አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ሜይ 1, 2026

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ኤፕሪል 30 ባካሄደው ስብሰባ የትምህርት ዓመት 2026–2027 የት/ቤቶች ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ማሻሻያዎችን አጽድቋል፣ አዲሱን Amplify Desmos የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት አጽድቋል፣ እንዲሁም በክፍል ደረጃዎች ሁሉ የሚሰጡ ትምህርቶችን ለማጠናከር በርካታ የሥርዓተ ትምህርት ማጎልበት ተነሳሽነቶችን አፅድቋል። ቦርዱ M.E.C.C.A. ቢዝነስ ለርኒንግ ኢንስቲትዩት (MBLI) ቻርተር እንዲሻር በቀረበው የሱፐርኢንቴንደንቱ ሀሳብ ላይ ድምጽ ሰጥቷል፣ ስለ ሠራተኞች ጠንካራ የበፊት ዳራ ማጣራት መስፈርቶችን አጽድቋል፣እና በተማሪዎች የምግብ ዋጋ ጭማሪ ላይ የቀረበውን ለውጥ የማድረግ አጀንዳ ውሳኔ ለሌላ ጊዜ አስተላልፏል። ሥነ ስርዓቱ ላይ የተካተቱት ብሔራዊ የበጎ ፈቃደኞች ሳምንት እና ብሔራዊ የተማሪዎች አመራር ሳምንት፣ ከዋልት ዊትማን፣ ከኩዊንስ ኦርቻርድ እና ከጄምስ ሁበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የስቴት ሻምፒዮን ቡድኖች እውቅና መስጠት እና ስለ ቀጣዩ የቦርድ አባል ምርጫ ወቅታዊ መረጃዎች ይገኙበታል።


2026-2027 የት/ቤቶች ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር | ፖሊሲ GCC | የሒሳብ ስርዓተ ትምህርት/ከሪኩለም | MBLI ቻርጀር | የምግብ ዋጋ | SMOB 49 | የሚከበርበት ሥነ ሥርዓት


2026–2027 የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ማሻሻያዎች

ቦርዱ ከወቅታዊ የስቴት መስፈርቶች ጋር እንዲጣጣም እና የተማሪዎችን የተቀላጠፈ እና የተሣለጠ የመማር ደረጃ ለመደገፍ 2026–2027 የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ማሻሻያዎችን አጽድቋል። የትምህርት አመቱ አሁንም ኦገስት 25 (ኦገስት 24 የሽግግር ቀን) የሚጀምር ቢሆንም፣ ቀደም ሲል የታቀዱ በርካታ የት/ቤቶች መዝጊያ ቀናት ወደ ትምህርት ቀናት ወይም ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀናት እንደሚሆኑ ማስተካከያ ተደርጎበታል። እነዚህ ማሻሻያዎች የሠመር ዕረፍትን እንዳለ ለመጠበቅ የሚረዱ ሲሆን፣ የትምህርት አመቱ እስከ ጁን 11, 2027 ድረስ እንደሚቀጥል ያረጋግጣሉ።

እነዚህ በጥልቀት ታስቦባቸው የተደረጉ ለውጦች ለአካዳሚክ ስኬት ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት እና ለማህበረሰብ ግብረመልስ ምላሽ ሰጪ መሆናቸውን ያንፀባርቃሉ። ለወደፊቱ ስኬታማ ዓመት ስናቅድ ስለ ቀጣይ አጋርነትዎ እናመሰግናለን!

የተሻሻለውን 2026–2027 የትምህርት ዓመት የት/ቤቶች ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር እዚህ ይመልከቱ።


ጥብቅ የዳራ ማጣራት (ፖሊሲ GCC)

ቦርዱ ለሁሉም ሰራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ እና በጎ ፈቃደኞች የበፊት ዳራ ማጣሪያ መስፈርቶችን በማጠናከር ፖሊሲ GCCለማፅደቅ ድምጽ ሰጥቷል። ይህ ፖሊሲ የተማሪዎችን ደህንነት ከመጠበቅ አንፃር የበለጠ ጥብቅ የሆነ የሠራተኞችን የበፊት ዳራ የማጣራት ሂደት ያረጋግጣል።

ፖሊሲ GCC የመጨረሻውን የተሻሻለ ሠነድ ያንብቡ።


አዲስ የሂሳብ ትምህርት፡ Amplify Desmos ጸድቋል

ቦርዱ "Amplify Desmos" ከቅድመ-መዋእለ ህጻናት እስከ ተቀናጀ አልጀብራ 2 ድረስ አዲስ ዲስትሪክት አቀፍ የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሆን በይፋ አጽድቋል/ወስኗል። ይህ ምርጫ 164 የማህበረሰብ እና የሰራተኞች ተወካዮችን ያካተተ ሰፊ የግምገማ ሂደት ተደርጎበታል። አዲሱ የትምህርት መርሃ ግብር የፅንሰ-ሀሳብ እሳቤዎችን እና የኮምፒውተር ቅልጥፍናን በማንፀባረቅ የዘመኑን MSDE ደረጃዎች ለማሟላት የተነደፈ ነው።

የሚተገበርበት የጊዜ ማእቀፍ፡

  • 2026–2027፡ አዲስ የቅድመ-መዋእለ ህጻናት-አልጀብራ 1 ሥርዓተ-ትምህርት ይጀመራል።

  • 2027–2028፡አዲሱ የተቀናጀ አልጀብራ 1 ኮርስ ሽግግር ይደረጋል።

  • 2028–2029የተቀናጀ አልጀብራ 2ትምሕርት ሽግግር ይደረጋል።

ይህንን ለውጥ ለመደገፍ፣ MCPS ቤተሰቦች በቤት ውስጥ ትምህርቱን ለሚወስዱት ለመርዳት ዕለታዊ የቪዲዮ መመሪያዎችን እና ፕሮብሌም መፍታት/ስሌት መልመጃዎችን የያዘ "Caregiver Hub" ያቀርባል።

እንዲፀድቅ የቀረበውን የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት ያንብቡ።


M.E.C.C.A. የቢዝነስ ትምሕርት ተቋም (MBLI) ቻርተር

የትምህርት ቦርድ M.E.C.C.A. የቢዝነስ ትምሕርት ኢንስቲትዩት (MBLI) ቻርተር እንዲሻር ሱፐርኢንቴንደንቱ ባቀረቡት አስተያየት ላይ ድምጽ ሰጥቷል፣ ይህም ከጁን 30, 2026 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። የቀረበውን ሀሳብ ስድስት አባላት ደግፈው ሁለቱ ደግሞ ተቃውመው ድምጽ ሰጥተዋል።

አብዛኛዎቹ የቦርድ አባላት ቀደም ሲል የማስተካከያ እርምጃዎች በተደረጉባቸው ጊዜያት የልዩ ትምህርት ሁኔታ ማሻሻያዎች ያልተሟሉ መሆናቸውን እና የአስተዳደር መለኪያዎችን በተመለከተ ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል። ቻርተሩን ለመሻር ከተወሰደው እርምጃ በኋላ፣ ቦርዱ ከሱፐርኢንቴንደንቱ የቀረበውን የማፍረስ/dissolution ዕቅድ አጽድቋል። የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አመራር ከአሁን ጀምሮ ተማሪዎች ወደ አካባቢያቸው ትምህርት ቤቶች ወይም 2026–2027 የትምህርት አመት ወደ ሌሎች አማራጭ ፕሮግራሞች እንዲመለሱ ድጋፍ መስጠት ይጀምራል።

የዚህ ሂደት አካል እንደመሆኑ፣ ሱፐርኢንቴንደንቱ እስከ ጁን 30, 2026 ድረስ ስለ መበታተን ዕቅዱ ወቅታዊ መረጃዎችን በየጊዜው ያቀርባሉ።

የቦርዱን የመጨረሻ ውይይት እና የድምጽ አሰጣጥ ይመልከቱ።


ለትምህርት አመት 2026–2027 ውሳኔ ሳይሰጥበት የተላለፈው የተማሪዎች የምግብ ዋጋ ጭማሪ

በተማሪዎች የምግብ ዋጋ ላይ $0.30 ጭማሪ እንዲደረግ የቀረበውን አጀንዳ በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ አልተሰጠበትም። ቦርዱ የቀረበውን ሀሳብ ተወያይቶበታል፤ ነገር ግን የትምህርት ቤቶችን አጠቃላይ የፊስካል ገጽታ እና የበጀት ሁኔታ ግልጽ ግንዛቤ እስኪገኝ ድረስ እርምጃውን ማዘግየት የተሻለ እንደሆነ ወስኗል።

ቀጣይ እርምጃዎች፡ ቦርዱ ተጨማሪ የተሟላ የፋይናንስ መረጃ ሲገኝ የቀረበውን ሀሳብ እንደገና ይመለከተዋል፤ እና አስቻይ ሁኔታ መኖሩን ከተረጋገጠ በሜይ ወር የሥራ ስብሰባ ላይ በድምጽ ውሳኔ የመስጠት ሁኔታ ይኖራል።


ልዑል ዳዊት የቦርዱ ቀጣይ የተማሪ አባል ሆኖ ተመርጧል።

በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልዑል ዳዊት ለትምህርት አመት 2026-2027 የትምህርት ቦርድ (SMOB) ተማሪ አባል በመሆን ተመርጧል። የልዑል ዳዊት የአገልግሎት ዘመን የሚጀምረው ጁላይ 1, 2026 ነው። ልዑል ዳዊት በጁን ወር የምትመረቀውን የሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆነችውን አኑቫ ማሉን ይተካል። ልዑል ዳዊት 49ኛ ተማሪ የቦርድ አባል ይሆናል። ይበልጥ ያንብቡ


EdTalk፡ በትምህርት ዘርፍ ሴቶች መሪዎች

EdTalk: በትምህርት የሴቶች መሪነት በቅርብ ጊዜ የቀረበውን ክፍል ይመልከቱ! በዚህ ማራኪ እና ሐቀኛ ውይይት ወቅት የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን ከአሜሪካ የማህበረሰብ ኮሌጆች ማህበር ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዴሪዮን ፖላርድ እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አባል ከሆኑት ከአት-ላጅ ካርላ ሲልቬስትሬ ጋር በውይይቱ ተሳትፈዋል። ሴቶች በትምህርት አመራር ውስጥ ስላላቸው ተጽዕኖ በጥልቀት ይዳስሳሉ፣ ያጋጠሟቸውን እንቅፋቶች ያጤናሉ፣ እና የወደፊት መሪዎችን መደገፍና መምከር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ያንፀባርቃሉ። ታሪኩን ይከታተሉ።


ሥነ ሥርዓቶች እና የተሰጡ እውቅናዎች

ብሔራዊ የበጎ ፈቃደኝነት ሳምንት

የቦርድ አባል ጁሊ ያንግ/Julie Yang በዲስትሪክቱ ውስጥ የበጎ ፈቃደኞችን ተጽእኖ በማክበር ብሔራዊ የበጎ ፈቃደኞች ሳምንት (ኤፕሪል 19-25, 2026) እውቅና ሰጥተዋል። በ ሊህ ብራድሌይ/Leah Bradley የሚመራው ኢምፓወርዚንግ ዘ ኤጅስ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለተማሪዎች ስላበረከተው ድጋፍ እውቅና ተሰጥቶታል። የክብር ተሸላሚዎቹ ርዕሰ መምህር ዳንኤል ዋልደር፣ እና የሊካ ባሬራ-ላቨርዴ (ዳይመንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)፣ ኬሲ ሜሬይ (ኬንስተን ፓርክውድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)፣ ሳሊ ካሜሮን (ኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) እና ዊኖና ሌኖን (ፍለወር ቫሊ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) ይገኙበታል።

ብሔራዊ የተማሪዎች መሪነት ሳምንት

ተማሪዎችን በመወከል የቦርድ አባል በሆነችው አኑቫ ማሉ/Anuva Maloo አማካኝነት የትምህርት ቤት ማህበረሰቦቻቸውን ከፍ የሚያደርጉ ተግባራትን ያከናወኑ የተማሪ መሪዎችን በማክበር ብሔራዊ የተማሪዎች አመራር ሳምንት (ኤፕሪል 24-30) እውቅና ሰጥተዋል። እውቅና ከተሰጣቸው መካከል ሃሊ ዷንግ፣ ትሬሲ ኤስፒኖዛ፣ ታንዲ ሌበር እና ክሪሽ ፑታ የሚገኙበት ሲሆን፣ ሚ/ስ ሼላ ቼሪም በተማሪ ፕሮግራሞች አመራር ላሳዩት ልዩ ብቃት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። 

MCPS የስቴት ሻምፒዮኖች

ቦርዱ የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት coed ትግል እና የሴቶች የቅርጫት ኳስ ቡድን፣ የኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴቶች የትግል ቡድን፣ እና የጄምስ ሁበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወንዶች የቅርጫት ኳስ ቡድንን ላሳዩት አስደናቂ ስኬት የስቴት ሻምፒዮን አትሌቲክስ ቡድኖችን አክብሮት ሰጥቷቸዋል፣ በዚህም ለጥሩ ስራዎቻቸው፣ ለቡድኖቻቸው እና ለስኬቶቻቸው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። 


ቀጣይ ስብሰባዎች

ሐሙስ፣ ሜይ 7፣ የቦርድ የስራ ክፍለ ጊዜ (12:00 p.m.)

ሐሙስ፣ ሜይ 14፣ የኮሙኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ የቦርድ አማካሪ ኮሚቴ (6:30 p.m)

ማክሰኞ፣ ሜይ 19፣ የልዩ ትኩረት ማህበረሰብ ኮሚቴ (9፡00 a.m.)
የፊስካል ማኔጅመንት ኮሚቴ (5፡30 p.m.)


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ። 

FacebookInstagramBluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org