የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ምርጦች ለማክበር ይቀላቀሉን!
2025 — የላቀ የሕዝባዊ ትምህርት አገልግሎት ላበረከቱት እውቅና ለመስጠት — ማክሰኞ ሜይ 6 በሚካሄድ ዝግጅት ላይ መላው ማህበረሰብ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድን እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል። ይህ ዝግጅት ስለ ህዝባዊ ትምህርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚዘከርበት በነፃ የሚሣተፉበት ዝግጅት ነው።
በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ አስተማሪዎች፣ ለተማሪዎች፣ እና የማህበረሰብ አጋሮች የላቀ እውቅና የሚሰጥበት ትልቅ ዝግጅት ነው። በዚህ ልዩ የሆነ የዘንድሮው ዝግጅት ላይ ከፍተኛ አገልግሎት ያበረከቱ ሰራተኞችን እውቅና ይሰጣል፤ እንዲሁም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህር፣ የአመቱን የድጋፍ አገልግሎት ሰራተኛ፣ እና የትምህርት ቦርድ የተማሪ አገልግሎት ሽልማቶችን ይሰጣል።
በዚህ አድራሻ ይቀላቀሉን፦ The Music Center at Strathmore, 5301 Tuckerman Lane in North Bethesda. 6:15 p.m. በሮች ይከፈታሉ፣ ፕሮግራሙ 6፡30 p.m. ላይ ይጀመራል። እውቅና የሚሰጣቸው እነማን እንደሆኑ ያንብቡእና ይመዝገቡ/RSVP።
አኑቫ ማሎ/Anuva Maloo ቀጣይዋ ተማሪ የቦርዱ አባል በመሆን ተመርጣለች።
በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪ የሆነችው ወይዘሪት አኑቫ ማሎ 2025-2026 የትምህርት አመት የትምህርት ቦርድ የተማሪ አባል (SMOB) ሆና ተመርጣለች። የወ/ሪት ማሎ የቦርድ አባልነት አገልግሎት ጊዜ ጁላይ 1, 2025 ይጀምራል።
ኤፕሪል 23 በተካሄደው ምርጫ ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ድምጽ ሰጥተዋል። ወይዘሪት ማሎ 62 በመቶ ድምጽ ያገኘች ሲሆን፥ ተፎካካሪዋ ሚስተር ፒተር ቦይኮ በኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጁንየር ተማሪ ሲሆን 38 በመቶ ድምፅ አግኝቷል።
ወይዘሪት ማሎ የትምህርት ቤቷ ፕሬዝዳንት እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሪጅናል የተማሪዎች አመራር ህብረት ወርክሾፕ ምክትል ሆና ታገለግላለች።
SMOB የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አባል በመሆን በጋራ ድርድሮች ላይ፣ የካፒታል እና የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ፣ እንዲሁም የትምህርት ቤቶች መዘጋት፣ እንደገና መከፈት፣ እና የትምህርት ቤቶችን ድንበሮች ማካለል ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ድምጽ መስጠት ይችላል/ትችላለች። ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል "SMOB" አሉታዊ በሆኑ የሠራተኞች እርምጃ አወሳሰድ ላይ ድምፅ አይሰጥም/አትሰጥም። SMOB ለሚያበረክተው/ለምታበረክተው የቦርድ አባልነት አገልግሎት አይከፈልም፥ ነገር ግን $25,000 የኮሌጅ ስኮላርሺፕ፣ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት እና አንድ የሶሻል ስተዲስ ኦነርስ-ደረጃ ክሬዲት ያገኛል/ታገኛለች። ይበልጥ ያንብቡ።
ቀጣዩ የፈጣን እድል ምልመላ ቀን ኤፕሪል 30 ነው!
ቀጣዩ MCPS የምግብ እና የአልሚ ምግብ አገልግሎት ክፍል የፈጣን እድል ምልመላ በዚህ አድራሻ ይካሄዳል፦ Division of Food and Nutrition Services (DFNS), 8401 Turkey Thicket Drive in Gaithersburg አዲሱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተንቀሳቃሽ የሥራ ፈላጊዎች ምልመላ ተሽከርካሪ ረቡዕ፣ ኤፕሪል 30 ከጠዋቱ 8፡30–11 a.m. ለምግብ አገልግሎት ክፍል (DFNS) እና የጥገና እና ኦፕሬሽንስ ክፍል ውስጥ ለሚሰሩ ስራዎች ሥራ ፈላጊዎችን ይቀጥራል።
DFNS በሚከተሉት ቦታዎች ለሚከተሉት የስራ መደቦች ሠራተኞችን ይቀጥራል፦ የካፊቴሪያ ሰራተኞች፣ ቋሚ ተተኪዎች እና ጊዜያዊ የትርፍ ጊዜ ሰራተኞችን ለ ባንኖክበርን እና ካርዴሮክ ስፕሪንግስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ፍራንሲስ ስኮት ኪይ እና ሲልቨር ክሪክ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ለፔይንት ብራንች እና የዊተን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች። (Bannockburn and Carderock Springs elementary schools, Francis Scott Key and Silver Creek middle schools, and Paint Branch and Wheaton high schools.)
DMO የጠቅላላ ጥገና II ሠራተኞችን፣ የጠቅላላ ጥገና III ሠራተኞችን እና የኮምፓክተር መኪና ኦፕሬተሮችን ይቀጥራል።
ኦፖርቹኒቲ ኤክስፕረስ ዲስትሪክቱ ያለውን ክፍት የስራ ቦታ ለማስተዋወቅ በካውንቲው ውስጥ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይዘዋወራል።
ኦፖርቹኒቲ ኤክስፕረስ በራሪ ጽሑፍ/Opportunity Express Flyer, April 30
ልዩ ትምህርት የሚሰጣቸው ልጆች ያሏቸው ወላጆች እስከ ሜይ 30 ድረስ ዳሰሳውን እንዲያጠናቅቁ ተጠይቀዋል።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የልዩ ትምህርት አገልግሎት የሚሰጠው/የሚሰጣት ልጅ አለዎት? የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) "የሜሪላንድ ልዩ ትምህርት የወላጅ ተሳትፎ ጥናት በራሪ ጽሑፍ" በሞንትጎመሪ ካውንቲ ልዩ ትምህርት እና ተዛማጅ አገልግሎቶችን ለሚያገኙ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ በፖስታ ተልኳል።
ይህ ለማንም ሌላ አካል ይፋ የማይደረግ የዳሰሳ ጥናት አላማው፥ የልጅዎ ትምህርት ቤት ምን ያህል ከእርስዎ ጋር አብሮ እየሰራ እንደሆነ ለማወቅ/ለማረጋገጥ ነው። የሚሰጡት መረጃ ስቴቱ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ልዩ ትምህርትና ተዛማጅ አገልግሎቶችን ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።
የዳሰሳ ጥናቱ እዚህ ይገኛል። ወላጆች እስከ አርብ፣ ሜይ 30 ድረስ ሞልተው እንዲመልሱ ይጠየቃሉ።
በወላጅ የሚሞላ በራሪ ጽሑፍ/Parent flyer
መጪዎቹ ዝግጅቶች
ስለ አእምሮ ጤንነት እና ደህንነት አውደ ርዕይ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጥቁሮች የአእምሮ ጤና እና ደህንነት አውደ ርዕይ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 26ሲልቨር ስፕሪንግ በስተምስራቅ በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Montgomery Blair High School, 51 University Blvd. East in Silver Spring. ዝግጅቱ ነፃ እና ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች፣ እና ሰራተኞች ክፍት ነው። ይመዝገቡ/RSVP
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና እድሳት የተደረገላቸው ኮምፒውተሮች ሽያጭ፦የትምህርት አመቱ የመጨረሻ ጊዜ ያገለገሉ መኪናዎች እና ኮምፒውተሮች ሽያጭ ቅዳሜ፣ ሜይ 10ጠዋት 9–11 a.m. በቶማስ ኤዲሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚከተለው አድራሻ ላይ ይካሄዳል፦ Thomas Edison High School of Technology, 12501 Dalewood Drive in Silver Spring. በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተማሪዎች አውቶሞቲቭ ትሬድ ፋውንዴሽን እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን ለስልጠና እና ለላቦራቶሪ ጥናት የተጠቀሙባቸውን ያገለገሉ መኪናዎችን እና ኮምፒውተሮችን ይሸጣሉ። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይለጠፋል።
የልዩ ትምህርት ቤተሰብ ሪሶርስ አውደ ርዕይ፦ ይህ በነጻ የሚቀርብ ዝግጅት ቅዳሜ፣ ሜይ 10 ጠዋት 10 a.m. እስከ 1 p.m. ጀርመንታወን ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚከተለው አድራሻ ይከናወናል፦ Seneca Valley High School, 19401 Crystal Rock Drive in Germantown. ይህ ዝግጅት ቤተሰቦችን፣ አስተማሪዎችን እና የማህበረሰብ ድርጅቶችን እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦች ለመደገፍ ጠቃሚ ግብዓቶችን እና መረጃዎችን ይሰጣል። ተሳታፊዎች መረጃ መሰብሰብ፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ እና ከባለሙያዎች እና ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር መገናኘት ይችላሉ።
ብሌር አውደ ርዕይ፡ ይህ ዝግጅት ዝናብ ወይም የፀሐይ ብርሀን ቢሆን ይካሄዳል። ቅዳሜ፣ ሜይ 10ከእኩለ ቀን እስከ 4 p.m. በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ያካሄዳል፦ አድራሻ፦ Montgomery Blair High School, 51 University Blvd. East in Silver Spring. ይህ ዝግጅት ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና የማህበረሰብ ባለድርሻ አካላትን ከአካባቢው ኤጀንሲዎች፣ የንግድ ማህበረሰቦች እና ድርጅቶች ጋር ያገናኛል። ተማሪዎች STEM እንቅስቃሴዎችን፣ ስነጥበብ እና እደ ጥበባትን፣ ሙዚቃ፣ ዳንስ፣ ትርኢቶችን እና የሌሎች ተግባራት ችሎታዎቻቸውን ያሳያሉ። ብሌር አውደ ርዕይ ላይ ለመሳተፍ ነፃ ቢሆንም፣ ለአንዳንድ ዝግጅቶች እና እንቅስቃሴዎች አስቀድሞ መመዝገብ ዋጋ ይጠቅማል።
የደህንነት ቀን፡ ይህ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ቅዳሜ ሜይ 10 ከጠዋቱ 11 a.m.–3 p.m. ይካሄዳል። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center parking lot, 850 Hungerford Drive in Rockville. የደህንነት ቀን ህብረተሰቡ ስለ ትራፊክ ደህንነት የበለጠ ለማወቅ አንድ ላይ የሚሰበሰብበት ቀን ነው። ዝግጅቱ ለሁሉም ዕድሜ ተስማሚ ስለሆነ፣ ከእንቅስቃሴዎች እና ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር ለሽልማት ተሳተፉ። የዝናብ ቀን፡- ቅዳሜ፣ ሜይ 17።
ከዜና ገጾቻችን የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች እንዳያመልጥዎት
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ዘገባዎችን MCPS Twitter፣ Facebook እና Instagram ላይ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org