መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ሜይ 29, 2025

2025 የምረቃ ሥነ ሥርአት በመካሄድ ላይ ነው!

የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማቸውን የሚያገኙ ወደ 13,000 የሚጠጉ ተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ተጀምሯል። የዊተን፣ ዊንስተን ቸርችል፣ ኩዊንስ ኦርቻርድ፣ አልበርት አንስታይን፣ ኮ/ል ዛዶክ ማግሩደር፣ ደማስከስ፣ ሴኔካ ቫሊ፣ እና ሸርውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ RICA እና Blair Ewing ሲንየር ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ በዚህ ሳምንት ሲመረቁ የመጀመሪያዎቹ ናቸው። የምረቃ ሥነ ሥርአቱ እስከ ሐሙስ፣ ጁን 12 ድረስ ይቀጥላል።

የፎተግራፎችን ክምችት ይመልከቷል

የምረቃ ቀናት፣ጊዜ/ሠአት፣ንግግር የሚያደርጉ እንግዶች፣ እና የምረቃ ሥነ ስርአት የሚካሄዱባቸው ቦታዎች ዝርዝር.


የድንበር ጥናቱ በልጅዎ ትምህርት ቤት ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ይኖራል? ተፅእኖ ይኖረው እንደሆነ ለማወቅ ይቀላቀሉን!

ሰኞ፣ ጁን 2 እስከ ረቡዕ፣ ጁን 4 ድረስ MCPS ተጨማሪ የድንበር ጥናት ተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎችን ያስተናግዳል። ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፋፋት፤ እና ከ 2027 የትምህርት አመት ጀምሮ የመለስተኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦችን እንዴት ሊነካ እንደሚችል የበለጠ ለማወቅ ይቀላቀሉን። 

ቨርቹዋል እና በአካል ተገኝተው መሣተፍ የሚችሉባቸው ክፍለ ጊዜዎች አሉ። RSVP እዚህ ይመዝገቡ.

ተጨማሪ መረጃ 


MCPS ከእርስዎ መስማት ይፈልጋል!

ቤተሰብዎ በትምህርት ቤቶቻችን ስላለው ልምድ MCPS የበለጠ ማወቅ ይፈልጋል። የእርስዎ አስተያየት የማስተማር፣ የመማር፣ እና የትምህርት ቤትን አካባቢ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንዴት እንደሚለማመዱ እንድንገነዘብ ይረዳናል። እባክዎ ይህን ሚስጥራዊ የዳሰሳ ጥናት.ለማጠናቀቅ 10 ደቂቃ ያህል ይውሰዱ። ዲስትሪክቱ የማስተማር ስራውን ለማሻሻል እና ትምህርት ቤቶቻችንን እና ዲስትሪክታችንን ለሁሉም ተማሪዎች፣ ለሰራተኞች፣ እና ለቤተሰቦች የበለጠ ምቹ ቦታ ማድረግ ይፈልጋል።


"GIVE Backpacks" ዘመቻ እየተካሄደ ስለሆነ ዛሬውኑ ይለግሱ

14ኛው አመታዊ GIVE BACKpacks ዘመቻ በመካሄድ ላይ ስለሆነ፥ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በጀርባ የሚያዝ የደብተር/የመጻህፍት ቦርሳዎችን እና የት/ቤት ቁሳቁሶችን በመግዛት የተቸገሩ ተማሪዎችን እርዷቸው። $20 በመለገስ የተማሪ ቦርሳ፣ ወረቀት፣ እርሳሶች፣ እስክሪብቶዎች፣ ከለር እርሳሶች፣ የእርሳስ መቅረጫ፣ የደብተር መያዣ፣ የወረቀት ማህደሮችን እና ሌሎችንም የትምህርት መርጃዎችን ጭምር መስጠት ይችላሉ። 

ከ 70,000 በላይ ተማሪዎች በገንዘብ ድህነት ውስጥ ስለሚገኙ በአዲሱ የትምህርት አመት መጀመሪያ ላይ ለመማር ዝግጁ እንዲሆኑ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለማግኘት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። MCPS በዊንተር/ክረምት ወራት የትምህርት መርጃዎችን በግዢ ለማቅረብ ያዛል፣ ዓላማውም በተቻለ መጠን ለብዙ ተማሪዎች የደብተር መያዣ ቦርሳ እና በትምህርት አመቱ መጀመሪያ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ነው። ጁን፣ ጁላይ፣ እና ኦገስት ገንዘብ ለማሰባሰብ እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ግዢ ለማቀላጠፍ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ወሳኝ ወራት ናቸው።

ስለ "MCPS GIVE Backpacks" በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችFAQs about MCPS GIVE BACKpacks


ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሠመር ኮድ መስጫ ካምፕ በነፃ ትምህርት ይሰጣል።"Free Summer Coding Camp"

ሞንትጎመሪ ካን ኮድ የሠመር ካምፕ "Montgomery Can Code’s summer camp" ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 6ኛ፣7ኛ፣ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአንድ ሳምንት የሚካሄድ ካምፕ ነው። በካምፑ ውስጥ የሚቆዩ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መተግበሪያዎችን ለመፍጠር ፕሮፌሽናል አልሚዎች በሚጠቀሙት ለመረዳት ቀላል በሆነው አፕል ስዊፍት ኮድ ማድረግን ይማራሉ። ተማሪዎች የፈጠራ ፕሮጀክታቸውን የሚያጠናቅቁት ኮድ የማድረግ ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች የተማሩትን "Swift" በመጠቀም ነው።

ካምፑ ጁላይ 14 እስከ 18 እና ጁላይ 21 እስከ 25 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በአራቱም የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ካምፓሶች ተማሪዎች በአካል ተገኝተው ይማራሉ። በተመሳሳዩ ሰዓቶች እና ሳምንታት ውስጥ በዙም የሚቀርብ ቨርቹዋል ትምህርትም ይኖራል።

ይህ ተነሳሽነት MCPS፣ ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የኢኮኖሚ ልማት ኮርፖሬሽን፣ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የመንግስት አስተዳደር እና Apple ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው። 

ምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃ

ጥያቄ ካለዎት ወደ
Montgomery Can Code ኢሜል ያድርጉ።

"Montgomery Can Code" አጭር የመግለጫ ጽሑፍ፣ በእንግሊዝኛ
"Montgomery Can Code" አጭር የመግለጫ ጽሑፍ፣ በስፓንሽኛ
"Montgomery Can Code" አጭር የመግለጫ ጽሑፍ፣ በፈረንሳይኛ
"Montgomery Can Code" አጭር የመግለጫ ጽሑፍ፣ በፖርቹጋልኛ


ማሳሰቢያ

የአካዳሚክ ፕሮግራሞች የዳሰሳ ጥናት፡ MCPS ሁሉም ተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አማራጭ ኮርሶች ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማድረግ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞችን እየገመገመ ነው። አንዳንድ ፕሮግራሞች በተማሪዎች የአካባቢ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ጉዞ ያስፈልጋቸዋል። በዚህ የዳሰሳ ጥናት ከህብረተሰቡ የሚሰጡ አስተያየቶች የትኛዎቹ ፕሮግራሞች በተመጣጣኝ ፍትኃዊነት ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽ መሆን እንዳለባቸው ለመወሰን ይረዳል። ዲስትሪክቱ ከሁሉም ቤተሰቦች መስማት ይፈልጋል። እባክዎን አስተያየትዎን ለማጋራት ይህን አጭር የዳሰሳ ጥናት እስከ ቅዳሜ፣ ሜይ 31 ሞልተው ይመልሱ።

SSL ሰዓቶች እስከ ሜይ 30 መቅረብ አለባቸው፡ ከጁን 1, 2024 ጀምሮ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያጠናቀቁ ተማሪዎች አስፈላጊውን SSL እንቅስቃሴ ማረጋገጫ ቅጽ ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ እስከ ሜይ 30 ማቅረብ አለባቸው።

የኩሩ ማህበረሰብ ቀን፦ እሁድ፣ ጁን 1 ከቀኑ 1-4 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ Bethesda-Chevy Chase High School, 4301 East-West Highway in Bethesda. ዝግጅቱ ለሁሉም ዕድሜ ክፍት ነው፣ ይህ ዝግጅት የተለያዩ ተግባራትን ያካትታል፣ ትራንቪያ፣ ቢንጎ፣ ስነጥበብ፣ እና እደ ጥበባት፣ እንዲሁም ለወጣት ተማሪዎች የታሪክ ክፍለጊዜ ይኖራል። በተጨማሪ፥ በማህበረሰብ ድርጅቶች የሚቀርቡ የመርጃ ቁሳቁሶች ይኖራሉ። 

የሥነ ምግባር ፓነል የትምህርት ቦርድ አምስት አባላት በሚኖሩት ፓነል ላይ አንድ ክፍት ቦታ ለመሙላት ይፈልጋል። ከጁላይ 1፣2025 ጀምሮ ክፍት ቦታው የሚሸፈነው ለሶስት አመት የአገልግሎት ጊዜ ነው። ለማገልገል የሚፈልጉ ግለሰቦች ደብዳቤ እና የስራ ልምድ መግለጫ/resumés እስከ ሰኞ፣ ጁን 9ከቀኑ 5 p.m. ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ተጨማሪ መረጃ

ህይወት አድን CPR መስጠት ይማሩ፡ CPR እንዴት እንደሚሰጥ ለመማር እየፈለጉ ነገር ግን የሚማሩበት ጊዜ አላገኙም? የሜድስታር የጤና ባለሙያዎች፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት አደጋ መከላከያ አገልግሎት ሠራተኞች፣ እና MCPS የአትሌቲክስ አሰልጣኞች በእጅ-ብቻ CPR እና AED ወርክሾፕ ቅዳሜ፣ ጁን 14ከጠዋቱ 11 a.m.-1 p.m. በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነጻ ስልጠና ይሰጣል። ምንም የምስክር ወረቀት አያስፈልግም — ህይወት አድን ክህሎት ለመማር 10 ደቂቃ ብቻ ይውሰዱ።ለመሣተፍ ይመዝገቡ።

ወደፊትን የመፍጠር ኤክስፖ፡ ይህ በነጻ የሚካሄድ የቤተሰብ ዝግጅት እሑድ፣ ጁን 1 ከቀኑ 10 a.m.-2 p.m. ኪድ ሙዚየም ውስጥ "KID Museum" ይካሄዳል። ለሁሉም ዕድሜ መስተጋብራዊ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ጭምር ድሮኖች እና የሮቦቲክስ ውድድር፣ ቨርቹዋል እና ጥምር ሁነታዎችን ጨምሮ የጨረር ቴክኖሎጂ ማሳያዎች፣ 3D ህትመት፣ የስክሪን ህትመት፣ የእንቅስቃሴዎች እና የፈጠራ ተግዳሮቶች ይኖሩታል። እንዲሁም "Invent the Future Challenge" የፈጠራ አነሳሽነት የተዘጋጁ ከ 100 በላይ በተማሪዎች የተሠሩ የፈጠራ ግኝቶች ይቀርባሉ። አድራሻ፦ KID Museum is located at 3 Bethesda Metro Center, adjacent to the Bethesda Metro


በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

"Montgomery County’s Paint the Plow snowplow naming contest" ውድድር ስላሸነፈ የሬድላንድ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንኳን ደስ አላችሁ! የአሸናፊው ዲዛይን አርዕስት “Life is a Highway” በሚል ርእስ የተዘጋጀ ሲሆን የራይድ ኦን አውቶቡስ Sam Eig Highway አውራ መንገድ ላይ ያለ ሰራተኛን ያሳያል። ሃሊ ዌልስ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛነትን ደረጃ ይዟል፣ እንዲሁም ጁሊየስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በሶስተኛነት አሸንፏል።ያቀረቧቸውን ዲዛይኖች/ንድፎቻቸውን ይመልከቱ

የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ያንብቡ። 


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)