ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት አቀራረብ ላይ የሚደረጉ ለውጦች
MCPS በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት ማድረግ ላይ ከ 2025–2026 የትምህርት አመት ጀምሮ ማሻሻያዎችን ያደርጋል። ይህ ከ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የመጨረሻ ውጤት ስሌት ላይ የሚደረግ የማሻሻያ ለውጥን ይጨምራል። እነዚህ ለውጦች የተነደፉት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ወጥነት እንዲኖራቸው እና የተማሪዎችን ትምህርት እና ተጠያቂነትን ለማጠናከር ነው።
ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የማጠናቀቂያ ውጤቶች የሚመዘኑት የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ አማካይ ነጥብ ስሌት ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ሌሎች ለውጦች የሚደረጉት የድጋሚ ግምገማ እድሎች ላይ ግልልጽ ማብራሪያ መስጠትን፣ የማጠናቀቂያ ቀናትን፣ እና የግዜ ገደቦችን በመሣሰለ የተማሪዎች ስራ ላይ ወቅታዊ ግብረመልስ መስጠትን ያካትታሉ። በተጨማሪም፣በሁለተኛውና በአራተኛው የማርክ መስጫ ወቅቶች አስፈላጊው የዲስትሪክት አቀፍ ምዘናዎች በተመረጡ ኮርሶች ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ።
ወላጆች እና ተንከባካቢዎች በትምህርት አመቱ የልጆቻቸውን የትምህርት መረጃዎች ለመከታተል እንዲችሉ ParentVUE እንዲመዘገቡ እናበረታታለን። ተማሪዎች በአካዳሚክ እድገት ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት "Canvas" መጠቀም አለባቸው።
በፎል ወቅት ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ስለሚያጋሩ MCPS ድረገጽ ላይ ያገኛሉ።
ስለ ውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት ማድረግ ተመሣሳይ ማድረግ 2025-2026
የትምህርት ቦርድ 2026 የስራ ማስኬጃ በጀትን እና ስትራቴጅክ/ስልታዊ እቅድ አፅድቋል።
የትምህርት ቦርድ 2026 የበጀት ዓመት (FY) የስራ ማስኬጃ በጀት አጽድቋል። ይህ ተግባር ያሉትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ፣አስፈላጊ የት/ቤቶችን ሥራ ድጋፍ ለማጠናከር እና በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ውጥኖች ለአዲስ የትምህርት ልህቀት ትኩረት ለመስጠት ቦርዱ እና ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ W. ቴይለር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።
$3.595 ቢሊዮን ዶላር በጀት ለመሠረታዊ ኢንቨስትመንቶች፣ ትምህርት ቤቶችን በቀጥታ ለመደገፍ፣ የተማሪዎችን ስኬት ለማጎልበት እና መዋቅራዊ ጉድለቶችን ለመቅረፍ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያግዝ ነው። የፀደቀው በጀት የተጠየቀውን 98.4% የሚያሟላ ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት በጀት ጋር ሲነፃፀር የ $273.2 ሚሊዮን ዶላር (8.2%) የኢንቨስትመንት ዕድገት ያሳያል። ይበልጥ ያንብቡ።
እንዲሁም ጁን 10 በተደረገው መደበኛ ስብሰባ፣ ቦርዱ ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ስኬት ግልጽ የሆነ ራዕይን የሚያንፀባርቅ ስለ MCPS የወደፊት ዝግጁ 2025–2030 ስትራቴጂክ እቅድ ተቀብሏል። እቅዱ ስለ ስኬታማ የትምህርት ስርአት አራት አላማዎችን የሚገልፅ ከመሆኑም በላይ የሚቀጥሉትን አምስት አመታት የትምህርት እድገትን የመከታተል መለኪያዎችን አስቀምጧል። የስትራቴጂክ ዕቅዱ ተማሪዎች በወደፊታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚፈልጓቸውን የክህሎት ስብስቦችን የሚገልጽ የተማሪ የወደፊት ዝግጁ ማዕቀፍ ያቀርባል፡ ሂሳዊ አስተሳሰብ፣ ግንኙነት፣ ትብብር፣ ፈጠራ፣ የማህበረሰብ ተፅእኖ እና ደህንነት ላይ ያተኩራል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
ሀሳብዎን ይንገሩን!
ስለ ቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገና መከፈት፣ ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፋፋት ላይ ያተኮረ የድንበር ጥናት ተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች ላይ ስለተገኙ እናመሰግናለን።
በተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎቹ ስለ 2027-2028 የትምህርት አመት የታቀዱ የትምህርት ቤት ድንበሮችን በቅድሚያ እንዲያውቁ ግንዛቤ ተሰጥቷል። እነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች የመጀመሪያ አማራጮችን ማሳወቅ እና በዚህ ሂደት ውስጥ ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ብቻ መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው።
የሚደረጉት ለውጦች የእርስዎን ተማሪ እንዴት ሊነኩ እንደሚችሉ አሁንም ጥያቄ ወይም ስጋት ሊኖርዎት እንደሚችል እናውቃለን። እናበረታታዎታለን፦
ካላቸው አቅም በላይ ተማሪዎች ያሏቸው ትምህርት ቤቶች ከጁላይ 1 በኋላ COSA ጥያቄዎችን አይቀበሉም።
MCPS ካላቸው አቅም በላይ ተማሪዎችን የመዘገቡ ትምህርት ቤቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው። ከታወቀ የምዝገባ አቅማቸው 10 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ቤት ምደባ ለውጥ (COSA) ጥያቄዎችን በዚህ ምክንያት ከጁላይ 1, 2025 ጀምሮ ይዘጋሉ። የተለየ ችግር ያለባቸው ወላጆች አሁንም COSA ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ፣ ነገር ግን መጠየቅ ያለባቸው ተማሪዎችን ከአቅማቸው በላይ ያልመዘገቡ ትምህርት ቤት መሆን አለበት። የምዝገባ እና የመቀበል አቅማቸው በየወሩ ይገመገማል።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪዎች በተመደበላቸው የመኖሪያ አካባቢ ት/ቤት ወይም ባለባቸው ግላዊ ሁኔታ ምክንያት በተመደቡበት የግላዊ ትምህርት ፕሮግራም (IEP) ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ይጠበቃል። ተማሪዎች በተወሰኑ መስፈርቶች መሰረት COSA ማመልከት ይችላሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ JEE፣ የተማሪ ዝውውር፣ COSA ለማጽደቅ ወይም ለመከልከል የሚደረግ ማጣራት፣ “የትምህርት ቤቱ አቅም፣ የክፍል ደረጃ፣ እና የክላስተር አቅምን ጨምሮ፣ የትምህርት ቤቱ አዳዲስ ተማሪዎችን የመቀበል ችሎታን የሚያሳዩ ሌሎች ጉዳዮችን ያጠቃልላል።
የአትሌቲክስ ማጣሪያ ኦገስት 13 ሊጀመር ተቃርቧል።
የፎል ወቅት አትሌቲክስ ቡድኖች እሮብ፣ ኦገስት 13 ማጣሪያ ሊጀምሩ ይችላሉ (ቅዳሜ፣ ኦገስት 16 መጀመር ነበረበት)። ቡድኖቹ ማክሰኞ፣ ኦገስት 12 የሚገለገሉበትን መሳሪያዎች ማሰራጨት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ የአካባቢዎን ትምህርት ቤት ያነጋግሩ።
በተጨማሪም MCPS የሚከተሉትን በስፕሪንግ ሻምፒዮና ያሸነፉትን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይፈልጋል፦
በዚህ ሠመር SSL ሰዓቶችን አግኙ!
ሠመር ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሠአቶችን የማገልገል እድሎች ላይ ለመሳተፍ እና 75 ሰአት የስቴት የመመረቂያ መስፈርቶችን ለማሟላት የሚያስችል ጥሩ ጊዜ ነው።
አምስተኛ ክፍል የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ከረቡዕ፣ ጁን 18 ጀምሮ SSL ዕድሎች ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
በአካል የሚገኙባቸው አንዳንድ አዝናኝ እድሎች ስላሉ MCPS SSL ድረ-ገጽ ላይ የተለጠፉትን መመሪያዎችን የሚያሟሉ የርቀት እድሎችን ይምረጡ። SSL ይህን ሊመስል እንደሚችል ምናልባት አላወቁም።
የፎረስት ኦክ ርእሰመምህር ብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች በማሸነፋቸው ተሸላሚ ሆነዋል።
"ይህ እውቅና የእኔ ላይ ብቻ አይደለም — በየቀኑ ከልባቸው፣ በአላማ ፅናት የሚተጉ እና በተማሪዎቻችን እምቅ አቅም የተገኘ በፎረስት ኦክ [መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት] ውስጥ ያሉ አስደናቂ ሰራተኞች ጥረት ጭምር ነው። እኔ የነዚያ ገፅታ ብቻ ነኝ” ሲሉ የ 2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መሪ ስለ ብዝሃ ቋንቋ ተማሪዎች ሽልማት የተበረከተላቸው ዶ/ር ዳሺያ ሰዌል/Dr. Dacia Sewell ተናግረዋል። በአመስጋኝነት እና በፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ የአመራር ችሎታቸው በፎረስት ኦክ ማህበረሰብ ላይ እንዴት ዘላቂ ተጽእኖ እያሳደረ እንደሆነ የበለጠ ያንብቡ። ይበልጥ ያንብቡ
ለዓመታዊው ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት የቀን መቁጠሪያዎን ምልክት ያድርጉ
MCPS ቅዳሜ፣ ኦገስት 23 ከጠዋቱ 10 a.m.–1 p.m. አመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርኢት በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ ማዕከል ያስተናግዳል። ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤቶች ስርዓትአቀፍ መረጃ እና ስለ ካውንቲ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች የሚያውቁበት ጥሩ ዝግጅት ስለሆነ አጋጣሚውን ይጠቀሙ። በልጆች እንቅስቃሴዎች፣ ሙዚቃ፣ መዝናኛ እና ስጦታዎችን በማግኘት ይደሰቱ። የልጆች ክትባት የሚሰጥበት ክሊኒክ ይኖራል
አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road. በሠመር ወቅት በሙሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ጋር ይከታተሉ።
ማሳሰቢያ
የትምህርት ቤት ድባብ የዳሰሳ ጥናት፡MCPS ቤተሰብዎ በትምህርት ቤቶቻችን ስላለው ልምድ መስማት ይፈልጋል! የዳሰሳ ጥናቱ የሚዘጋው ሰኞ፣ ጁን 16 ስለሆነ እባክዎን ዛሬውኑ ሞልተው ይመልሱልን! (የዳሰሳ ጥናቱን መጠይቅ ለመሙላት፣ የተማሪዎ መታወቂያ ቁጥር ያስፈልግዎታል፣ ይህም ParentVue ላይ ይገኛል።) የትምህርት ቤት አውድ ነገሮች እንዴት እንደሚከናወኑ ብቻ ሳይሆን … በጋራ/በመተባበር እንዴት የበለጠ ማሻሻል እንደምንችል ነው።
ህይወት አድን CPR መስጠት ይማሩ፡ CPR እንዴት እንደሚሰጥ ለመማር እየፈለጉ ነገር ግን የሚማሩበት ጊዜ አላገኙም? የሜድስታር የጤና ባለሙያዎች፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት አደጋ መከላከያ አገልግሎት ሠራተኞች፣ እና MCPS የአትሌቲክስ አሰልጣኞች በእጅ-ብቻ CPR እና AED ወርክሾፕ ቅዳሜ፣ ጁን 14ከጠዋቱ 11 a.m.-1 p.m. በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነጻ ስልጠና ይሰጣል። ምንም የምስክር ወረቀት አያስፈልግም — ህይወት አድን ክህሎት ለመማር 10 ደቂቃ ብቻ ይውሰዱ። ለመሣተፍ ይመዝገቡ።
የሠመር ወቅት ምንባብ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ መፃህፍት አመታዊ የሠመር ወቅት ምንባብ ፉክክር ቅዳሜ፣ ጁን 14 ያቀርባል። ህጻናትን፣ ታዳጊ ልጆችን፣ እና ጎልማሶችን በመፃህፍት፣ በሙዚቃ፣ በቲያትር እና በኪነጥበብ "ዓለማችንን ማቅለም" ትእይንት ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል። ዝግጅቱ/ፕሮግራሙ እስከ እሑድ፣ ኦገስት 31 ድረስ ይቆያል። ይመዝገቡ
በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
ከሠርጉድ ማርሻል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ "ደብዳቤ አለዎት!" ከሚገለፅ በላይ ነው — ሊተርሲ፣ የፈጠራ እና የተማሪ ድምጽ የሚሰማበት ነው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
የምረቃ ሥነ ስርአቶች ዛሬ ይጠናቀቃሉ፡ የፎቶግራፍ ክምችት እንዳያመልጥዎት!
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org