አበይት ጉዳዮች
ሴፕቴምበር 11, 2025
|
በዚህ ሳምንት ሊታወቁ የሚገባቸው ሶስት በጣም አስፈላጊ ነገሮችን እነሆ፦
ተጨማሪ ነገሮችን ለማወቅ ያንብቡ!
|
|
የሚቀጥለውን ዓመት የትምህርት ቤት ካለንደር/የቀን መቁጠሪያ ለመቅረጽ ያግዙን —ሀሳብዎን ያጋሩን!
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2026-2027 የትምህርት ቤት ካላንደር ለማዘጋጀት እየሠራን ስለሆነ የእርስዎን አስተያየት ግብአት እንፈልጋለን። አስተያየትዎን ለማጋራት ይህን ዳሰሳ እስከ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 30 ሞልተው ይመልሱልን። የእርስዎ ግብአት ለእድገት ሂደታችን አስፈላጊ አካል ነው። የዳሰሳ ጥናቱን ዛሬውኑ ይሙሉ!
|
|
|
ጠንካራ የኋላ ታሪክ ፍተሻ፣ የጣት አሻራ፣ እና ባጅ መስጠት እየተካሄደ ነው።
የተማሪዎቻችን እና የሰራተኞቻችን ደህንነት ሁል ጊዜ ቅድሚያ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የዋና ኢንስፔክተር ጽህፈት ቤት የወጣው የቅርብ ጊዜ ሪፖርት የኋላ ታሪክ የማጣራት ሂደቶች በሚፈለገው መጠን ጠንካራ ወይም ወጥ እንዳልነበሩ ግልጽ አድርጓል። በእነዚያ ግኝቶች ስለምንስማማ እነዚህን ጉዳዮች ለማስተካከል በፍጥነት እየሰራን ነው። ይህ ሥራ በሁሉም ዲስትሪክትአቀፍ የትምህርት ተቋማት ተጀምሯል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ |
|
|
የሚቀጥለው ዙር የድንበር ጥናት አማራጮችን የሚመለከቱ ስብሰባዎች በኦክቶበር ወር ይካሄዳሉ።
ነግረውናል፣ ስምተንዎታል። በኦክቶበር ወር የወሰን ጥናት አማራጭ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እቅድ ያዙ። የቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለመክፈት፣ የክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፋፋት የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ላይ በሚደረጉት ውይይቶች ማህበረሰቡ ስለ 2027-2028 የትምህርት አመት የተጣራ የድንበር አማራጮችን ያዳምጣል፣ አስረጂ ካርታዎች፣ ንድፎች፣ የመረጃ ሰንጠረዦች እና የካርታ ምስሎች ይቀርባሉ። ተሰብሳቢዎች ትርጉም ያለው አስተያየት መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ MCPS ለእያንዳንዱ የድንበር ጥናት የዳሰሳ ጥናቶችን ያጋራል። ቨርቹዋል ወይም በአካል የሚሳተፉበት ክፍለ ጊዜ ላይ ለመሳተፍ ያሉትን እድሎች ይመልከቱ።
MCPS የድንበር ጥናት ድረ-ገጽ
|
|
|
EdTalk Premieres ሴፕቴምበር 12
በሞንትጎሞሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ (BOE) ፕሬዝደንት ጁሊ ያንግ (Julie Yang)፣ ፣ የሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ዋና ዳይሬክተር አን ካዴሚን (Anne Khademien) እና የሞንትጎመሪ ካውንስል ፕሬዘዳንት ኬት ስቱዋርት (Kate Stewart) ስለወደፊት የትምህርት ዝግጅት ያደረጉትን አስደሳች ውይይት ፍንጭ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ። ሙሉው ተከታታይ ውይይት፣አርብ ሴፕቴምበር 12 ከቀኑ 12:01 a.m. ላይ በፖድካስት ይተላለፋል ይተላለፋል።
|
|
|
ስለ ክትባቶች እንዳይረሱ!
ሴፕቴምበር እስከሚገባደድ ድረስ፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ እና ሰብአዊ አገልግሎት ክፍል (DHHS) እድሜያቸው ለትምህርት ለደረሱ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ህጻናት በካውንቲው የተለያዩ ቦታዎች በትምህርት ቤት የሚወስዱ ክትባቶችን በነፃ ይሰጣል።
ተጨማሪ መረጃ ያግኙ፤ እና ቀጠሮ ይያዙ።
|
|
|
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲሱ የውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ ከኮሌጅ መግቢያ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ይገንዘቡ፦
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት አቀራረብ ፖሊሲ እና የኮሌጅ መግቢያ ሂደት ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 25 ክቀኑ 6፡30-8 p.m ላይ ውይይት ስለሚደረግ በዌቢናር ይቀላቀሉን። ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ፣ ከታውሰን ዩኒቨርሲቲ፣ እና ከሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጅ ፓርክ የምዝገባ ዳይሬክተሮችን ውይይት ያዳምጡ። ይመዝገቡ/Register.
ስለ ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት ማድረግ፣ እና የኮሌጅ ምዝገባዎች፣ ሴፕቴምበር 25, 2025
|
|
|
መደበኛ የምላሽ ፕሮቶኮል፡ አሁን ያውቃሉ
MCPS ስለ ከባድ ክስተቶች ለመግለጽ የተሻሻለ የደህንነት ፕሮቶኮል ተግባራዊ አድርጓል። መደበኛ ምላሽ የመስጠት ፕሮቶኮል (SRP) አምስት መመሪያዎችን ያካትታል፡ ባሉበት መቆየት፣ ጽናት፣ መቆለፍ፣ ለቆ መውጣት፣ እና ከለላ መያዝ። ትምህርት ቤቶች የአደጋ ጊዜ ዝግጁነታቸውን ለማረጋገጥ የደህንነት ሂደቶችን ይገመግማሉ፣ ያላቸውን ሪሶርሶች/መገልገያዎች ይጋራሉ፣ እና ልምምዶችን ያካሂዳሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
|
የሠመር የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶች ከሴፕቴምበር 26 በፊት መቅረብ አለባቸው።
በሠመር ወቅት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰአታትን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የተግባር ማረጋገጫ ቅጾቻቸውን ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ እስከ አርብ፣ ሴፕቴምበር 26 ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። ከ 6ኛ ክፍል በኋላ በ MCPS የተመዘገቡ ተማሪዎች የ SSL መስፈርትን በማጣጣት የሚያካክስ/ እፎይታ ያገኛሉ።
በአካል እና ቨርቹዋል አገልግሎት ለመስጠት ያሉት እድሎች፣ማሳሰቢያዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች በሙሉ SSL ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።
በሴፕቴምበር ወር ያሉት እድሎች
|
|
|
MCPS ውስጥ በጎ ፈቃደኝነት መሥራት ይፈልጋሉ?
MCPS በጎ ፈቃደኞችን ይቀበላል! ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች፣ እና የማህበረሰብ አባላት ለመርዳት ዝግጁ ስለሆኑ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች የበለጠ ጠንካራ ናቸው። በጉዞ ላይ ተማሪ ልጆችን በማጀብ፣ በማሰልጠን፣ ወይም በክፍል ውስጥ በመርዳት በጎ ፈቃደኞች በተማሪዎች ላይ እውነተኛ ለውጥ ያደርጋሉ። ነገር ግን፣የእያንዳንዱን ልጅ ደህንነት ከመጠበቅ የበለጠ ምንም አስፈላጊ ነገር የለም። ለዚህ ነው ሁሉም በጎ ፈቃደኞች አስፈላጊውን ስልጠና እንዲያጠናቅቁ የምንጠይቀው — እና አንዳንድ በጎ ፈቃደኞች የጣት አሻራ የኋላ ታሪክ ማጣራት የመሳሰሉትን ማጠናቀቅ አለባቸው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…
ስለ Remind፣ ParentSquare፣ ParentVUE ያሉዎትን ጥያቄዎች መመለስ፡ አሁን በሰባት ቋንቋዎች ተተርጉሟል፣ይህ ባለአንድ ገጽ ልዩነቶቹን ግልጽ ማድረግ እና ለጥያቄዎችዎ መልስ መስጠት ይችላል።
የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች የስራ ትርኢት፡ አውደ ርዕዩ ከ10፡30 am.-12፡30 p.m. ይካሄዳል። ሐሙስ ሴፕቴምበር 18, በ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville የበለጠ መረጃ ለማግኘት 240-740-6080 ይደውሉ.
የሂስፓኒክ ቅርስ የሚዘከርበት ወር!፡የሞንትጎመሪ ኮሌጅ የሂስፓኒክ ቅርስ የሚዘከርበትን ወር ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 18 ከቀኑ 5-7 p.m. በሮክቪል ካምፓስ ለማክበር ፊስታ እያዘጋጀ ነው። ዋና ተናጋሪው ቪልማ ናጄራ (Vilma Najera) በዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ናት። ኮሌጁ በሚመጣው ወር የሚከበሩ ሌሎች ዝግጅቶችም አሉት፣ ውይይት የሚደረግበት የስፓኒሽ አውደ ጥናት፣ የላቲን ዳንስ፣ የአካል ብቃት ክፍል እና ዘጋቢ ፊልም ይኖራል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
|
|
ትምህርት ቤት በማይኖርበት ጊዜ? KID ሙዚየም ይኖራል!
KID ሙዚየም ትምህርት ቤቶች በሚዘጉበት ቀናት ካምፖች አሉት። የቀን ካምፖች ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 5ኛ ክፍል ተማሪዎች አርብ፣ ኦክቶበር 17 እና ሰኞ፣ ኦክቶበር 20. ከጠዋት 9 am. እስከ 4 p.m ክፍት ናቸው። ኪድ ሙዚየም/KID Museum የሚገኝበት አድራሻ፦ 3 Bethesda Metro Center in Bethesda. ለመሣተፍ ክፍያ ይኖራል።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ፤ ይመዝገቡ።
|
|
|
የዜና አምድ
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
|
|