የፓርክላንድ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ የ MCPS የአመቱ ምርጥ መምህርን አሸንፋለች
ሜገን ካምቤል፣ የመሳሪያ ሙዚቃ መምህርት በፓርክላንድ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለትምህርት የላቀ አገልግሎት ክብረ በአል ወቅት የ2025–2026 MCPS የአመቱ ምርጥ መምህር ተሰይማለች። በቀጣይም በሜሪላንድ የአመቱ ምርጥ አስተማሪ ላይ ለመወዳደር ትሄዳለች። የፓራ መምህር (Paraeducator) ጆን ስፓሮው የአመቱ ምርጥ የድጋፍ አገልግሎቶች ሰራተኛ ተብሎ ተሰይሟል፣ እና ጀርመን ዲያዝ-ፔናል፣ የሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተዳደር፣ የትምህርት ቦርድን የተማሪ አገልግሎት ሽልማት አሸንፏል።
በተጨማሪም፣ ሌሎች የMCPS የሰራተኛ አባላትም ለላቀ ስራ እና ቁርጠኝነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
የምሽቱን ቪድዮ ይመልከቱ እና ከ
ለ “Counted Out” (ተቆጥሯል) ዶክመንተሪ ሜይ 13 ላይ ከኛ ጋር ይካፈሉ
የMCPS ቅድመ ኬጂ-12 የሒሳብ ቡድን፣ ከሞንጎመሪ ካውንቲ NAACP የወላጅ መማክርት እና የጥቁር እና ቡኒ ጥምረት (The Black and Brown Coalition) ጋር በመተባበር፣ የዶክመንተሪ “Counted Out፣” በነፃ የማሳየት እና የፓናል ውይይት ያዘጋጃል፣ ከ 6:15-9 p.m. ማክሰኞ፣ ሜይ 13 ላይ። ይህ ዶክመንተሪ የማህበራዊ ጉዳዮችን ለመፍታት የሒሳብ ትምህርትን ማሻሻል አስፈላጊነት ይዳስሳል፣ የሒሳብ ቀውስን ይከታተላል፣ እና የሒሳብ አለማወቅ መንስኤ እና ውጤቶችን ይመረምራል። ምግብ የሚቀርብ ይሆናል።
ዶክመንተሪው የሚታየው በ 15 ዌስት ጉዴ ድራይቭ፣ ስዊት 100፣ በሮክቪል ነው። ያለው ቦታ ውስን ነው፣ መመዝገብ ያስፈልጋል። ዶክመንተሪው ከታየ በኋላ፣ የሒሳብ ብቃትን ተደራሽነት በሚመለከት የተነሱ ጉዳየችን አንድምታ እና የቀረበው አዲሱ የሜሪላንድ የሒሳብ ፖሊሲ በምን መልኩ መፍትሄ ለመስጠት አንሰበ በሚመለከት የፓናል ውይይት ይኖራል። ይመዝገቡ
ለአውቶቡስ ሹፌርነት ሜይ 16 ላይ የስራ አውደርዕይ ተዘጋጅቷል።
MCPS ሰኞ ሜይ16 ቀን ከጠዋቱ 10:30 a.m.–12:30 p.m. ለአውቶቡስ ሾፌሮች የስራ አውደርዕይ ያዘጋጃል። አውደርዕዩ የሚካሄድበት ቦታ፦ Department of Transportation, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville
የአውቶቡስ ሹፌር ለመሆን መሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች፦
ቢያንስ 21 አመት ዕድሜ ያለው/ያላት።
ንጹህ የመንዳት ታሪክ ይኑርዎት፣ በመንጃ ፍቃዱ ላይ የጥፋተኝነት ነጥብ ከአንድ በላይ የሌለው
U.S ውስጥ ቢያንስ አንድ አመት የማሽከርከር ልምድን ጨምሮ ቢያንስ ሶስት አመት መኪና የማሽከርከ ልምድ ያለው/ያላት።
ሁሉንም የቅድመ-አገልግሎት ስልጠና እና የፈተና መስፈርቶችን የማሟላት ችሎታ ያለው/ያላት
ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች MCPS Careers portal ላይ አስፈላጊ መረጃ የሚሰጥ መገለጫ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። በዝግጅቱ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-6080 ይደውሉ።
ማሳሰቢያ
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞች የዳሰሳ ጥናት፦ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ዝንባሌና ፍላጎቶችን የሚያንፀባርቁ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖራቸው MCPS እያካሄደ ስላለው ጥናት መረጃ ለማግኘት ኢሜልዎን ይፈትሹ። አንዳንድ ፕሮግራሞች በተማሪዎች የአካባቢ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ጉዞ ያስፈልጋቸዋል። ይህ የዳሰሳ ጥናት የትኞቹ ፕሮግራሞች በተመጣጣኝ ርቀት ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽ መደረግ እንዳለባቸው ለመወሰን የሚረዱ ግብአቶችን ለማሰባሰብ የታለመ ነው። ስለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ትንተና የበለጠ ይወቁ። የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ።
ያገለገለ መኪና፣ ኮምፒውተር ሽያጭ፦ በትምህርት አመቱ የመጨረሻው ያገለገሉ መኪናዎች እና ኮምፒውተሮች ሽያጭ ቅዳሜ ሜይ 10 ከጠዋቱ 9–11 a.m. ሲልቨር ስፕሪንግ በቶማስ ኤዲሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 12501 ዴልዉድ ድራይቭ፣ በሲልቨር ስፕሪንግ ይካሄዳል። ተጨማሪ መረጃ
የልዩ ትምህርት ቤተሰብ ሪሶርስ አውደ ርዕይ፦ ይህ በነጻ የሚቀርብ ዝግጅት ቅዳሜ፣ ሜይ 10 ጠዋት 10 a.m. እስከ 1 p.m. ጀርመንታወን ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚከተለው አድራሻ ይከናወናል፦ Seneca Valley High School, 19401 Crystal Rock Drive in Germantown. ይህ ዝግጅት ቤተሰቦችን፣ አስተማሪዎችን እና የማህበረሰብ ድርጅቶችን እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦች ለመደገፍ ጠቃሚ ግብዓቶችን እና መረጃዎችን ይሰጣል። ተሳታፊዎች መረጃ መሰብሰብ፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ እና ከባለሙያዎች እና ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር መገናኘት ይችላሉ። የልዩ ትምህርት የቤተሰብ መገልገያ/ሪሶርስ አውደርዕይ በራሪ ጽሑፍ 2025
የደህንነት ቀን፡ ይህ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ቅዳሜ ሜይ 10 ከጠዋቱ 11 a.m.–3 p.m. ይካሄዳል። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center parking lot, 850 Hungerford Drive in Rockville. ዝግጅቱ ለሁሉም ዕድሜ ተስማሚ ነው፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ክንውኖች እና የማህበረሰብ አጋሮች የተለያዩ ስጦታዎችን እና ሽልማቶችን ይዘው ይሳተፋሉ።
የጌይተርስበርግ የመፅሀፍ አውደርዕይ፦ ለቅዳሜ፣ ሜይ 17፣ ከ 10 a.m. to 6 p.m. ድረስ ተዘጋጅቷል፣ በቦህረር (Bohrer) ፓርክ፣ 506 ኤስ. ፍሬድሪክ ጎዳና፣ በጌይተርስበርግ። ከሼዲ ግሮቭ ሜትሮ ስቴሽን እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፌርግራውንድስ የሚመጡ ሻትል መጓጓዣዎች ነፃ ናቸው። ይህ ዝግጅት ከ 100 በላይ ፀሀፊዎች ለንግግሮች፣ ፓናል ውይይቶች፣ ፕሮግራሞች፣ ለህፅናት፣ ለታዳጊዎች፣ ለአዋቂዎች አውደ ጥናቶች፣ እና ማንበብ፣ መፃፍ እና በስዕል መግለፅን የሚያበረታቱ ተግባራይን ያካተተ ነው።
ከዜና ገፅ ላይ የቅርብ ጊዜ ጉዳዮች
የእናንተ ትምህርት ቤት በዝርዝሩ ውስጥ መካተት ቻለ?፦ MCPS 12 አዲስ ግሪን ት/ቤቶችን ጨምሯል፤ አራት ት/ቤቶች ፈቃድ አግኝተዋል።
የጆን ኤፍ። ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህር ኬንድራ ስሚዝ የትውልዶች አካታች ቴክኒኮችን ተጠቅማ እንዴት ግንኙነትን እንደምታዳብር ይመልከቱ።
ከሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ ምድር መጨረሻ ድረስ! መምህርት ክሪስታ ማክኪም በዚህ ፎል ወቅት ወደት እንደሄደች አንብቡ።
ተመራቂ ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጥቁር ት/ቤት መምህራን ትብብር ስለተሰጣቸው ክብር አንብቡ።
ጆንስ ሌን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እንዴት በት/ቤት መኩራትን እና መልካምነት በአዲስ ዘፈን እና የሙዚቃ ቪድዮ እንደሚያከብር ይመልከቱ።
በዚህ ሳምንት ለተጨማሪ ታሪኮች የእኛን የዜና ገፅ መከታተል ይቀጥሉ።
የ MCPS ድህረ ገፅ ጥገና
የ MCPS ድህረ ገፅ አርብ ሜይ 9 ላይ ከምሽቱ 10 ሰአት (10 pm) አካባቢ መደበኛ ጥገና ይደረግለታል እና ለአጭር ጊዜ ለማግኘት አይቻልም።
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ዘገባዎችን MCPS Twitter፣ Facebook እና Instagram ላይ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org