የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ መለያ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ሴፕቴምበር 18, 2025

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

የሚቀጥለው ዙር የድንበር ጥናት አማራጮችን የሚመለከቱ ስብሰባዎች በኦክቶበር ወር ይካሄዳሉ።

ነግረውናል፣ ስምተንዎታል። በኦክቶበር ወር የወሰን ጥናት አማራጭ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እቅድ ያዙ። ስለ ቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን መከፈት፣ ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት፣ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ማስፋፋት በሚመለከት ለህብረተሰብ መረጃ የማጋራት ስብሰባዎች ላይ ስለ ትምህርት አመት 2027-2028 የተጣሩ የድንበር አማራጮችን በተመለከተ ለማህበረሰቡ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል። ተሰብሳቢዎች ትርጉም ያለው አስተያየት መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ MCPS ለእያንዳንዱ የድንበር ጥናት የዳሰሳ ጥናቶችን ያጋራል። ቨርቹዋል ወይም በአካል የሚሳተፉበት ክፍለ ጊዜ ላይ ለመሳተፍ ያሉትን እድሎች ይመልከቱ

MCPS የድንበር ጥናት ድረ-ገጽ

ስለ ፕሮግራሞች ትንታኔ የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜ ይቀላቀሉን

ቀኖቹን ያስታውሱ የፕሮግራሞች ትንታኔ ሲቀርብ ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ

MCPS የአካዳሚክ ፕሮግራሞቹን ተደራሽነት ለማስፋት ሪጅናል ሞዴል እየነደፈ ነው፤ ስለዚህም ብዙ ተማሪዎች—በካውንቲው ብዙ አካባቢዎች—ለመኖሪያ ቤታቸው ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች ጠንካራ የትምህርት ፕሮግራሞች ውስጥ መሳተፍ ያስችላቸዋል። ግባችን የላቀ ትምህርት እና ፍትሃዊነትን ማስፈን ነው። በሪጅን ደረጃ በማስፋፋት ፈጣን ነባር ፕሮግራሞችን እና ጥንካራ የትምህርት ፕሮግራሞችን እያበለፀግን ውስንነትን በርቀት በርቀት ምክንያት ያሉትን መሰናክሎች መቀነስ እንችላለን። የትምህርት ቦርድ ዲሴምበር 2025 የመጨረሻ እርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። MCPS ይህንን የፕሮግራም ትንተና የሚያካሂደው ለምንድን ነው? ይበልጥ ያንብቡ

ኮሌጅ ስለመግባት እና ተደራሽ ስለማድረግ

MCPS፣ Career Council, Inc. እና College Fairs USA አርብ፣ ኦክቶበር 10፣ 9:30 a.m.-12:30 p.m. በጌትስበርግ ቦኽረር ፓርክ የእንቅስቃሴ ማዕከል/Activity Center at Bohrer Park in Gaithersburg ስለ ኮሌጅ መግቢያ ሂደት አውደ ርዕይ ያስተናግዳሉ። ይህ ዝግጅት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ነው።

ከኮሌጁ ትርኢቱ በፊት፣ስለ ኮሌጅ ስኮላርሺፕ የመረጃ ልውውጥ በሚደረግበት የምሽት ፕሮግራም ላይ ይቀላቀሉን እና አቅም በሚፈቅድ ተመጣጣኝ ወጪ እንዴት ኮሌጅ መግባት እንደሚቻል ይወቁ። ሁለት ክፍለ ጊዜዎች ይካሄዳሉ፦

  • ኦክቶበር 7፣ 6-8 ፒ.ኤም፣ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ታኮማ ፓርክ ካምፓስ
  • ኦክቶበር 9፣ 6-8 ፒ.ኤም፣ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ጀርመንታወን ካምፓስ

በሁለቱም ክፍለ ጊዜዎች ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቆዎች መረጃዎች ይቀርባሉ። ይመዝገቡ/Register. ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።

ስለ MCPS አዲስ የውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ እና የኮሌጅ መግቢያ ሂደት በሚመለከት ሴፕቴምበር 25 ለሚደረገው የዌቢናር ውይይት መመዝገብ እንዳይረሱ። 6፡30-8 ፒ.ኤም ይካሄዳል 

የሂስፓኒክ ቅርስ የሚዘከርበት ወር

በአሁኑ ጊዜ በዋተርስ ላንዲንግ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሶስተኛ ክፍል መምህርት የሆነችው Miguelina Tejada መምህር መሆን ለተማሪዎቿ የተሻለ የወደፊት እድል ለመፍጠር የበኩሏን አስተዋፅዖ እንድታደርግ እንደሚፈቅድላት ታውቅ ነበር። የዶሚኒካን ሪፑብሊክ ዝርያ ያላት ስትሆን፣ የህይወት ጉዞዋ ትምህርትን እንዴት እንደሚያበረታታ እውቀት ነበራት። ይበልጥ ያንብቡ።

በህግ መወሰኛ ጉባኤ 2026 ቁልፍ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በጉልህ ተመክሮባቸዋል።

የትምህርት ቦርድ 2026 የህግ መወሰኛ መድረኮችን ይፋ ለማድረግ በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የህግ ማውጣት ስብሰባ አድርጓል። አራቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች፡- የመመረቂያ መስፈርቶች መደበኛ ግምገማ፣ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ወጪዎችን ቅድሚያ ትኩረት መስጠት፣ የላቀ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች ምደባ እና የኢንተርናሽናል ባካሎሬት ፈተናዎች ክፍያን ሚዛን በገቢ አቅም መጠን እንዲሻሻል ክለሳ ማድረግ፣ እና የትምህርት ሰዓቶችን ወይም የትምህርት ቀኖችን መስፈርት የማሟላት አማራጭ መመልከት ናቸው። የውይይቱን ማጠቃለያ ይመልከቱ።

የሞንትጎሞሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 100ኛ ዓመቱን ያከብራል

የሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 100ኛ የምስረታ በዓሉን ለአንድ ዓመት የሚያከብርበትን ዝግጅት እያካሄደ ነው። VIPs እና የክብር እንግዶች ከካውንቲው፣ ከስቴት፣ እና ከሀገር አቀፍ የትምህርት ተቋማት እና የማህበረሰብ ድርጅቶች የተውጣጡ ሰዎች በዓሉን ለማስጀመር አርብ፣ ሴፕቴምበር 26 ከቀኑ 5:30 p.m. በብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይገኛሉ። በዓሉ የሚመራው በብሌር የቀድሞ ተማሪዎች ማህበርነው።

አሁን ያውቃሉ፦ ልዩነቱ ምንድን ነው?

MCPS: ParentSquare፣ ParentVUE፣ Remind እና Canvas ወይም (MyMCPS Classroom) ላይ በርካታ የዲጂታል መሳሪያዎችን እንጠቀማለን። ግራ የሚያጋባ ነው አይደል? ስለዚህ ልዩነቱ ምንድን ነው? ከፋፍለን እንየው

EdTalk፣ አዲሱ የትምህርት ቦርድ አምድ

አምልጦት ከሆነ፣ ሴፕቴምበር 12 የተጀመረው EdTalk ትምህርት ቤቶቻችን ለወደፊት ዝግጁ ናቸው በሚል ርእስ ያማከለ ነው? የቀረበውን ይመልከቱ።

በተማሪዎች ጥገና የተደረገላቸው ኮምፒውተሮችን ለማግኘት ለኮምፒውተር ቤተ ሙከራ ያመልክቱ፦

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ተማሪዎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን/Montgomery County Students Information Technology Foundation, Inc. (ITF) እድሳት የተደረገላቸው ኮምፒውተሮችን ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ 501(c)(3) ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ይሸልማል። ቤተ-ሙከራው ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች፣ ዝርግ LCD ማሳያዎች፣ ኪቦርዶች፣ mice እና አንድ ፕሪንተር ያላቸው ስድስት የዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች ይኖሩታል። ማመልከቻ በኦንላይን ይገኛል። ጥያቄዎችን በቀጥታ ወደ Kelly Johnson ያቅርቡ፥ ወይም 240-740-2051 ይደውሉ። ማመልከቻዎች መቅረብ ያለባቸው እስከ ዓርብ፣ ኦክቶበር 3 ነው።

MCPS በብሔራዊ የትምህርት ቤት ምግብ ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋል፦

MCPS በብሔራዊ ትምህርት ቤት ቁርስ ፕሮግራም፣ በብሔራዊ የትምህርት ቤት ምሳ ፕሮግራም፣ ከትምህርት በኋላ በሚስጥ የመክሰስ ፕሮግራም፣ በአስጊ ሁኔታ ወቅት ከትምህርት በኋላ በሚሰጥ የእራት ፕሮግራም እና በቤተሰብ ቀን እንክብካቤ ፕሮግራሞች ውስጥ ይሳተፋል። ምግብ፦ ዘር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ዕድሜ፣ የአካል ጉዳተኝነት ወይም ብሔር ሳይለይ ለተመዘገቡ ተሳታፊዎች በሙሉ ይሰጣል፣ በምግብ አገልግሎት እና መገልገያዎች ተደራሽነት ላይ ምንም አይነት አድልዎ አይደረግም። MCPS ድረ ገጽ ላይ በተዘረዘሩት ጣቢያዎች ምግብ ይቀርባል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።

ከ… MCPS አመራር አንደበት!

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤት መሪዎች በዋና እሴቶቻችን ላይ ሃሳብብ ሲያጋሩ ያድምጡ። ይመልከቱ

ማሳሰቢያ

የዜና አምድ

  •  "Stitch by Stitch"፡ ፋሽን በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እያደገ ያለ ፕሮግራም ሲሆን ዲስትሪክቱ ሁለት ኮርሶችን ስለ ፋሽን ስዕላዊ መግለጫ እና ፋሽን ፕሮዳክሽን በዘጠኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየሰጠ ስላለ 2022 ዓ.ም ጀምሮ በእጥፍ እየጨመረ ይገኛል።
  • የቅርብ ጊዜ መረጃ ለማግኘት የዜና አምዳችንን ይመልከቱ።

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2025 Montgomery County Public Schools