MCPS ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ - ኦገስት 23
ቀኑን ያስታውሱ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርኢት የሚቀርብበት ቀን ተቋርቧል!

  • መቼ: ቅዳሜ፣ ኦገስት 23 ከጠዋት 10 a.m. እስከ 1 p.m.
  • አድራሻ: Westfield Wheaton, 11160 Veirs Mill Road, Wheaton

ይህ ነጻ ዝግጅት ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ክፍት ሲሆን 2025-2026 የትምህርት አመት የሚጀመርበት ቀን ነው።

ስለ MCPS፣ በካውንቲው ስለሚገኙት ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ለማወቅ፣ ስጦታዎችን ለመውሰድ፣ እና ክትባቶችን ለማግኘት ጎራ ይበሉ። በሥፍራው ተገኝተው በሙዚቃ፣ በመዝናኛ፣ እና በልጆች እንቅስቃሴዎች ይደሰቱ።

MCPS ከአምስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ ዝግጅቱ ሥፍራ የሚያመላልስ ነጻ መጓጓዣ ይኖረዋል። የበለጠ ለማወቅ እና ጉብኝትዎን ለማቀድ የዝግጅቱን ድረገጽ ይጎብኙ። 


በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org