መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ሜይ 1, 2025

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ምርጦች እናከብር!

ለትምህርት የላቀ አገልግሎት ያበረከቱትን 2025 የትምህርት አመት እውቅና ለመስጠት — ማክሰኞ፣ ሜይ 6 MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድን ለመቀላቀል እቅድ ያውጡ። — ለሕዝብ የሚሰጥ ትምህርት ኃይል ያለው መሆኑን እውቅና ለመስጠት የታለመ ዝግጅት ነው፣  

በዝግጅቱ ላይ ለመሣተፍ ለሚመጡት 6፡15 p.m. በሮች ይከፈታሉ። ይህ ዝግጅት ለሞንትጎመሪ ካውንቲ አስተማሪዎች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለማህበረሰብ አጋሮች እውቅና የሚሰጥበት የዓመቱ ትልቁ እና ከፍተኛው ሥነ ሥርዓት ነው። ይህ ልዩ ዝግጅት የላቀ አገልግሎት ላበረከቱ ሰራተኞች እውቅና የሚሰጥበት ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህር፣ የአመቱ ምርጥ የድጋፍ አገልግሎት ሰራተኛ፣ እና የትምህርት ቦርድ የተማሪ አገልግሎት ሽልማት አሸናፊ ይቀርባሉ።

በዚህ አድራሻ ይቀላቀሉን፦ The Music Center at Strathmore, 5301 Tuckerman Lane in North Bethesda. ፕሮግራሙ ከቀኑ 6፡30 p.m. ላይ ይጀመራል።እውቅና ስለሚሰጣቸው ግለሰቦች ያንብቡ እና ይመዝገቡ/RSVP


የ 2025 ዓ.ም የምረቃ መርሃ ግብር በይነመረብ ላይ ይገኛል

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምረቃ ስነስርዓቶች ከእሮብ፣ ሜይ 28 እስከ ሐሙስ፣ ጁን 12 ይከናወናሉ። የምረቃ ሥነ-ሥርዓቶቹ በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካምፓሶች፣በዋሽንግተን ዲ.ሲ. DAR Constitution Hall ፣ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ XFINITY Center/ማዕከል፣ በኮሌጅ ፓርክ፣ Mount St. Mary’s University፣ እና በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ባልቲሞር ካውንቲ ይካሄዳል።

የእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምረቃ ቀናት፣ ቦታዎች፣ እና ሰዓቶች


ለሙአለህፃናት፣ ለቅድመ መዋዕለ ሕፃናት፣እና ለሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ክፍት ነው።

የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ፦ እስከ ሴፕቴምበር 1, 2025 እድሜቸው 5 ዓመት የሚሆናቸው ልጆች ለመመዝገብ ብቁ ናቸው። ምዝገባ የሚደረገው በኦንላይንParentVUE ፖርታል ነው። ቤተሰብዎ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ ከሆኑ፣ እዚህ PreentVue አካውንት መክፈት ያስፈልግዎታል። ስለ ብቁነት እና የምዝገባ ሂደት መረጃ MCPS የመዋለ ህፃናት ምዝገባ ድረ-ገጽ ይጎብኙ ወይም የአካባቢዎን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያነጋግሩ።

ቅድመ መዋዕለ ሕጻናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ፦ ሴፕቴምበር 1, 2025 ወይም ከዚያ በፊት 4 ዓመት ለሚሆናቸው ልጆች፣ እንዲሁም በሴፕቴምበር 1, 2025 ወይም ከዚያ በፊት 3 ዓመት ለሆኑ ህጻናት ለመመዝገብ የተወሰነ ቁጥር ቦታ ይኖራል። ቤተሰቦች ለማመልከት በገቢ አቅም-ብቁ መሆን አለባቸው፥ ልጆቻቸውን በኦንላይን ማስመዝገብ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-4530 ደውለው ይጠይቁ።

ለሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ፦የተማሪዎን ትምህርት ቤት ካውንስለር ያነጋግሩ። በአካል ለመማር በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኝ ሲሆን፣ ቨርቹዋል አማራጮችም አሉ።


ሜይ 17 የሚካሄደው የጌትስበርግ የመጽሐፍት አውደርዕይ/ፌስቲቫል እንዳያመልጥዎት!

የጌትስበርግ የመጽሐፍት ፌስቲቫል፦ ከ 100 በላይ ተሸላሚዎችን እና እውቅ ደራሲያን በልብ ወለድ፣ እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ጽሑፍ፣ ረቂቅ ጽሑፎችን፣ ሳይንሳዊ ልብወለድ፣ ግጥም፣ የህጻናት እና የጎልማሶች ስነ-ጽሁፎችን የሚያቀርብ የመጻሕፍት እና የጸሐፊዎች ክብረ በዓል በሚከተለው አድራሻ፦ Bohrer Park, 506 S. Frederick Avenue in Gaithersburg ቅዳሜ ሜይ 17 ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 6 p.m. ድረስ ይካሄዳል። ከሼዲ ግሮቭ ሜትሮ ስቴሽን እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፌርግራውንድስ የሚመጡ ሻትል መጓጓዣዎች ነፃ ናቸው።

በፌስቲቫሉ ላይ የበርካታ ደራሲዎች ስብስብ እና በሁሉም እድሜ ለሚገኙ ህጻናት ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ይቀባሉ። ለህጻናት፣ ለወጣቶች እና ለጎልማሶች የማንበብ፣ የመጻፍ እና መግለጫ የመስጠት ዝንባሌን ለማበረታታት የተነደፉ ፕሮግራሞች፣ ወርክሾፖች፣ እና እንቅስቃሴዎች በልጆች መንደር "Children’s Village" ይካሄዳሉ። ከ130 በላይ ደራሲያን እና ገለጻ አድራጊዎች ይገኙበታል።

የዘንድሮው ከደራስያን ክምችት ላይ የአሽበርተን የስነ ጥበብ መምህር ጆናታን ሮዝ የሚገኝበት ሲሆን፣ “Rover and Speck: It’s a Gas!” የተሰኘ የቅርብ ጊዜ ድርሰቱን ያቀርባል። በተጨማሪ፥ የቀድሞዋ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መምህርት ሳራ ጉድማን ኮንፊኖ/Sara Goodman Confino፣ “Behind Every Good Man.” የተሰኘ የቅርብ ጊዜ ልቦለድ ሥራዋን ታቀርባለች። መግቢያ እና መኪና ማቆሚያ በነፃ ነው።


ማሳሰቢያዎች እና መጪ ዝግጅቶች

የድንበር ጥናት ወቅታዊ መረጃ፦ ለአዲሱ የክራውን እና ደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፕሮጀክቶች የድንበር ጥናት እንዲሁም አዲሱን የውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮጀክትን በተመለከተ ሀሙስ፣ ሜይ 8 የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ ጠቃሚ ማሻሻያዎች ይደረጋሉ። የቦርዱ ስብሰባ ሜይ ወር መጨረሻ እና ጁን መጀመሪያ ላይ ስለ ቀጣይ ዙር የማህበረሰብ ተሳትፎ ማስታወቂያን ጨምሮ ስለ ተሳትፎ እቅድ መግለጫ ይሰጣል። በእነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች ተሳታፊዎች የፕሮጀክቶቹን ቀደምት አማራጮች ለመገምገም እና ለመወያየት እድል ይኖራቸዋል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞች የዳሰሳ ጥናት፦ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ዝንባሌና ፍላጎቶችን የሚያንፀባርቁ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖራቸው MCPS እያካሄደ ስላለው ጥናት መረጃ ለማግኘት ኢሜልዎን ይፈትሹ። አንዳንድ ፕሮግራሞች በተማሪዎች የአካባቢ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ጉዞ ያስፈልጋቸዋል። ይህ የዳሰሳ ጥናት የትኞቹ ፕሮግራሞች በተመጣጣኝ ርቀት ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽ መደረግ እንዳለባቸው ለመወሰን የሚረዱ ግብአቶችን ለማሰባሰብ የታለመ ነው። ስለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ትንተና የበለጠ ይወቁ።የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ።

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና እድሳት የተደረገላቸው ኮምፒውተሮች ሽያጭ፦የትምህርት አመቱ የመጨረሻ ጊዜ ያገለገሉ መኪናዎች እና ኮምፒውተሮች ሽያጭ ቅዳሜ፣ ሜይ 10ጠዋት 9–11 a.m. በቶማስ ኤዲሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚከተለው አድራሻ ላይ ይካሄዳል፦ Thomas Edison High School of Technology, 12501 Dalewood Drive in Silver Spring. ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይለጠፋል።

የልዩ ትምህርት ቤተሰብ ሪሶርስ አውደ ርዕይ፦ ይህ በነጻ የሚቀርብ ዝግጅት ቅዳሜ፣ ሜይ 10 ጠዋት 10 a.m. እስከ 1 p.m. ጀርመንታወን ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚከተለው አድራሻ ይከናወናል፦ Seneca Valley High School, 19401 Crystal Rock Drive in Germantown. ይህ ዝግጅት ቤተሰቦችን፣ አስተማሪዎችን እና የማህበረሰብ ድርጅቶችን እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦች ለመደገፍ ጠቃሚ ግብዓቶችን እና መረጃዎችን ይሰጣል። ተሳታፊዎች መረጃ መሰብሰብ፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ እና ከባለሙያዎች እና ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር መገናኘት ይችላሉ። ዲጄ/DJ፣ የጨረቃ ድብብቆሽ፣ የስዕል ሥራዎች እና የንቅሳት አርቲስቶች የሚሳተፉበት ለልጆች የተዘጋጁ ፕሮግራሞች ይኖራሉ። የልዩ ትምህርት የቤተሰብ መገልገያ/ሪሶርስ አውደርዕይ ​​በራሪ ጽሑፍ 2025

የብሌር አውደ ርዕይ፡ ቅዳሜ፣ ሜይ10 ከእኩለ ቀን እስከ 4 p.m. በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Montgomery Blair High School, 51 University Blvd. East, Silver Spring, rain or shine. ይህ ዝግጅት ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና የማህበረሰብ ባለድርሻ አካላትን ከአካባቢው ኤጀንሲዎች፣ የንግድ ማህበረሰቦች እና ድርጅቶች ጋር ያገናኛል። ተማሪዎች STEM እንቅስቃሴዎችን፣ ስነጥበብ እና እደ ጥበባትን፣ ሙዚቃ፣ ዳንስ፣ ትርኢቶችን እና የሌሎች ተግባራት ችሎታዎቻቸውን ያሳያሉ።

የደህንነት ቀን፡ ይህ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ቅዳሜ ሜይ 10 ከጠዋቱ 11 a.m.–3 p.m. ይካሄዳል። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center parking lot, 850 Hungerford Drive in Rockville. ዝግጅቱ ለሁሉም ዕድሜ ተስማሚ ነው፣ በደርዘን የሚቆጠሩ እንቅስቃሴዎች እና የማህበረሰብ አጋሮች የተለያዩ ስጦታዎችን እና ሽልማቶችን ይዘው ይሳተፋሉ። የዝናብ ቀን፡- ቅዳሜ፣ ሜይ 17። 

KID ሙዚየም ፕሮግራሚንግ


ከዜና ዘገባዎቻችን የቅርብ ጊዜ ዜና እንዳያመልጥዎት


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)