ተዘጋጅተሃል/ተዘጋጅተሻል?

ክረምት እየመጣ ነው — ዋነኛው ጥያቄ … ዝግጁ ነዎት?

እኛ ለመርዳት ዝግጁ ነን።

ቀኖቹ እያጠሩና እየቀዘቀዙ ሲሄዱ፣ ትንሽ (ወይም ብዙ) በረዶ ሊያጋጥመን ይችላል። የበረዶ ቀን ሲሆን ት/ቤቶችን መክፈት፣ ዘግይቶ መክፈት፣ ወይም የበረዶ ቀን መሆኑን ለማሳወቅ ስንወስን ቤተሰቦችን ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ ምክንያቶች በትምህርት ቤት ስራዎች ላይ ስለሚያሳድሩት ተጽዕኖዎች ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለመስጠት ዝግጁ MCPS ነው።

ጥሪውን እንዴት እንደምናስተላልፍ

ደህንነት ለእኛ ተቀዳሚ ትኩረታችን ነው። ለዚህም ነው MCPS ትምህርት ቤቶች በሰዓቱ ይከፈቱ፣ ዘግይተው ይከፈቱ፣ ቀደም ብለው ይሰናበቱ፣ ወይም ት/ቤቶች መዘጋት አለባቸው የሚለውን ለመወሰን ደረጃ በደረጃ በሚደረግ ሂደት ላይ የተመሰረተ ውሣኔ እንጂ — በግምታዊ አሠራር አይደለም። በአካባቢዎ ሁኔታዎች ጥሩ ሆነው ሲታዩ ነገር ግን በሌሎች የካውንቲው አካባቢዎች ትክክለኛ የደህንነት ስጋቶች ሲኖሩ ሊያበሳጭ ይችላል—ቢሆንም ደህንነትን እናስቀድማለን። 

በአየር ሁኔታ ምክንያት ውሳኔ ሲሰጥ ምን እንደሚካተት

ከጠዋቱ 2 a.m., ጀምሮ እና ብዙውን ጊዜ ከቀኑ በፊት ባሉት ሰዓታት ውስጥ፣ ቡድናችን የመንገድ ሁኔታዎችን ይፈትሻል፣ በካውንቲው ውስጥ 500+ ካሬ ማይል በላይ ስፋት ያላቸውን ትንበያዎች ይገመግማል፣ እና ከመጓጓዣ፣ ከፋሲሊቲዎች እና ከአደጋ መከላከያ አጋሮች ጋር ምክክር ይደረጋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ በጣም ሰፊ ነው—እና አውቶቡሶቻችን፣ ተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን ለፕሮግራሞች፣ ለአትሌቲክስ እና ለስራ በሪጅኑ ውስጥ ረጅም ርቀት ይጓዛሉ። ለዚህም ነው ማንኛውም ውሳኔ ለአንድ ሰፈር ብቻ ሳይሆን በካውንቲውበጠቅላላ ተፈጻሚ መሆን ያለበት። የልጅዎ የትምህርት ቤት ሰራተኞች ሁልጊዜ በአካባቢዎ እንደማይኖሩ እና የእርስዎ አካባቢ መንገዶች ነጻ ቢሆኑም እንኳ በሌሎች አካባቢዎች ወደ ሥራ መሄድ የማይቻል ሊሆን እንደሚችል ያስታውሱ… እና ሠራተኞች ወደ ትምህርት ቤት መድረስ ካልቻሉ ትምህርት ቤት የለም ማለት ነው።

እና አሁን ስለ አስደሳች ነገሮች…

ከዚህ በታች ውሳኔ እንዴት እንደሚደረግ (ገበታ አዘጋጅተናል!)፣ የክረምት የአየር ሁኔታ እና የበረዶ ቀን "toolkit"፣ እና ሱፐርኢንቴንደንቱ “የበረዶ ቀን ጥሪ” ለማድረግ ሲዘጋጅ የሚያሳይ ቪዲዮ ያገኛሉ። ይህ ማስታወቂያ እንዳያመልጥዎት — በጣም የሚያጓጓ ይመስላል። በእርግጠኝነት በሚዘጋበት ቀን የበረዶ ቀን ሙሉ ቪዲዮ ይለቀቃል። በተጨማሪም፣ በቀለም ኮድ በተሰየመው የሁኔታ መግለጫ ላይ (ቀይ፣ ቢጫ፣ ሰማያዊ፣ ብርቱካናማ፣ እና አረንጓዴ) ቀለማትን በመጠቀም የመጨረሻውን ውሳኔ እንዴት እንደምናስተላልፍ ያያሉ፣ ስለዚህ ምን እየተከናወነ እንዳለ እና በትምህርት ቀን ምን ሊወሰን እንደሚችል ሁልጊዜ ማወቅ ይችላሉ።


ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ፣ ቀይ፣ ቢጫ፣ ሰማያዊ፣ ብርቱካናማ፣ ወይስ አረንጓዴ ሊሆን ይችላል?


የሱፐር ኢንተንደንቱ የቪድኦ መልክት


ቪዲዮ ይመልከቱ


ተዘጋጅተዋል? የክረምት ወቅት ዝርዝር ማረጋገጫ

ማድረግ ያለብዎት ነገሮች

በረዶ ለሚጥልበት ጊዜ፣ የሚያዳልጥ በረዶ ወይም የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ሲያጋጥም፣ ዝግጁ መሆንዎን ማረጋገጥ አለብዎት። ሊያደርጉዋቸው የሚችሏቸው ነገሮችን ዝርዝር እነሆ፦

ቤትዎን ማዘጋጀት

  • አካፋ እና የበረዶ ማቅለጫ ያዘጋጁ። በረዶ ያለበት የእግር መንገድ ላይ ጨው ወይም አሸዋ ይነስንሱ።

  • የእጅ ባትሪዎችን፣ ተጨማሪ ባትሪዎችን፣ ብርድ ልብሶችን እና ምናልባትም በባትሪ የሚሰራ ሬዲዮ ሊኖርዎት ይገባል።

  • ቧንቧ ቢፈነዳ የውሃ ማስተላለፊያውን እንዴት መዝጋት እንደሚችሉ ማወቅ አለብዎት።

  • የእሳት ማሞቂያ ማገዶ የሚጠቀሙ ከሆነ ችምኒውን (ጭስ መውጫው) ማጽዳት ያስፈልጋል።

  • የጭስ እና የካርቦን ሞኖክሳይድ ማስጠንቀቂያ መሣሪያዎች በትክክል መስራታቸውን ይፈትሹ።

  • ማሞቂያዎችን ተቀጣጣይ ከሚሆን ከማንኛውም ነገር ቢያንስ በሦስት ጫማ ርቀት ላይ ያስቀምጡ።

መኪናዎን ማዘጋጀት

  • የመኪናዎን ባትሪ፣ በጎማዎች ውስጥ ያለውን የንፋስ መጠን እና የመኪና መስታወት መጥረጊያዎች በትክክል መሥራታቸውን ያረጋግጡ። የመኪናዎ ነዳጅ ሙሉ መሆኑን ያረጋግጡ።

  • የበረዶ መፈቅፈቂያ እና የበረዶ መጥረጊያ ብሩሽ፣ የጃምፐር ኬብሎች፣ የመጀመሪያ እርዳታ ኪት፣ ብርድ ልብስ (ከተቻለ ሁለት) እና ለመኪና ክብደት የሚጠቅም የከረጢት አሸዋ እንዳለዎት ያረጋግጡ።

  • ወደ የትኛውም ቦታ ከመንዳትዎ በፊት መኪናዎን 30 ሰከንድ እስከ 1 ደቂቃ ድረስ ሞተር አስነስተው እንዲሞቅ ያድርጉ።

እራስዎን እና ቤተሰብዎን ማዘጋጀት

  • የትምህርት ቤት Chromebooks፣ ስልኮች እና ሌሎች መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ቻርጅ መደረጋቸውን ያረጋግጡ። 

  • ሰውነትዎን ሙቀት ለማግኘትና አእምሮዎን ለማነቃቃት እንደ እንቁላል፣ እርጎ፣ ወይም ኦትሜል የመሳሰሉ ፕሮቲኖችን ለመመገብ ይሞክሩ። ብዙ ውሃ ይጠጡ።

  • የማይበላሹ ምግቦችን፣ መክሰስ፣ ውሃ፣ እና መድሃኒቶችን ጨምሮ አስፈላጊ ነገሮችን አዘጋጅቶ መያዝ ያስፈልጋል። አስፈላጊ ከሆነ እንደ ፎርሙላ እና ዳይፐር የመሳሰሉ ተጨማሪ ነገሮችን እና የቤት እንስሳት ምግብ እና ለህፃናት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በጊዜ አዘጋጅተው ይያዙ።  

  • የክረምት ልብሶችን ያውጡ፡- የሚሞቅ ጃኬት፣ ጓንት፣ ኮፍያ፣ አንገትልብሶች፣ ወፍራም ካልሲዎች እና ቦት ጫማዎችን አዘጋጅተው መያዝ ያስፈልግዎታል።

  • ምናልባት ሙቀት ቢቋረጥብዎት (ብዙውን ጊዜ በቤትዎ ውስጥ ትንሹ ክፍል) የሚሞቅ "ደህንነቱ የተጠበቀ ክፍል" አዘጋጅተው፣ ብርድ ልብሶችን ወይም ሙቀት የሚሰጡ የመኝታ ልብሶችን ይጠቀሙ።

  • ስለ ጉዞ ሁኔታ ማሳሰቢያዎች እና ስለ አየር ቅዝቃዜ የሚሰጡ ማስጠንቀቂያዎችን ለማወቅ የአካባቢውን መመሪያ ይከተሉ።

ማድረግ ያለብዎት ነገሮች

MCPS ለኦፊሴላዊ የበረዶ ቀን በሩን ከዘጋ፣ በቤት ውስጥ ለመዝናናት እና (በእርግጥ ከበረዶ ኳስ መወራወር በኋላ) ለመሳተፍና ለመጫወት የሚያስችሉ ብዙ መንገዶች አሉ።

  • በቦርድ ጨዋታዎች ወይም ካርዶችን በመጫወት ይሟሟቁ፣ ከዚያም የፊልም ማራቶን ይከተላል። ሙቅ ቸኮሌት፣ ማርሽማሎው እና ፖፕኮርን የተሟላ ይሆናል። ምናልባት ዋይፋይ (Wi-Fi) ከጠፋ ፊልሞችን ለመመልከት ቀድመው ያውርዱ።

  • መጽሐፍ ያንብቡ። ሌጎስ ይገንቡ። በድምፅ ተነባቢ መጽሐፍ ወይም ፖድካስት ያዳምጡ። የቤተሰብ Mad Lib ተጫወቱ።

  • ካሜራ ወደ ውጭ ወስደው የእንቅስቃሴ ፎቶዎችን መቅረጽ ወይም የተፈጥሮ ፎቶዎችን አንሱ።

  • የበረዶ ገጽታ ያለው የጥበብ ስራ ለመስራት የግንባታ ወረቀት፣ መቀስ፣ ማርከሮች ወይም ቀለሞች፣ ሙጫ፣ ተለጣፊዎች፣ ፕሌይ-ዶህ ወይም ዶቃዎችን በመሰብሰብ ሥሩ። የበረዶ ግሎብ ወይም የጓደኝነት አምባሮችን እንዴት እንደሚሰራ በጉግል ተመልከቱ።

  • የቤት ውስጥ "scavenger hunt." አደን ያዘጋጁ።

  • የግል ፒዛዎችን ያዘጋጁ ወይም ኩኪዎችን ይጋግሩ።

  • የፊት ጭምብሎችን፣ የእጅ ጥፍር እና የእግር ጥፍሮችን በመጠቀም የስፓ ቀን ተጫወቱ።

  • የቪዲዮ ጨዋታዎችን ይጫወቱ ወይም የዳንስ ፓርቲ ይኑራችሁ።

  • "obstacle course or fort" ምሽግ ይገንቡ።

  • ከቤት ውጭ በጣም ቀዝቃዛ ካልሆነ ውጭ በእግር ተራመዱ። ተፈጥሮ መንፈስን የሚያድስ ሊሆን ይችላል፣ እና ከቤት ውጭ ጊዜ ማሳለፍ ስሜትዎን ሊያድስ ይችላል።

ምክረ ሀሳብ፡ የበረዶ ቀን የጥናት ማበረታቻ
እያንዳንዱ MCPS Chromebook ክረምት ከመምጣቱ በፊት ሙሉ በሙሉ ቻርጅ ስለሚደረግ፣ የበረዶ ቀን የትምህርት ቤት ስራዎችን ለመከወን ወይም ለመከታተል ሊጠቅም ይችላል።

20–30 ደቂቃዎችን ይውሰዱ

  • ማስታወሻዎችን ወይም የጥናት መመሪያዎችን ለመገምገም

  • ለመሥራት ያሰቡትን ሥራ ለመጨረስ።

  • በአስተማሪዎ የታዘዘ የኦንላይን የትምህርት ሥራ ግብዓቶችን ያስሱ።

  • የእርስዎን Google Drive ወይም Planner ያደራጁ።

  • አስተማሪ የሰጠ(ች)ውን ምዕራፍ አንብቡ (ወይም አንድ ምዕራፍ አስቀድመው ይጻፉ!)

ትንሽ ትኩረት የተደረገበት ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት መመለስን የበለጠ ምቹ ያደርገዋል — እና የቀረውን ቀን በበረዶ ለመዝናናት ክፍት ያደርገዋል።


MCPS ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ

  • ኢሜይል፣ አጭር የጽሑፍ መግለጫ እና MCPS ድረ ገጽ ላይ ይመልከቱ።

  • Alert MCPS

  • የሠራተኞች ኢሜል

  • የሚድያ አጋሮች

  • ማህበራዊ ሚዲያ

  • MCPS-TV(Comcast 34, Verizon 36, RCN 88)

  • የትምህርት ቤትዎን የመረጃ ገጽ ይከታተሉ

2025–2026 መደበኛው የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ስድስት የአስቸኳይ ሁኔታ የመዝጊያ ቀናትን ያካትታል፣ እና ቤተሰቦች ነገሮች የት እንዳሉ እንዲያውቁ በቀለም ኮድ መግለጫ የተሰጠበትን የአየር ሁኔታ መግለጫዎችን መጠቀም አለባቸው። ስለ እያንዳንዱ የቀለም ኮድ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን ድረ ገጽ ይጎብኙ ወይም QR ኮድ ይጠቀሙ።
https://www.montgomeryschoolsmd.org/emergency/closings/ 


አሁን ዝግጁ ነዎት

ይህን ሁሉ ካደረጉ፣ በይፋ ለክረምት ዝግጁ ነዎት -- ስለሚዘጋጁበት ሁኔታ መረጃ ስላገኙ ወቅቱ ለሚፈጥረው ለማንኛውም ነገር ዝግጁ ይሆናሉ። በረዶ ይጥላል? የሚያዳልጥ ሊሆን ይችላል? ክረምቱን ድንቅ እንዲሆን በማድረግ እንነቃቃለን ወይስ ሌላ ቀዝቃዛ ቀናት ብቻ ይሆናሉ? ለነገሩ… እስካሁን አላወቅንም። 

ነገር ግን አሁን እርስዎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት፣ MCPS እንዴት ጥሪ እንደሚያደርግ እና እያንዳንዱን የክረምት ቀን እንዴት በተሻለ ሁኔታ መጠቀም እንደሚችሉ በትክክል ያውቃሉ። ስለዚህ መዘጋጀት ያስፈልጋል፣ እና ቀጥሎ ተፈጥሮ ለሚያስከትለው ለማንኛውም ነገር ተዘጋጁ!


በዚህ አድራሻ ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org