የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ መለያ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኦክቶበር 2, 2025

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

የአካዳሚክ ፕሮግራም ትንተና፣ የክልል/የሪጅን ማስተካከያ እና የቤተሰብ መረጃ ክፍለ-ጊዜዎች ወቅታዊ መረጃዎች

MCPS ለእያንዳንዱ ተማሪ የመኖሪያ አካባቢያቸው የትም ቢሆን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ፕሮግራሞች እና የመማር እድሎችን እንዲያገኙ ለማድረግ አስፈላጊ እና የተቀናጁ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው። የአካዳሚክ ፕሮግራም ትንተና እና የድንበር ጥናቶች የተለያዩ ጥረቶች አይደሉም፣ ነገር ግን MCPS ትልቅ ቁርጠኝነት ያለው እቅድ በመንደፍ እና ግብዓቶችን በተገቢው ሁኔታ እና በፍትኃዊነት በማመቻቸት ተማሪዎች ጠንካራ ትምህርቶችን እንዲያገኙ እና ለወደፊታቸው ዝግጁ እንዲሆኑ ማስቻል ነው። የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ቀደም ሲል በሪጅን 5) እና ኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ቀደም ሲል በሪጅን 6) ክልላቸው/ሪጅናቸው ይቀየራል። ተጨማሪ ያንብቡ እና ይህ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ይወቁ።

ስለ ድንበር ጥናት አማራጮች ላይ ውይይት የሚደረግባቸው ስብሰባዎች ኦክቶበር 6 ይጀምራሉ።

በኦክቶበር ወር ለሚደረገው የድንበር ጥናት አማራጮች ስብሰባ ይቀላቀሉን። እነዚህ ለህዝብ መረጃዎችን የማጋራት ስብሰባዎች የሚደረጉት 2027-2028 የትምህርት አመት ላይ ስለ ቻርልስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገና መክፈት፣ ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መክፈት፣ እና ስለ 2027-2028 የትምህርት አመት ከህብረተሰቡ የተሰጡትን ግብአቶች የሚያንፀባርቁ የተጣራ የድንበር አማራጮች ይቀርባሉ።የስብሰባ ቀኖቹን ዝርዝር ይመልከቱ

የሂስፓኒክ ቅርስ ወርን ማክበር፡ በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመጀመሪይቱ ላቲኖ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር

አሊሺያ ዲኒ/Alicia Deeny የሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰመምህርት መሆኗ ሲነገራት፣ በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁ/ደ/ት/ቤት የተሾመች የመጀመሪያዋ ሴት ነበረች። እንዲሁም በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመጀመሪያዋ ላቲኖ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት ነበረች። ዲኒ/Deeny አሁን የሪቻርድ ሞንትጎመሪ ት/ቤት መሪነትን ከያዘች አምስተኛ አመቷን እያስቆጠረች ነው። ከፖርቶ ሪኮ ተወላጅ እናት እና ከኒው ጀርሲ የአይሪሽ ተወላጅ ከሆኑት አባት በዋሽንግተን ዲሲ የተወለደችው ዲኒ እና እህቷ በአያቶች፣ብዙ አክስቶች እና በአጎቶች በፍቅር ተከብበው ስለ ዘሮቻቸው እና ስለ አስተዳደጋቸው ታሪክ በስፋት ተምረዋል። ዲኒ/Deeny ብዙ ቁምነገሮች አሏት። ይበልጥ ያንብቡ።

2026-2027 FAFSA አሁን ክፍት ስለሆነ ቀደም ብለው ያመልክቱ።

2026-2027 ለፌደራል የትምህርት እርዳታ (FAFSA) ነጻ ማመልከቻ/Free Application አሁን ክፍት ነው። የሜሪላንድ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የትኛውንም አይነት የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እቅድ ቢኖራቸውም ማመልከቻዎቻቸውን ቀድመው እንዲያጠናቅቁ ይበረታታሉ፣ FAFSA ሞልተው በማስገባት፣ ተማሪዎች በስቴት ደረጃ፣ በፌደራል፣ እና በተቋም ፕሮግራሞች ምን ያህል የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች ማመልከቻዎችን ማቅረብ በቅርቡ ይጀመራል፣ ከኖቬምበር 7 በፊት መቅረብ አለበት።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በአካባቢያቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም ለሪጅናል እና ለካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች ለማመልከት የተለያዩ እድሎች አሏቸው። ረቡዕ፣ ኦክቶበር 8 ጀምሮ ወይም በዚያ ገደማ፣ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች "ParentVUE" ውስጥ የሚገኘውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማመልከቻ ቅጽ በመጠቀም ለሪጅናል/ለካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች ParentVUE ላይ የማመልከት እድል ይኖራቸዋል። በተጨማሪም፣ ከ 9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በተለያዩ የካውንቲው አካባቢዎች በትርፍ ጊዜ ለሥራ ዝግጁነት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለከፍተኛ ክፍል የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ሰኞ፣ ኦክቶበር 6 ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ። የሚፈልጓቸውን ቅጾች የሚያገኙባቸው ሊንኮች

9ኛ ክፍል
10ኛ ክፍል
11ኛ ክፍል

ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜዎች አሁን በመካሄድ ላይ ናቸው። በልዩ ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ላይ ሁሉንም ቀኖች ማየት ይቻላል። ማመልከቻ መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀነገደብ አርብ፣ ኖቨምበር 7 ከቀኑ እስከ 3 p.m. ነው። የበለጠ ግንዛቤ ይውሰዱ

አሁን ያውቃሉ፦ ስለ ድንበር ጥናት እና የፕሮግራሞች ትንተና

ድምጽዎን ለማሰማት እና የትምህርት ቤቶቻችንን የወደፊት ሁኔታ ለመቅረጽ MCPS ለእርስዎ ጠቃሚ እድሎችን ሰጥቷል። በመጀመሪያ የሚቀርበው የድንበር ጥናት፤ የትምህርት ቤት ድንበሮችን የሚመለከት ሲሆን የተማሪዎች ምዝገባን ለማመጣጠን፣ በት/ቤት ያሉትን ቦታዎች በብቃት ለመጠቀም፣ እና ለእያንዳንዱ ተማሪ ፍትሃዊ ተደራሽነትን በማረጋገጥ ላይ ያተኩራል። ለእያንዳንዱ ተማሪ ፍላጎታቸውን የሚያሟሉ ፕሮግራሞችን እንዲያገኙ ዲስትሪክቱ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትንተናላይ፣ ስለተዘጋጀው የሪጅናል እቅድ እና የፕሮግራሞች ትንተና እና ግምገማ ቨርቹዋል የመረጃ ክፍለ ጊዜዎች ይስተናገዳሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

Watch in Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ የምግብ አገልግሎት ማመልከቻ እስካሁን አቅርበዋል?

የምግብ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ዛሬውኑ በኦንላይን ያመልክቱ! የቤተሰብዎን FARMS ማመልከቻ ካላስገቡ፣ጊዜው ከማብቃቱ በፊት አሁን ያቅርቡ። ይህንን ጥቅም ለማግኘት በየትምህርት ዓመቱ አዲስ FARMS ማመልከቻ መቀረብ አለበት። MCPS ለማመልከት ብቁ ሊሆኑ የሚችሉትን ቤተሰቦች በሙሉ በወቅቱ እንዲያመለክቱ ያበረታታል። እባክዎ በኦንላይን FARMS ማመልከቻ MySchoolApps ላይ ስለሚገኝ ሞልተው ያቅርቡ (በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ትርጉሞች አሉ)። በአንድ ቤተሰብ ለሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች የሚያስፈልገው አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው።

ስለ ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞች፣ ቪዲዮዎችን እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የምግብ + ስነ-ምግብ አገልግሎቶችን ድረ ገጽ ይጎብኙ።

የተማሪ አገልግሎት ሠዓት (SSL) ይፈልጋሉ? አርቀው ይመልከቱ!

ለማስታወስ ያህል፣ ሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማግኘት አለባቸው።

ለዚህ ዓላማ የሚጠቅሙ በኦክቶበር ወር ያሉትን እድሎች ይመልከቱ። በአካል እና ቨርቹዋል አገልግሎት ለመስጠት ያሉት እድሎች፣ማሳሰቢያዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በሙሉ SSL ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ። 

ብላክሮክ/BlackRock ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የስነጥበብ ፕሮግራም በነጻ ያስተምራል

ብላክሮክ የስነጥበብ ማዕከል "BlackRock Center for the Arts" ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 5ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ነፃ የስነጥበብ እና የማህበራዊ/ስሜታዊ ትምህርት ከዚህኛው ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 4 ጀምሮ እስከ ዲሴምበር 13 ድረስ ያስተምራል። ትምህርቱ ስነ ጥበብን ከጽሑፍ እና ከቃላት ጋር በማጣመር የሚሰጥ ነው። የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ

የብላክሮክ አድራሻ፦ BlackRock is located at 12901 Town Commons Drive in Germantown

በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

  • ብሔራዊ የርእሰ መምህራንን ወር ማክበር ላይ፡ Spotlight on Stacey Brown ፣ በዊልያም ታይለር ፔጅ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር

  • ወጣቱ ጀግና የተሰጠው ክብር፦ ጄፈርሰን ሬየስ፣ በሮሊንግ ቴረስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ፣ ኦክቶበር 2024 ተማሪዎች ከትምህርት ቤት በተለቀቁበት ሠዓት አንድ ትንሽ ልጅ ጎትቶ ከአደጋ ስላዳነ በካውንቲው የአክብሮት እውቅና አግኝቷል።

  • የግንባታ ሰራተኞች ህብረት፡ በሳምንት ሁለት ጊዜ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፒክልቦል ሜዳ እየተገናኙ የሚጫወቱ፣ የሚወዳደሩ፣ እና የሚደሰቱ የሰራተኞች ቡድን እያደገ ወደ ጠንካራ ተወዳዳሪ ኃይል እና የሳቅ/የደስታ ማዕከልነት ተቀይሯል።

  • እንኳን ለ 100 ኛ ዓመት አደረሳችሁ!፡ የሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመቶ አመት ክብረ በዓሉን ሴፕቴምበር 26 ላይ አክብሯል።

  • ለውጡን የመሩ ተማሪዎች፦ የማይኖሪቲ ምሁራን ፕሮግራም አሁን 20ኛ ዓመቱ ላይ በቅርቡ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ማህበር ተሸልሟል።

  • ሙቀት መጋራት፦ "Operation Warm and Warner Brothers" —በኬምፕ ሚል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው አንዳንድድ እንዲደርስ ወደ 400 የሚጠጉ አዳዲስ ጃኬቶችን አበርክተዋል።

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2025 Montgomery County Public Schools