSL ሽልማት (75-ሰዓት SSL የመመረቂያ መስፈርቶችን ያጠናቀቁ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች) ተማሪዎች MCPS ቅጽ 560-51 ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ እስከ ኤፕሪል 4 ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ሌሎች SSL ቅጾች በሙሉ በተከታታይ መቅረብ አለባቸው፣ ነገር ግን አርብ፣ ሜይ 30 በኋላ መሆን የለበትም።


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)