የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ/Logo

አብይ ጉዳዮች

ጁላይ 3, 2025

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

የሠመር ትምህርት እየተካሄደ ነው ስለ ሠመር ትምህርት ጥያቄ አለዎት? ይጠይቁን!

የሠመር ትምህርት ቤት እገዛ ከፈለጉ፣ ይሄን ቅጽ ይሙሉ። የሠመር ትምህርት ቤት ቡድን በተቻለ ፍጥነት ጥያቄዎን ገምግሞ ምላሽ ይሰጣል።

ለእርዳታ ይህን ቅጽ ይሙሉ።

የሠመር ወቅት የምግብ አገልግሎት አሁን ተጀምሯል

ዕድሜያቸው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በታች ለሆኑ ልጆች የሠመር ምግብ አገልግሎት ይሰጣል። ተማሪዎች ከሰኞ እስከ አርብ ምንም ወጪ የማይጠይቅ ጤናማ እና የተመጣጠነ ምሳ በካውንቲው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ማግኘት ይችላሉ። በ 2025 የሠመር ምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ጣቢያዎችን ዝርዝር ይመልከቱ። ምንም ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግም። ምግቦቹን በቦታው መመገብ አለባቸው።

የሠመር ምግብ ፕሮግራም ድረገጽ ይጎብኙ።

ትምህርት ቤት የሚጀመርበት ቀን፦ አርኮላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ለአርኮላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ቤተሰቦች 2025-2026 የትምህርት አመት በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል። የመዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች እና ለአርኮላ ት/ቤት አዲስ የሆኑ ተማሪዎች ጁላይ 7 ለሚካሄደው የተማሪዎች የሽግግር ቀን ተጋብዘዋል፣ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ጁላይ 8 ነው።

የኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤት ካለንዳር/ቀን መቁጠርያ ይመልከቱ።

ስለ ውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት የማቅረብ ደንብ

ስለ ውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት የማቅረብ ደንብ IKA-RA የተሻሻለው ሠነድ አሁን ተዘጋጅቷል። ከትምህርት አመት 2025–2026 ጀምሮ MCPS የማጠቃለያ ውጤት ስሌት እንዴት መሠራት እንዳለበት ለውጥ ተደርጓል። ይህም ከ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል። እነዚህ ለውጦች የተነደፉት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ወጥነት እንዲኖራቸው እና የተማሪዎችን ትምህርት እና ተጠያቂነትን ለማጎልበት ነው።

ወላጆች እና ተንከባካቢዎች በትምህርት ዓመቱ በሙሉ ስለ ልጆቻቸው የትምህርት ውጤቶች ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት ParentVUE እንዲመዘገቡ እናበረታታለን። ተማሪዎች በአካዳሚክ እድገት ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት "Canvas" መጠቀም አለባቸው።

በዚህ ፎል ወቅት ለትምህርት ቤቶች ተጨማሪ መረጃዎችን እናጋራለን።

የውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት ማቅረቢያ ድረገጽ ይጎብኙ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ 48ኛ የተማሪ ቦርድ አባል የአገልግሎት ዘመኗን ጀምራለች

የሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪ አኑቫ ማሎ/Anuva Maloo የትምህርት ቦርድ 48ኛ ተማሪ (SMOB) የቦርድ አባል በመሆኗ እንኳን ደስ አለሽ እንላለን።

ተጨማሪ ያንብቡ።

የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን የወደፊት ሁኔታ ለመቅረጽ እገዛ ማድረግ

በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ MCPS የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞቹን አጠቃላይ ግምገማ ማድረግ ጀምሯል። በ 2025–2026 የትምህርት አመት መገባደጃ ላይ ሙሉ ፕሮፖዛሉ ለትምህርት ቦርድ ይቀርባል። የሀሳብ እና የአስተያየት ግብአቶችን ማሰባሰብ፣ ሃሳቦችን ማጥራት፣ እና ማህበረሰቡን በማሳተፍ ውይይቶችን ማድረግ እንቀጥላለን።

ጥያቄዎን እና ያለዎትን ስጋት በዚህ ይላኩ።

ሀሳብዎን ይግለጹልን! የትምህርት ቤት ምደባ ለውጥ ሊኖር ይችላል።

ስለ ቻርልስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ስለ ክራወን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት እንዲሁም ስለ ደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፋፋት ለቤተሰብዎ ምን ተጽእኖ እንደሚኖረው አሁንም ጥያቄ አለዎት? በቢሮ ሰዓታችን ይቀላቀሉ፣ አስተያየት ይስጡ፣ በወላጅ የማህበረሰብ አስተባባሪዎች የሚስተናገዱ የማህበረሰብ ተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎችን ይቀላቀሉ እና የታቀዱትን የወሰን አማራጮች ይመልከቱ።

በተጨማሪ፣ በስፓኒሽኛ ቋንቋ ክፍለ ጊዜ Pregúntale a MCPS ጁላይ 9 ከቀኑ 6:30 p.m., MCPS en Español Facebook ላይ በቀጥታ ስለሚተላለፍ ይከታተሉ።

የሚያደርጉትን ተሳትፎ ይቀጥሉ፥ እዚህ የበለጠ መረጃ ይመልከቱ።

ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂዎች የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ስኮላርሺፕ ይገኛል።

የሞንትጎመሪ ኮሌጅ በ 2025 ስፕሪንግ/ፀደይ ወቅት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተመረቁ እና በዚህ ፎል ለተመረጡ የስራ ግብረሃይል ልማት ሠልጣኞች እና ቀጣይ የትምህርት ፕሮግራሞችን ባለ ስድስት ክሬዲት ኮርስ ለሚወስዱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች $1,000 ዶላር የትምህርት ስኮላርሺፕ ይሰጣል።

የብቁነት መሥፈርቱን በመመልከት እስከ አርብ፣ ኦገስት 1 ድረስ ማመልከቻ ያስገቡ።

በ ካትዘን አርት ማዕከል/Katzen Arts Center የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ታዳጊ ወጣት ተሞክሮ

ከ MCPS ቪዥዋል አርት ሴንተር በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በካትዘን የስነጥበባት ማእከል፣ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም ከአሁን እስከ ኦገስት 10 ድረስ የሚቀርበውን በተማሪ አርቲስቶች ፈጠራ የተዘጋጁ ትእይንቶችን ይመልከቱ።

የሥዕሎች ቅብ፣ እንክብካቤ እና አስደናቂ አካባቢዎች፣ ይህ ኤግዚቢሽን ማንነትን፣ አእምሯዊ ጤናን፣ ቤተሰብን እና ዲጂታል ህይወትን ከታዳጊ ወጣቶች ተሞክሮ ጋር በማነጻፀር ይዳስሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ።

በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

  • ብሔራዊ የወጣት ኦርኬስትራዎች፦ ለሠመር ጉብኝት ወደ ኒው ዮርክ እና ከአገር ውጭ ያቀኑትን የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ይገናኙ።

  • "2025 Montgomery Serves" ሽልማቶች፦ 10 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በቅርቡ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እውቅና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

ከ MCPS የበለጠ መረጃ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2025 Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ