ስለ MCPS የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያ/ካላንደር መሻሻል መልካም ዜና

ውድ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና ቤተሰቦች

ተማሪዎች ትምህርት የሚያጠናቅቁበት የመጨረሻ ቀን ሐሙስ፣ ጁን 18, 2026 ይሆናል። 

ሦስት ቀናት ተማሪዎች በትምህርት ላይ መገኘት አለባቸው የተባለውን እንዲሠረዝ ያቀረብነውን ጥያቄ ዛሬ፣ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ ተቀብሏል/በውሳኔ አጽድቋል።  ይህ የተራዘመ የትምህርት ቀናት እንዲቀር መፈቀዱ፣ ኤፕሪል 15 ተማሪዎች ቀደም ብለው ከትምህርት ቤት የሚለቀቁበት የትምህርት ቀን ጋር ተዳምሮ፣MCPS የትምህርት ዓመቱን ከተገለጸው ጊዜ ቀደም ብሎ እንዲያጠናቅቅ እና ሁሉንም በስቴት የተደነገጉ የትምህርት ጊዜ እንዲያሟላ ያስችለዋል።

ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ በርካታ የት/ቤቶች መዘጋት ከተከሰተ በኋላ፣ የተስተካከለው የትምህርት ቀን መቁጠሪያ አሁንም የስቴቱን የትምህርት መስፈርቶች ያሟላል እንዲያውም ያልፋል፤ ይህም ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 1,080 የትምህርት ሰዓታት እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 1,170 ሰዓታት በትክክል የሚያሟላ ነው። ግባችን የትምህርት ጊዜን ትርጉም ያለው ማድረግ ነው፣ እና እስከ ጁን መጨረሻ ድረስ ማራዘም ያንን ትርጉም እንደሚያጣ እናውቃለን። የትምህርት ዓመቱን እስከ ጁን መጨረሻ ድረስ ሳናራዝም፣ ቤተሰቦች ያላቸው መርሃ ግብሮች እንደተጠበቁ ሆነው እና በጸደይ ወቅት ከፍተኛ ከትምህርት ቤት መቅረት ሳይኖር የሚፈለገውን የትምህርት ጊዜ ሁሉ ማሟላት በመቻላችን ደስተኞች ነን እና አመስጋኞች ነን።

ይህ ለእርስዎ ምን ማለት ነው፡

  • ሰኞ፣ ጁን 15 (ሙሉ ቀን)

  • ማክሰኞ፣ ጁን 16 (ሙሉ ቀን)

  • ረቡዕ፣ ጁን 17 (ሙሉ ቀን)

  • ትምህርት ቤት የመጨረሻ ቀን - ሐሙስ፣ ጁን 18 (ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን)

አርብ፣ ጁን 19 (ጁንቲንዝ) የፌዴራል እና የስቴት የዓል ቀን በመሆኑ ዝግ ነው (ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው)። 

ለአርኮላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያ የሚከተል ትምህርት ቤት)፣ የመጨረሻ ቀን ጁን 17 ይሆናል።

MCPS ለወደፊቱ ከአየር ሁኔታ ጋር ለተያያዙ የትምህርት መስተጓጎሎችም ከወዲሁ እየተዘጋጀ ነው። ማርች 26 ለትምህርት ቦርድ ከቀረበ በኋላ፣ MCPS ለሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ የመጥፎ የአየር ሁኔታ ቨርቹዋል የማስተማር እቅድ ያቀርባል። አንዴ ከፀደቀ በኋላ፣ ይህ እቅድ ት/ቤቶች ለብዙ ቀናት ዝግ ሆነው በሚቆዩ ጊዜያት ቨርቹዋል ትምህርት ትምህርት በመስጠት መቀጠል ያስችለናል። የወደፊት የትምህርት ቀናት መቆራረጦችን ለመቀነስ የሚቀጥለውን ዓመት የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ እንገመግማለን።

የቀረበውን ቨርቹዋል የትምህርት እቅድ እዚህ ማየት ይችላሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools


በዚህ አድራሻ ኢሜል ላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org