የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ መለያ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኦገስት 07, 2025

አዲሱ የትምህርት ዓመት ተቃርቧል — ማወቅ ያለብዎት ጉዳይ ምን አዲስ ነገር አለ?

የውጤት አሰጣጥ ለውጦች፣ በት/ቤት የሞባይል ስልክ አጠቃቀም መመሪያ፣ የሽግግር ቀን እና ሌሎችም ዝርዝሮችን በተመለከተ ሳምንታዊው የሐሙስ መታወቅ ያለባቸው አበይት ጉዳዮች፦ ቤተሰቦች አዲሱን የትምህርት አመት ለመቀበል ማወቅ በሚያስፈልጓቸው ጉዳዮች ዙርያ ወቅታዊ መረጃዎችን ይሰጣል። ሳምንታዊ አበይት ጉዳዮች እና (አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ በጣም አስፈላጊ ነገሮችን ማሳሰቢያ ኢሜይሎች) እንዳያመልጥዎት።

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

ቀኑን ይቆጥቡ — ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ አውደ ርዕይ እየመጣ ነው!

MCPS ቅዳሜ፣ ኦገስት 23 ከጠዋቱ 10፡00 a.m እስከ 1 p.m. አመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ በሚከተለው አድራሻ ያስተናግዳል፦ Westfield Wheaton mall (11160 Veirs Mill Road in Wheaton) ስለ ትምህርት ቤት ስርዓት፣ በካውንቲው ስለሚገኙ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ይወቁ፣ ስጦታዎችን ይውሰዱ፣ እና ህጻናት ክትባቶችን ያግኙ። በሙዚቃ የታጀበ መዝናኛ ይኖራል፤እንደ ብስክሌት ሮዲዮ የመሳሰሉ ለልጆች አስፈላጊ የብስክሌት ደህንነት ክህሎቶችን ለማስተማር የተዘጋጁ አስደሳች እንቅስቃሴዎች ስለሚኖሩ ተገኝተው ይደሰቱ።

ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

አዲስ የተማሪዎች ሽግግር ቀን እየመጣ ነው፤ ኦገስት 25 — ምንድነው?

የተማሪዎች የሽግግር ቀን 2025-2026 የትምህርት አመት የሚከናወን አዲስ የሙሉ ቀን ዝግጅት ነው። ይህ የሽግግር ቀን ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳቸው በፊት ከአዲስ የትምህርት ምህዳር ጋር ትውውቅ እንዲኖራቸው እና የትምህርት ዝግጁነትን በማጎልበት አዲስ ወደ ትምህርት ቤት የሚገቡ ወይም ወደ አዳዲስ ህንፃዎች የሚገቡትን ተማሪዎች ሽግግር ለማቃለል የታለመ ነው።

ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ

የውጤት አሰጣጥ ስሌት ላይ ለውጦች ይደረጋሉ።

MCPS በዚህ የትምህርት አመት በሁለተኛ ደረጃ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት ማድረግ ላይ ጠቃሚ ለውጦችን ያደርጋል። ከ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የማጠናቀቂያ ውጤቶች የሚሰሉት በአራቱ የማርክ መስጫ ወቅት አማካይ ውጤት ላይ ተሞርኩዞ ይሆናል። እነዚህ ለውጦች የተነደፉት ወጥነትን ለማስፋት እና ተማሪዎች የሚጠበቅባቸውን ትምህርት የመቅሰም ግንዛቤ ለማጠናከር እንዲሁም በት/ቤት ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህር ችሎታ ለመለካት ነው።

ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ።

አነስተኛ ስልክ የመጠቀም ጊዜ = ይበልጥ ትምህርት የመማር ጊዜ ይሰጣል።

የተሻሻለው የተንቀሳቃሽ ስልክ እና የግል ሞባይል መሳሪያ አጠቃቀም ደንብ (COG-RA)፣MCPS በትምህርት ቀን የግል ሞባይል መሳሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ይገድባል። በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ እና የግል ሞባይል መሳሪያዎች በትምህርት ቀን ተዘግተው መቀመጥ አለባቸው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አስተማሪ በግልፅ ካልፈቀደ(ች) በስተቀር በትምህርት ቀን ተንቀሳቃሽ ስልክ እና የግል ሞባይል መሳሪያዎች በትምህርት ክፍለጊዜ ተዘግተው መቀመጥ አለባቸው። እነዚህ ለውጦች ትኩረትን የሚከፋፍሉ ሁኔታዎችን ይቀንሳሉ፣ በትምህርት ላይ ትኩረት ማድረግን ይጨምራሉ፣ እና በተማሪዎች መካከል በአካል ተሳትፎ የማድረግ ሁኔታን ያጠናክራሉ።

 

የአውቶቡስ መስመርዎን ይፈልጉ! የአውቶቡስ መስመር መረጃ ኦገስት 15ይወጣል።

2025-2026 የትምህርት አመት የአውቶቡስ መስመሮች ከኦገስት 15 ጀምሮ ይፋ ይሆናሉ። የአውቶቡስ መስመርዎን ለማግኘት እና ለመጀመሪያው የትምህርት ቀን ለመዘጋጀት የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍል ድረገጽ ይመልከቱ!

ይህን አሁኑኑ ያድርጉ! ለነጻ እና ለቅናሽ ዋጋ ምግብ (FARMS) ዛሬውኑ ያመልክቱ

የምግብ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ዛሬውኑ በኦንላይን ያመልክቱ! ምንም እንኳን ልጆቻችሁ ባለፈው አመት ብቁ ቢሆኑም በየትምህርት አመቱ አዲስ FAARMS ማመልከቻ መቅረብ አለበት። የፌደራል የገቢ ደረጃዎችን የሚያሟሉ ቤተሰቦች ለነጻ የትምህርት ቤት ምግብ ብቁ ናቸው፣ ነገር ግን ይህንን ጥቅማጥቅም ለማግኘት ማመልከት አለባቸው። በአንድ ቤተሰብ ለሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች የሚያስፈልገው አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት ክፍል ድረገጽ ይጎብኙ።

በእነዚህ 60 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተመዘገቡ ተማሪዎች ያለ ምንም ወጪ ቁርስና ምሳ ያገኛሉ፣ እና አባወራዎች በዝርዝር ውስጥ ያልተካተተ ሌላ ትምህርት ቤት ውስጥ የተመዘገበ(ች) ተማሪ ከሌላቸው በስተቀር FARMS ማመልከቻ ማቅረብ አያስፈልጋቸውም።

ስለ MCPS ዳራ የማጣሪት ሁኔታ ማወቅ ያለብዎት ጉዳይ

MCPS የተማሪዎች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የዋና ኢንስፔክተር ጽህፈት ቤት የበፊት ታሪክ/ዳራ ማጣራትን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ ካመለጠዎት እዚህ ሊያነቡት ይችላሉ። MCPS በሪፖርቱ ውስጥ የተገለጹትን ችግሮች እየፈታ ነው።

ምን እየተደረገ እንዳለ የበለጠ ለማወቅ ያንብቡ።

የሠመር ምረቃ ላይ መነሳንሶችን/መርገፍ የማዞር ጊዜው አሁን ነው - እንኳን ደስ አላችሁ!

የሠመር ትምህርት ቤት ምረቃ ዓርብ፣ ኦገስት 15 ቀን ጠዋት 10 a.m. በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ጥያቄ ካለዎት የሠመር ትምህርት ቤት አስተማሪ ያነጋግሩ።

በተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2025 Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ