መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ሜይ 22, 2025

ኤዥያን አሜሪካውያን እና የፓሲፊክ ደሴት ታሪካዊ ቅርስ ወር ይከበራል

ለኤዥያን አሜሪካን እና የፓሲፊክ ደሴት ነገድ (AAPI) መታሰቢያ ወር ክብረ በዓል፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ጁሊ ያንግ ጋር ልዩ የሆነ የጥያቄ እና መልስ ክፍለጊዜ እንዳያመልጥዎት።

እንዲሁም በርተንስቪል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የበጎ ፍቃደኝነት-ፓራ አኢጁኬተር የሆነችውን "በፈጠራ የሂሳብ ሥራ" ቡድኖቿ ዘንድ ከተማሪዎች ጋር ባላት ጠንካራ ትስስር የምትታወቅ ጄሲካ ዋንግ ጋር የመገናኘት እድል ይኖርዎታል። ታሪኳን ያንብቡ

MCPS ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች፣ እና ከማህበረሰብ አባላት ጋር በዙም ዌብናሮች ስለ AAPI እና የአይሁዳውያን አሜሪካውያንን የታሪክ ቅርስ ወር ያከብራል። ተማሪዎች በአንድ ዝግጅት በመሣተፍ እስከ ሁለት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።

የእስያውያን አሜሪካውያን እና የፓሲፊክ ደሴት (AAPI) ተወላጆች ታሪካዊ ቅርስ የሚዘከርበት ወር
AAPI ተሞክሮዎች ቅኝት
ሐሙስ፣ ሜይ 22, 6-7:30 p.m.
መመዝገቢያ ሊንክ/Registration Link
በራሪ ጽሑፍ

የአይሁዳውያን አሜሪካውያን ታሪካዊ ቅርስ የሚዘከርበት ወር
የአይሁዶች ብዝሃነት ቅኝት
እሮብ፣ ሜይ 28, 5-6:30 p.m.
መመዝገቢያ ሊንክ/Registration Link
በራሪ ጽሑፍ


ትምህርት ቤቶች የምረቃ ፕሮግራሞችን ሜይ 28 ይጀምራሉ 

የ 2025 ተመራቂዎች ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂዎች ከእሮብ፣ ሜይ 28 ጀምሮ በዊተን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ሜይ 29 ከዊንስተን ቸርችል እና ኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ RICA እና Blair Ewing ዲፕሎማቸውን መቀበል ይጀምራሉ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርአቶች እስከ ሐሙስ፣ ጁን 12 ድረስ ይቀጥላሉ። ሥነ ሥርዓቱ የሚካሄደው በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካምፓሶች፣በዋሽንግተን ዲሲ "DAR Constitution Hall"፣ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ XFINITY ሴንተር፣ በኮሌጅ ፓርክ፣ Mount St. Mary’s University፣ እና በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ባልቲሞር ካውንቲ ይደረጋል።

ስለ እያንዳንዱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤት የምረቃ ስነ ስርአት የሚካሄድባቸውን ቀኖች፣ ቦታዎችን፣ ሰዓቱን፣ እና ንግግር የሚያደርጉትን የክብር እንግዶች ዝርዝር ይመልከቱ። 


የድንበር ጥናት ተሳትፎ ክፍለ-ጊዜዎች ሜይ እና ጁን ላይ ይደረጋሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ ስለ ቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳግም መከፈት፣ ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት፣ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፋፋት ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን በሚመለከት በሚቀጥሉት የተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። እነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች ስለ እያንዳንዱ ጥናት የመጀመሪያ አማራጮችን ይመለከታሉ፤ እና የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ባሏቸው ቤተሰቦች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ለውጦች ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ውይይት ይደረጋል። የስብሰባዎቹ ጊዜያት ለአንድ ሰዓት ያህል የሚቆዩ ናቸው። 

ቨርቹዋል ወይም በአካል ክፍለ ጊዜ ላይ ለመሳተፍ ያሉትንእድሎች ይቃኙ።


የትምህርት ቦርድ ለሥነምግባር ፓነል አመልካቾችን ይፈልጋል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አምስት አባላት ባሉት የሥነ ምግባር ፓነል ላይ ክፍት ቦታ ለመሙላት ይፈልጋል። ከጁላይ 1፣2025 ጀምሮ ክፍት ቦታው የሚሸፈነው ለሶስት አመት የአገልግሎት ጊዜ ነው። አባላት የሚያገለግሉት ያለምንም ማካካሻ ክፍያ ነው።

የቦርድ ፖሊሲ፣ BBB፣ ስነምግባር ላይ እንደተገለጸው ከፓነሉ ኃላፊነቶች መካከል፡ የፋይናንስ መግለጫ ቅጾችን ማጽደቅ፣ የትምህርት ቦርድን የሥነ ምግባር ፖሊሲ መተርጎም፣እና አፈጻፀምን በሚመለከት የምክር አስተያየቶችን መስጠት እና ጥሰት ከተከሰተ በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ የችሎት ምርመራ ማካሄድን ያካትታል።

አመልካቾች እስከ ሰኞ፣ ጁን 95 p.m. ድረስ የፍላጎት ደብዳቤ ከስራ ልምድ ወይም ሌላ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው። እባክዎ የፍላጎት ደብዳቤ እና የሥራ ልምድ በዚህ አድራሻ ይላኩ፦Tom Lockman, Montgomery County Board of Education, 15 West Gude Drive, Suite 100, Rockville, MD 20850. ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።


ማሳሰቢያ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች ዳሰሳ አምልጦዎት ከሆነ፥ MCPS የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ፍላጎቶች የሚያሟሉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን ፍትሃዊ ተደራሽነት ለማረጋገጥ ጥናት እያካሄደ ነው። ዲስትሪክቱ ልጆቻቸው ገና ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያልገቡትን ጭምር ከሁሉም ቤተሰቦች መስማት ይፈልጋል። እባክዎን ይህን አጭር የዳሰሳ ጥናት ሞልተው ይመልሱ፣ይህን መጠይቅ ለመሙላት ከአምስት ደቂቃ በላይ አይወስድም። 

የኩሩ ማህበረሰብ ቀን፦ እሁድ፣ ጁን 1 ከቀኑ 1-4 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ Bethesda-Chevy Chase High School, 4301 East-West Highway in Bethesda. ዝግጅቱ ለሁሉም ዕድሜ ክፍት ነው፣ ይህ ዝግጅት የተለያዩ ተግባራትን ያካትታል፣ ትራንቪያ፣ ቢንጎ፣ ስነጥበብ፣ እና እደ ጥበባት፣ እንዲሁም ለወጣት ተማሪዎች የታሪክ ክፍለጊዜ ይኖራል። በተጨማሪ፥ በማህበረሰብ ድርጅቶች የሚቀርቡ የመርጃ ቁሳቁሶች ይኖራሉ። 

SSL ሰዓቶች ሜይ 30 ላይ ተጠናቀው መቅረብ አለባቸው፦ ከጁን 1, 2024 ጀምሮ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያጠናቀቁ ተማሪዎች አስፈላጊውን SSL እንቅስቃሴ ማረጋገጫ ቅጽ ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ እስከ ሜይ 30 ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።


ከዜና ገጾቻችን ወቅታዊ መረጃ

የዜና ገጻችንን በዲስትሪክቱ ዙሪያ ከተካሄዱ ዝግጅቶች ጋር የምናዘምን ስለሆነ፣የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ለመከታተል በዚህ ድረገጽ ላይ ይመልከቱ 

ተማሪዎች 2 ሚሊዮን ዶላር የስኮላርሺፕ ሽልማት አግኝተዋል፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የትምህርት ፋውንዴሽን 170 ባለ $10,000 የሩት እና ኖርማን ራልስ-ፓትሪሺያ ባየር ኦኔል ስኮላርሺፕ ጭምር የላቀ የአካዳሚክ ደረጃ ያገኙትን 200 የሚጠጉ ተማሪዎች ሽልማት ሰጥቷቸዋል። 

Burtonsville Breaks Ground፦ MCPS ለትምህርት አመት 2026-2027 ይከፈታል ተብሎ ለሚጠበቀው አዲሱ የበርተንስቪል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ መጀመርን ለማብሰር ሜይ 19 የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ተካሄዷል። 

ጊልበርት ጌምስ፦ የዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሜይ 20 ሶስተኛውን የጊልበርት ጌምስ አስተናግዷል። የቀድሞ ተማሪዋ የሳራ ጊልበርትን መታሰቢያ በማክበር ይህ ልዩ ዝግጅት የሁሉንም ተማሪዎች ችሎታ በማቀናጀት ለአንድ ቀን፣ የሚያበረታታ እና መንፈስ ቀስቃሽ የሆነ ውድድር ያካሄዳል።

በመካከላችን ያሉ ጀግኖች፦ የኮ/ሎ. ዛዶክ ማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት "Montgomery County Fire and Rescue Services" ተማሪ-ሰራተኞች የቅርጫት ኳስ ጨዋታን ተከትሎ የልብ ድካም ያጋጠመው ፓራ ኢጁኬተር እና ረዳት የእግር ኳስ አሰልጣኝ ህይወት በመታደጋቸው ልዩ አክብሮት አግኝተዋል።


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)