አበይት ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፥ ጁን 26, 2025

የሠመር የምግብ አገልግሎት አሁን ተጀምሯል

የሠመር ምግብ አገልግሎት

18 አመት ወይም ከዚያ በታች ያሉ ልጆች ጤናማ እና የተመጣጠነ ምሳ ለመብላት ከሰኞ እስከ አርብ የሠመር የምግብ አገልግሎት ወደሚሰጥባቸው ቦታዎች ሊመጡ ይችላሉ። የሠመር ምግብ ፕሮግራም ትምህርት ቤቶች ዝግ በሚሆኑበት ጊዜ ለቤተሰቦች ያለምንም ወጪ "የአመጋገብ ክፍተትን" ለማስተካከል የተነደፈ ነው። 

የ 2025 የሠመር ምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ጣቢያዎችን ዝርዝር ይመልከቱ። ምንም ቀጠሮ አያስፈልግም፤ ምግብ በቦታው መበላት አለበት።

የሠመር ምግቦች ዝርዝር፦

2025 ሠመር በከረጢት የተዘጋጁ ምግቦች የሚቀርቡበት ጣቢያዎች ዝርዝር

2025 የሠመር ካፌ ጣቢያዎች ዝርዝር

ለበለጠ መረጃ የሠመር ፕሮግራሞችን ድረ ገጽ ይጎብኙ።


ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት ቤት ሲስተም መገንባት

የትምህርት ቦርድ ጁን 24 ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ስለ ትምህርት ቤቶች ደህንነት ወቅታዊ መረጃ አግኝቷል። የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነው — በዚህ ረገድ MCPS እድገት እያሳየ ነው።

በዚህ አመት MCPS ቁልፍ የደህንነት ጉዳዮችን የሚመለከቱ በርካታ ጥረቶችን አድርጓል፦

መረጃው እንደሚያመለክተው ባለፈው አመት የተማሪዎች የደህንነት ችግሮች ከ 1,069 ወደ 966 በመቀነሱ አጠቃላይ መሻሻል ታይቷል። በትልቁ መቀነስ የታየው የእርስበርስ መደባደብ/ጠብ እና ደንብ መተላለፍ ነው፤ከጦር መሳሪያ ጋር የተያያዙ ግጭቶችም ቀንሰዋል።

ጁን 24 መደበኛ ስብሰባ ላይ ለቦርዱ የቀረበውን ይመልከቱ


ሀሳብዎን ይግለጹልን!

2027-2028 የትምህርት አመት መጀመሪያ ላይ፣ MCPS ሁለት አዳዲስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ይከፍታል — ይኼውም ቻርልስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት — እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፋት ፕሮግራም ይጠናቀቃል። እነዚህን ት/ቤቶች ለመክፈት በሚደረገው ዝግጅት፣ ሁሉም ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ዲስትሪክቱ በካውንቲው ሰፊ ቦታዎችን የሚያካልል የት/ቤት ወሰኖችን እያጠና ነው።

ፀደይ ላይ/በስፕሪንግ ወቅት፣ MCPS የመጀመሪያ የድንበር ጥናት አማራጮችን ለማህበረሰብ አጋርቷል፤ እና አስተያየት እንዲሰጥበት አቅርቧል። ከብዙዎቻችሁ ሰምተናል — እና የሰጣችሁት ግብረመልስ ቀጣዮችን እርምጃዎች እንዴት መከወን እንዳለብን እየተመራንበት ነው።

ለውጦቹ ለተማሪዎ ምን ማለት እንደሆነ ጥያቄ ወይም ስጋት እንደሚኖርዎት እናውቃለን። እናበረታታዎታለን፦

ሴፕቴምበር ላይ፣ የተሻሻሉ ዕቅዶችን ለመገምገም እና ግብረመልስ ለመስጠት ሌላ ዕድል ይኖርዎታል።

ስለ ድንበር ጥናቶች ተጨማሪ መረጃ


"Regeneron Science Talent Search" አሁን ክፍት ነው!

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች ለሀገሪቱ አንጋፋው STEM ውድድር ኦሪጅናል ምርምር በማቅረብ እንዲወዳደሩ እና ወደፊት የሳይንስ መሪ ለመሰኘት እና ከፍተኛውን $250,000 ዶላር ሽልማት ለማሸነፍ እንዲወዳደሩ 2026 "Regeneron Science Talent Search" ማመልከቻ ለማቅረብ አሁን ክፍት ነው።

ኦንላይን ማመልከቻ ኦሪጅናል የጥናት ወረቀት፣ ድርሰቶች፣ ሪኮመንዴሽኖች፣ እና ትራንስክሪፕቶችን ማካተት አለበት። ድረገጻችንን ይጎብኙ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እና ሀሳቡን ባላችሁ የግንኙነት መስመር ለሌሎች ወጣት ሳይንስቲስቶች ለማሠራጨት የዚህ አመት የመጨረሻ ቀነገደብ ሐሙስ፣ኖቨምበር 6 ከቀኑ 8 p.m. ነው።


በዚህ ሠመር SSL ሰዓቶችን አግኙ!

በዚህ ሠመር SSL ሰዓቶችን አግኙ!

ሠመር ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሠአቶችን የማገልገል እድሎች ላይ ለመሳተፍ እና 75 ሰአት የስቴት የመመረቂያ መስፈርቶችን ለማሟላት የሚያስችል ጥሩ ጊዜ ነው።

አምስተኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች SSL ሰዓቶችን ማግኘት መጀመር ይችላሉ። በአካል የሚገኙባቸው አንዳንድ አዝናኝ እድሎች ስላሉ MCPS SSL ድረ-ገጽ ላይ የተለጠፉትን መመሪያዎችን የሚያሟሉ የርቀት እድሎችን ይምረጡ። SSL ይህን ሊመስል እንደሚችል ምናልባት አላወቁም።

ጁላይ ወር ያሉት እድሎች


ጁን 27 በሚካሄደው VAC የተማሪዎች እና መምህራን ነጻ የጋለሪ ንግግር ይቀላቀሉ

ከ MCPS የትወና ስነጥበብ ማዕከል፣ ከአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካትዘን ስነጥበባት ማእከል ከአሁን ጀምሮ እስከ ኦገስት 10 ድረስ በአሜሪካን ዩኒቨርስቲ ሙዚየም የሚታይ በተማሪ አርቲስቶች የተዘጋጀውን "Teen Experience" ይመልከቱ። ዝግጅቱ በነፃ የቀረበ የጋለሪ ጭውውት ተማሪዎች እና መምህራኖቻቸው የሚሳተፉበት ስለሆነ አርብ፣ ጁን 27 ከቀኑ 2-3 p.m. ይካሄዳል።

በተቀቡ ሥዕሎች፣ እንክብካቤዎች እና አስደናቂ አካባቢዎች፣ ይህ ኤግዚቢሽን ማንነትን፣ አእምሯዊ ጤናን፣ ቤተሰብን እና ዲጂታል ህይወትን ከታዳጊ ወጣቶች አንፃር ይዳስሳል። የወጣት ተሞክሮ "Teen Experience" ማደግ ማለት ዛሬ ምን ማለት እንደሆነ እንዲያስቡ በሁሉም እድሜ የሚገኙትን ይጋብዛል። 

የወጣት ተሞክሮ "The Teen Experience"


ለዓመታዊው ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት የቀን መቁጠሪያዎን ምልክት ያድርጉ

በዚህ ሠመር SSL ሰዓቶችን አግኙ!

MCPS ቅዳሜ፣ ኦገስት 23 ከጠዋቱ 10 a.m.–1 p.m. አመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርኢት በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ ማዕከል ያስተናግዳል። ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤቶች ስርዓትአቀፍ መረጃ እና ስለ ካውንቲ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች የሚያውቁበት ጥሩ ዝግጅት ስለሆነ አጋጣሚውን ይጠቀሙ። በልጆች እንቅስቃሴዎች፣ ሙዚቃ፣ መዝናኛ እና ስጦታዎችን በማግኘት ይደሰቱ። የልጆች ክትባት የሚሰጥበት ክሊኒክ ይኖራል

አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road. በሠመር ወቅት በሙሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ጋር ይከታተሉ።



በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

2024–2025 ስንሰናበት፡የትምህርት አመቱን አጠናቀናል። የ 2025 ተመራቂዎቻችንን እናከብራለንእና መልካም የሠመር ወቅት ይሁንልን!

የአምስተኛ ክፍል ተማሪ የልጅ ህይወት አድኗል፥ አንድ ቀን የሮሊንግ ቴረስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሚሠናበቱበት ሠዓት የትምህርት ቤት አውቶቡስ ሲመጣ አንድ ትንሽ ልጅ ከወላጁ አፈትልኮ ወደ አውቶቡስ መስመር ሲሮጥ በመመልከት የደህንነት ጥበቃ ሰራተኛው ጀፈርሰን ሬይስ የልጁን ህይወት ለማዳን ፈጣን እርምጃ ወስዷል።

የብሔራዊ ታሪክ የክብር ሽልማት፡ አምስት የተማሪ ቡድኖች ወደ 3,000 የሚጠጉ ተማሪዎችን ባስተናገደው የዘንድሮው የብሔራዊ ታሪክ ቀን ውድድር የፕሮጀክቶቻቸውን ብሄራዊ እውቅና አግኝተዋል። 

የሴት ልጅ ስልጣን፡ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሴቶች ውድድር ኮሚሽን ተማሪዎች ሌሎችን ለማነቃቃት እና ለማበረታታት ሚዲያን ይጠቀማሉ። አሸናፊዎቹን ይመልከቱ፦ 

በዜና ገጻችን ላይ በዲስትሪክቱ ዙሪያ ያሉ ወቅታዊ ሁነቶችን ስለምናቀርብ፣ የቅርብ ጊዜውን መረጃ ለማግኘት ይህን ድረገጽ ይከታተሉ።



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)