የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ኤፕሪል 16 ባካሄደው የሥራ ክፍለ ጊዜ የትምህርት አመት 2026-2027 የሚቀርጹ የተለያዩ ጉዳዮችን ገምግሟል፤ ከእነዚህም ውስጥ የታቀዱ የቀን መቁጠሪያ/የካለንደር ማስተካከያዎች፣ በትምህርት ቤት ደህንነት እና ጥበቃ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች፣ ለሰራተኞች ዳራ ምርመራ አዲስ የታቀደ ፖሊሲ እና በተማሪዎች የምግብ ዋጋ ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦችን ያካትታል። በተጨማሪም ቦርዱ M.E.C.C.A. ቢዝነስ ለርኒንግ ኢንስቲትዩት ቀጣይዩ የቻርተር ትምህርት ቤት ግምገማ አካል አድርጎ ተወያይቷል።
እንዲሁም በዚህ ማሻሻያ ውስጥ፦ በትምህርት ዘርፍ የሴቶች መሪዎችን እና ስለመጪው የቦርድ አባል (SMOB) ምርጫ መረጃ የሚያንፀባርቅ አዲስ EdTalk ክፍል ላይ ተካቷል።
2026-2027 ካለንደር/የት/ቤቶች ቀን መቁጠሪያ | የት/ቤቶች ደህንነት እና ሠላም | ፖሊሲ GCC | የምግብ ዋጋ | MBLI ማሻሻያ | EdTalk | አርባዘጠነኛው ተማሪ የትምህርት ቦርድ (SMOB 49) ተወዳዳሪዎች
ቦርዱ በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ በመጥፎ የአየር ሁኔታ ምክንያት የሚደረጉ ለውጦችን በተመለከተ ከወቅታዊ መስፈርቶች ጋር እንዲጣጣም የትምህርት አመት 2026–2027 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያን/ካለንደር ለማሻሻል የታሰበ ነው።
የቀረበው ሀሳብ የትምህርት ቤቶችን የመጀመሪያ ቀን ወደ ኦገስት 20, 2026 እና የመጨረሻውን ቀን ወደ ጁን 11, 2027 ያዛውራል። የተሻሻለው የቀን መቁጠሪያ ከጁነትንዝ/Juneteenth holiday በዓል በፊት የትምህርት ጊዜ መጠናቀቁን ለማረጋገጥ ዲሰምበር 23 የማካካሻ ቀናትን እና ጁን አጋማሽ ላይ በርካታ ቀናትን ያካትታል።
ቦርዱ ኤፕሪል 30, 2026 ከታቀደው ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የማህበረሰብ አባላት በዳሰሳ ጥናቶች እና በኮሚቴ ስብሰባዎች አስተያየት የመስጠት እድል ይኖራቸዋል።
የዲስትሪክቱ ባለስልጣናት በሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ ት/ቤቶች ደህንነት እና ጥበቃ የተደረጉ ጥረቶችን በሚመለከት ወቅታዊ መረጃ አቅርበዋል።
ውይይቱ በትምህርት ቤት መግቢያዎች ላይ አካላዊ የደህንነት ጥበቃን ማሻሻል እና የተማሪዎችን ባህሪ እና የትምህርት ቤት ሁኔታን ለማሻሻል የታለሙ የመተግበር ተሞክሮዎችን ቀጣይነት ባለው መልኩ መተግበር ላይ አፅንዖት ሰጥቷል። የቦርድ አባላት ለተማሪዎችና ለሠራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ የመማሪያ አካባቢን መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
በተጨማሪ የቦርድ አባላት ለሠራተኞች፣ ለኮንትራክተሮች፣ እና ለበጎ ፈቃደኞች ስለ በፊት ታሪካቸው ማጣራት የቀረበውን አዲሱን የፖሊሲ GCC ረቂቅ ገምግመዋል።
ይህ ፖሊሲ ተማሪዎች ሊኖራቸው የሚገባቸውን ሁሉንም ጥብቅ የደህንነት መስፈርቶች መሟላታቸውን ለማረጋገጥ የማጣሪያ ሂደቱን ለማጠናከር እና ለማቀላጠፍ የታለመ ነው።
MCPS ለበጀት ዓመት 2027 በምግብ ዋጋ ላይ የሚደረጉ ለውጦችን ሀሳብ አቅርቧል። ሰራተኞች የሥራ ክፍያ እና የምግብ ወጪ መጨመር ዋና ዋና ምክንያቶች እንደሆኑ ጠቅሰው፣ ማንኛውም ለውጥ የፕሮግራሙን ቀጣይነት በመጠበቅ የአመጋገብ ደረጃዎችን ለማስቀጠል እንደሚረዳ አስታውቀዋል።
ቦርዱ MBLI’s ቻርተርን ለመሻር ሱፐርኢንቴንደንቱ ያቀረቡትን ሀሳብ በተመለከተ ከዲስትሪክቱ አስተዳደር እና M.E.C.C.A. የቢዝነስ ትምህርት ኢንስቲትዩት (MBLI) አመራር ገለጻዎችን አግኝቷል። አባላት በትምህርት ቤቱ የቀረቡትን የማስተካከያ እርምጃዎች በተመለከተ በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አስተዳደራዊ እና አፈጻጸም ላይ የተመሰረቱ ምክንያቶችን ተመልክተዋል። ጉዳዩ በዲስትሪክቱ የቻርተር ትምህርት ቤት ሰፊ ግምገማ አካል ሆኖ እየተገመገመ ነው። ለቦርዱ የቀረቡትን ሰነዶች እዚህ ይመልከቱ።

EdTalk: ሴቶች የትምህርት መሪዎች የቅርብ ጊዜ ምልከታ እንዳያመልጥዎት። በትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን በተዘጋጀው በዚህ ግልጽ ውይይት ላይ የአሜሪካ የማህበረሰብ ኮሌጆች ማህበር ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዴሪዮን ፖላርድ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አባል የሆኑት አት-ላርጅ ካርላ ሲልቬስትሬ ይገኙበታል። በጋራ፣ ሴቶች በትምህርት አመራር ውስጥ ስላላቸው ተጽእኖ፣ ተግዳሮቶች፣ እና ቀጣዩን ትውልድ የመምራት አስፈላጊነት ላይ ጠንካራ ግንዛቤዎችን ይሰጣሉ። አዲስ የቀረበውን ክፍል ይመልከቱ።

ለ 49ኛው ተማሪ የቦርድ አባልነት (SMOB) የመጨረሻ እጩዎችዎን ያግኙ!
በዚህ የእጩዎች መድረክ፣ ልዑል ዳዊት/Leul Dawit እና ሬሜይ ገርሜይ/Reemey Ghermay ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ያላቸውን ራዕይ ያካፍላሉ። በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ሰው ሰራሽ አዕምሮ (AI) የሚያሳድረውን ተፅእኖ እና የትምህርት ቤት ደህንነትን ከመቆጣጠር ጀምሮ እስከ መሠረተ ልማት ማሻሻል እና የተማሪዎችን መብቶች ማስፋፋት ድረስ፣ በትምህርት ቦርድ ውስጥ ድምጽዎን በተሻለ ሁኔታ የሚወክል እጩ ማን እንደሚሆን ይመልከቱ።
ሙሉውን ቪድኦ ይመልከቱ
ጥያቄና መልስ/Q&A: ስለ $3.7 ቢሊዮን ዶላር በጀት እና ከትምህርት ቤት ለቆ መውጣት ያላቸው አመለካከት።
መብረቃዊ ለውጥ:ተወዳጅ የትምህርት ቤቶች ፉክክር እና ምርጥ የካፊቴሪያ ምግብ።
የመዝጊያ/የማጠቃለያ ክርክር፡ ለምን የእርስዎ ድምጽ እንደሚገባቸው እንደሚያምኑ ይገልጻሉ።
የምርጫው ቀን ረቡዕ፣ ኤፕሪል 22 ነው። አሁን ይመልከቱ እና በመረጃ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ መራጭ ይሁኑ!
ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 28፣ የልዩ ማህበረሰብ ኮሚቴ (10:00 a.m.)
ሐሙስ፣ ኤፕሪል 30፣ የቦርድ መደበኛ ስብሰባ (4:00 p.m)
ሐሙስ፣ ሜይ 7 የቦርድ የሥራ ክፍለጊዜ (12:00 p.m.)
በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ።
Facebook፣ Instagram፣ Bluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org