ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች
ማርች 26፣ 2026 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አዲስ የሁለተኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወሰኖችን እና በትምህርት ዲስትሪክቱ ውስጥ ለሚገኙ የሪጅናል ሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች አዲስ አቀራረብን አጽድቋል። በሥራ ላይ እንዲውሉ የጸደቁት ምክረሃሳቦች በዲስትሪክቱ ውስጥ ላሉ ተማሪዎች የትምህርት እድሎችን ማስፋት፣ የተማሪዎችን ምዝገባ ተለዋዋጭ አዝማሚያዎችን እና ወጥነት የሌላቸው የት/ቤቶች ህንጻዎችን የአጠቃቀም ችግር ለመፍታት የታለሙ ናቸው። እነዚህ ለውጦች 2027-2028 የትምህርት አመት መኸር ወቅት ፎል ሴሚስተር ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ።
ቦርዱ ሶስት እርስ በርስ የተሣለጡ ምክረ ሀሳቦችን እንደ አንድ ጣምራ ዕቅድ አጽድቋል፦
የቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ስለመከፈት እና ኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ማስፋፋት።
ቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ወደ ክራውን ፋርም ማዛወር እና ደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ማስፋፋት።
በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ የሪጅናል ሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች አቀራረብ መመስረት።
እነዚህ እርምጃዎች እርስ በርስ የተሣለጡ እና ተማሪዎች የሚኖሩበትን እና የሚማሩበትን አካባቢ በተሻለ ሁኔታ ለማሳለጥ እና በካውንቲው ውስጥ ካሉ የአካባቢ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ለተማሪዎች የፕሮግራሞችን ተደራሽነት እድሎች ለማስፋት የተነደፉ ናቸው።
እነዚህ ውሳኔዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን እንደሚነኩ በመረዳት፣MCPS ግልፅነት የሰፈነበት እና አሳታፊ ሂደት በመፍጠር ሲሰራ ቆይቷል። ዲስትሪክቱ በአካል ተገኝተው የተሳተፉባቸውን እና ቨርቹዋል ስብሰባዎችን አስተናግዷል፣ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች አጋርቷል፣ እና ካርታዎችን እና መረጃዎችን በይነመረብ ላይ አቅርቧል። እነዚህ ጥረቶች ከመላው ካውንቲ ማህበረሰብ ጠንካራ ተሳትፎ እንዲኖራቸው አስችለዋል፣ እና የማህበረሰብ ግብረመልስ የሱፐርኢንቴንደንቱን ሀሳብ እና የቦርዱን የመጨረሻ ውሳኔ በመቅረጽ ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።
ስለ ፕሮግራሞች ወይም ስለ ትምህርት ቤት ወሰኖች በሚመለከት ፍጹም የሆነ መፍትሔ እንደሌለ ይታወቃል። በእነዚህ ውሳኔዎች ላይ የብዙ ቤተሰቦች አስተያየታቸው ተንፀባርቆ ቢታይም፣የአንዳንዶች ግን ላይታይ ይችላል። እያንዳንዱን ጥያቄ ማሟላት ባይቻልም እንኳ እያንዳንዱን አመለካከት ለማገናዘብ ጥንቃቄ ተደርጎበታል። MCPS ማህበረሰባችን በዚህ ሂደት ውስጥ ስላጋራው ጊዜ፣ የተሰጡ ግብዓቶች፣ እና ተገቢ አመለካከቶች አመስጋኝ ነው።
በመላው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ የማሽቆልቆል ሁኔታ እና ተመጣጣኝ ያልሆነ የትምህርት ቤት ህንፃዎች አጠቃቀም እያጋጠመ ነው። አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከአቅማቸው በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ መያዝ ከሚችሉት አቅም ያነሰ ስለሆነ ብዙ ክፍት ቦታ አላቸው። እና ለብዙ ዓመታት የሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራም አወቃቀራችን ለአንዳንድ ተማሪዎች የጠንካራ ትምህርት እድሎችን ይሰጣል፣ ነገር ግን ብዙ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ለፕሮግራሞች ፍትሃዊ ተደራሽነት አሳጥቷቸዋል ወይም ረጅም ጉዞ ስለሚፈጅ እድሉን ሳያገኙ ቀርተዋል።
ዛሬ የፀደቁት የወሰን እና የፕሮግራም እርምጃዎች፣ MCPS በርካታ ወሳኝ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች በጋራ እንዲያሳካ ጠንካራ መሰረት ይጥላሉ፦
ያለውን የትምህርት ቤት ቦታ በተሻለ መንገድ በመጠቀም የተማሪዎችን ቁጥር ማመጣጠን እና መጨናነቅን መቀነስ፤
ተማሪዎች ከአካባቢያቸው ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸውን የሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞችን የማግኘት ፍትሃዊ እድሎችን ማስፋት እና ማሻሻል፤
ስለ ፋሲሊቲዎች እና ስለ ካፒታል ኢንቨስትመንቶች የረጅም ጊዜ እቅዶችን ማጠናከር።
አሁን ምክረ ሀሳቦቹ በቦርዱ ተቀባይነት ስላገኙ፣ MCPS ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራል። የተደረጉት የወሰን እና የፕሮግራሞች ለውጦች ለተማሪዎች 2027-2028 የትምህርት አመት ላይ ተግባራዊ መሆን ይጀምራሉ። እነዚህን ለመተግበር ቀጣዩ የዕቅድ ደረጃ የሚከተሉትን ያካትታል፦
ለውጦቹ ለተማሪዎቻቸው የትምህርት ቤት ምደባ ምን ማለት እንደሆነ ከመግለፅ አንጻር ከቤተሰቦች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ይደረጋል፤
የሪጅናል ፕሮግራም አቅርቦቶችን በሚመለከት ከትምህርት ቤቶች እና ከመምህራን ጋር በሙያቸው ዘርፍ በቀጥታ መስራትን ጨምሮ፤ጥልቀት ያለው ሥርዓተ ትምህርት ማዘጋጀት፣
በሁሉም ሪጅኖች ውስጥ ካሉ የአንደኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች ጋር በመገናኘት ስላሉት የፕሮግራም እድሎች፣ እንዲሁም ተማሪዎች ለመማር የሚፈልጉትን ለመምረጥ ያላቸውን የጊዜ ማእቀፍ እና ሂደት በመሳተፍ በተገቢ ጊዜ እንዲያውቁ ማድረግ፤
እንደገና ለተከፈተው የውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ቤት አመራር መቅጠር፣ በክራውን ፋርም አካባቢ አዲሱን የቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ መቀጠል እና የውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ወደ አዲሱ ህንፃ ስለሚዛወርበት ሁኔታ ማቀድ።
ከ 2027–2028 የትምህርት አመት በፊት በኖርዝኢስት ኮንሰርቲየም ወይም ዳውንካውንቲ ኮንሰርቲየም የተመደቡ ተማሪዎች ወይም አሁን ባለው የምዝገባ ሂደት አማካኝነት በማዕከላዊ ቁጥጥር ስር ባለው ሪጅናል ወይም በካውንቲ አቀፍ ፕሮግራም 8ኛ፣ 11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች የተመዘገቡ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምደባን የመቀየር የጊዜ ሰሌዳ ከአጠቃላይ የትግበራ ጊዜ ሰሌዳ ሊለያይ ይችላል። ስለእነዚህ የሽግግር ልዩ ሁኔታዎች ቤተሰቦች የበለጠ ዝርዝር መረጃ ያገኛሉ፣ እና በውሳኔዎቹም ውስጥ ተዘርዝረዋል።
ይህ የረጅም ጊዜ ዕቅድ እያንዳንዱን ተማሪ አሁን እና ለሚመጡት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል። እነዚህ ውሳኔዎች ጥያቄዎችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ እንረዳለን፣ እናም ለውጦቹ በሚከናወኑበት ወቅት አብረን ወደፊት እየተራመድን ለቤተሰቦች እና ለማህበረሰቡ መረጃዎችን ለማጋራት ቁርጠኛ ነን። በሚቀጥሉት ሳምንታት፣ MCPS ለቤተሰቦች ትምህርት ቤት ተኮር መረጃዎችን እና የሽግግር የጊዜ ሰሌዳዎችን ያካፍላል፣ እንዲሁም በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ግንኙነቶችን እንቀጥላለን።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
በዚህ አድራሻ ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org