አበይት ጉዳዮች
ዲሰምበር 4, 2025
|
|
አስፈላጊ የተማሪዎች የአፈጻጸም ውጤቶች አሁን ParentVUE ላይ ይገኛሉ።
ወላጆች እና አሳዳጊዎች የተማሪዎቻቸውን የመኸር (Fall) የትምህርት እድገት መለኪያ (MAP) የትምህርት እድገት ግምገማ ውጤቶች አሁን ParentVUE ላይ ማየት ይችላሉ። ቤተሰቦች ParentVUE ዳሽቦርድ ላይ የተሰጡትን ደረጃ በደረጃ መመሪያዎችን በመጠቀም መክፈት እና የልጆቻቸውን ውጤቶች መመልከት ይችላሉ።
Fall 2025 የመኸር የትምህርት ውጤቶች ጀምሮ፣ አዲስ ብሔራዊ የንጽጽር መረጃዎችን (ደንቦችን) እየተጠቀምን ነው። ይህ ማለት የተማሪዎ RIT ውጤት ከአዲሱ የብሔራዊ አማካይ ውጤት ጋር ይነጻጸራል ማለት ነው፣ ይህም ምንም እንኳን ትክክለኛው RIT ውጤታቸው ባይለወጥም ከቀደሙት ዓመታት የበለጠ ከፍተኛ መቶኛ ደረጃ ሊያስከትል ይችላል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
የቅርብ ጊዜ EdTalk ትኩረት የተማሪ መሪዎችን በመገንባት ላይ ይሆናል።
በትምህርት ቦርድ አባል ጁሊ ያንግ/Julie Yang የተዘጋጀው አዲሱ EdTalk ፖድካስት ለተማሪዎች የአመራር ልምዶችን መስጠት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ፣ እነዚህ ልምዶች እንዴት እንደሚቀርቡ እና ጥቅሞቹን ያብራራሉ። እንግዶች በሥራ ጉዞአቸው ላይ የተማሩትን የአመራር ልምዶቻቸውን እና ክህሎቶቻቸውን ያካፍላሉ። የቀረበውን ይመልከቱ። |
|
|
አትዘግዩ፤ የዳሰሳ ጥናቱን ዛሬውኑ ይፈጽሙ!
MCPS በትምህርት፣ በኮሙኒኬሽን፣ እና በትምህርት ቤት እና በዲስትሪክቱ ስላላቸው አጠቃላይ እርካታ ልምዳቸውን እና ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ ወላጆችን/ተንከባካቢዎችን ይጋብዛል። የዳሰሳ ጥናቱ በቅርቡ የሚዘጋ ስለሆነ ዛሬውኑ ሞልተው ያቅርቡ!
የዳሰሳ ጥናቱ በስምንት ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል።
የዳሰሳ ጥናቱ የልጅዎን የተማሪ መታወቂያ ቁጥር ይጠይቃል። የልጅዎን መታወቂያ ቁጥር ParentVue ከፍተው የተማሪ መረጃ ላይ ጠቅ በማድረግ ማግኘት ይችላሉ። የሚሰጡት ምላሽ በሚስጥራዊነት ይጠበቃል፤የተማሪ መታወቂያው የሚያስፈልግበት ምክንያት ምላሾቹን ከትክክለኛው ትምህርት ቤት ጋር የሚገናኙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳናል።
|
|
|
አስተያየትዎን ያቅርቡ!
የትምህርት ቦርዱ በአራት ፖሊሲዎች ላይ በተደረጉ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል፤ የፖሊሲ DIG፣ የኦፕሬቲንግ ፈንድ ኢንቨስትመንቶች፣ ፖሊሲ DAA፣ የፊስካል ኃላፊነት እና ቁጥጥር፣ ፖሊሲ GIG፣ ጡረታን ለመደገፍ/የጡረታ ስርዓት የገንዘብ ድጋፍ እና ፖሊሲ IGS፣ አዳዲስ የትምህርት ቴክኖሎጂዎች። አስተያየቶቹ የሚቀርቡበት ቀነገደብ ረቡዕ፣ ዲሰምበር 17 እና ሰኞ፣ ጃንዋሪ 26 ድረስ መቅረብ አለባቸው።
ረቂቅ ፖሊሲዎቹን ይመልከቱ እና አስተያየት ይስጡ።
|
|
|
ቀኑን ያስታውሱ፦ በጀት ዓመት FY 27 የሥራ ማስኬጃ በጀት ዲሰምበር 17 ይቀርባል።
ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር ረቡዕ፣ዲሰምበር 17 ከቀኑ 6፡30 p.m. የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት ረቂቅ ያቀርባሉ። በኦንላይን እና በቴሌቪዥን በመመልከት ቨርቹዋል ይቀላቀሉን። ዝርዝሩ በቅርቡ ይለቀቃል።
ሱፐርኢንቴንደንቱ በዚህ ሳምንት ከሠራተኞች፣ ከወላጆች፣ እና ከማህበረሰብ አባላት የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎች ላይ አንደኛው በአካል ሌላኛው ደግሞ በቨርቹዋል የተካሄዱ አስተያየቶችን አድምጠዋል። ተሳታፊዎች አስፈላጊ ጥያቄዎችን ከማንሳታቸውም በላይ ሐቀኛ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
የክረምት ስፖርት "Winter Sports" የሚጀመርበት ወቅቱ አሁን ነው
የክረምት ስፖርቶች ተጀምረዋል! ዝግጅቶች የሚጀምሩት አርብ፣ ዲሰምበር 5 ነው። የጊዜ ሰሌዳዎችን ለማየት እና ቲኬቶችን ለመግዛት GoFan ይጎብኙ።
|
|
|
|
|
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አትሌቲክስ እንደገና የተዘጋጀውን ድረ ገጽ ይፋ አድርጓል።
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አትሌቲክስ የነደፈውን ድረ ገጽ ይፋ አድርጓል። አዲሱ ድረ ገጽ ከዚህ በፊት የሚያገኙትን ሁሉንም መረጃዎች—የጊዜ ሰሌዳዎችን፣ የቲኬት መረጃዎችን፣ የስፖርት ምዝገባ እና የጤና/ደህንነት ግብዓቶችን—እንዲሁም ከመላው ካውንቲ የተውጣጡ ሁነቶችን እና ስለ MCPS የአትሌቲክስ "ታሪኮችን" ያካትታል። በድረገጹ አናት ላይ ያለው ምልክት ተጠቃሚዎችን በቀጥታ ከማንኛውም MCPS የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአትሌቲክስ ድረ-ገጽ ጋር ያገናኛል። የድረ ገጽ ጣቢያው ከካውንቲው የተውጣጡ ሁነቶችን በቪዲዮ እና ከኢንስታግራም የተወሰዱ ቅንጭቦችን እንዲሁም የስፖርት ትረካዎችን ያካትታል።እዚህ ይመልከቱት!
|
|
|
SMOB ምን ያደርጋል? ዲሰምበር 16 ያገኛሉ!
ሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመለስተኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስለ ትምህርት ቦርድ የተማሪ አባል (SMOB) የምርጫ ሂደት እና SMOB ምን እንደሚያደርግ የበለጠ ለማወቅ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። SMOB 101 ፕሮግራም ላይ የሚሳተፉ ሰዎች ከቀድሞ SMOB እና የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች የሚቀርቡ ንግግሮችን ያዳምጣሉ። ቨርቹዋል ስብሰባው ማክሰኞ፣ ዲሰምበር 16 ከቀኑ 6-7:30 p.m. ይካሄዳል። ይመዝገቡ/RSVP።
|
|
|
ሱፐር ኢንተንደንቱ ዲሰምበር 8 የልዩ ትምህርት ተማሪዎች ወላጆች ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋሉ።
የልዩ ትምህርት አማካሪ ኮሚቴ (SECAC) ሰኞ፣ ዲሰምበር 8 ከቀኑ 7 p.m. ላይ ዙም/Zoom ስብሰባ ይካሄዳል (የስብሰባ መለያ ቁጥር፦ 891 9108 9916፤ የይለፍ ኮድ፦ 886463)። ዋናው ተናጋሪ ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር ናቸው። ተጨማሪ መረጃ፣ አጀንዳውን እና የዙም/Zoom ሊንክ ጨምሮ፣ የልዩ ትምህርት አገልግሎት ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።
የሚቀጥለው የልዩ ትምህርት አማካሪ ስብሰባ ዲሰምበር 8 ይካሄዳል።
|
|
|
አዲስ ሳይንቲስት ወይም መሐንዲስ ያውቃሉ?
ለሞንትጎመሪ ካውንቲ የሳይንስ ትርኢት ምዝገባ ክፍት ተደርጓል፣ ይህም የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳይንቲስቶች እና መሐንዲሶች ስራቸውን ለማሳየት እና የገንዘብ ሽልማቶችን ለማግኘት የመወዳደር እድል ይሰጣቸዋል።
በሲኒየር ዲቪዚዮን ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ወደ ሬጄኔሮን ዓለም አቀፍ የሳይንስ እና ምህንድስና ትርኢት (ISEF) የማለፍ እድል አላቸው፣ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተሳታፊዎች ደግሞ Thermo Fisher Junior Innovators Challenge (JIC) ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ።
|
|
|
ለትምህርት ቤቶቻችን ደህንነት ቅድሚያ መስጠት
ባለፈው ሳምንት፣ MCPS ቡድኖቻችን የዊትማን እና የሼርውድ ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል። ዲስትሪክቱ በዚህ ወር የሠራተኞችን የበፊት ታሪክ ፍተሻ፣ የጣት አሻራ፣ እና የባጅ መስጠት ሂደትን ለማጠናቀቅ በትክክለኛው መንገድ ላይ ይገኛል። ከዚህ በታች እስካሁን ድረስ ስለተከናወነው ሂደት ወቅታዊ መረጃ ይገኛል፣ ይህም እንደገና ማጣሪያ ያጠናቀቁ ሠራተኞችን ቁጥር የሚያንፀባርቅ ነው።
ሜትሪክ/Metric |
ቫልዩ/Value |
እስከ ዛሬ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ጠቅላላ ሠራተኞ ብዛት |
7,881 |
% የተጠናቀቀ የትምህርት ቤት ሠራተኞች |
67% |
# የተጠናቀቀ የትምህርት ቤቶች ብዛት |
184/211 |
|
|
|
ሠመር ራይዝ "Summer RISE 2025" አስተናጋጅ ለመሆን ምዝገባ አሁን ክፍት ነው።
የወደፊት ተነሳሽነት! ተማሪዎችን በሙያ ጉዞአቸው ይምሯቸው! MCPS ከጁን 22 እስከ ጁላይ 24, 2026 ለሚካሄደው 2026 የሠመር ራይዝ ፕሮግራም አስተናጋጆችን ይፈልጋል። የስራ ቦታዎን ለታዳጊ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጁንየር እና ሲንየር ተማሪዎች 50 ሰዓታት ተግባራዊ ትምህርት እንዲያገኙ—በቨርቹዋል፣ በአካል፣ ወይም በጣምራ ተሞክሮ ልምድ እንዲቀስሙ ክፍት ያደርጉ።
የመረጃ ስብሰባ ላይ በመሣተፍ የበለጠ ይወቁ፣ www.MCPS-SummerRISE.org ድረ ገጽ ይጎብኙ ወይም በስልክ ቁጥር 240-740-5599 Mr. Davida Gurstelle ያነጋግሩ።
|
|
|
የተሻለ እንግሊዝኛ መማር ይፈልጋሉ? የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ያቀርብልዎታል
የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ለሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች (ESOL) በርካታ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርቶችን ይሰጣል።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
|
የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምሽት KID ሙዚየም ውስጥ ይካሄዳል።
6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ያሏቸው ወላጆች ከመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር አርብ፣ ዲሰምበር 12 ከቀኑ 5:30-7:30 p.m. KID ሙዚየም ውስጥ 6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ጋር ማሳለፍ ይችላሉ። ተማሪዎች የተለያዩ ተግባራዊ STEM እንቅስቃሴዎችን የመሞከር እድል ይኖራቸዋል። የመግቢያ ዋጋ በአንድ ተማሪ $20 ነው። ወጪ እንቅፋት የሚሆን ከሆነ፣ Access for Every Maker ቅጽ ይሙሉ።
|
|
|
ከዜና አምዳችን
-
ከትምህርት ክፍል ወደ ማህበረሰብ፦ የሎንግቪው ትምህርት ቤት የተዋጣላት የኪነጥበብ መምህርት ሳራ ሉካስ-ድሬይስ ተማሪዎችን ሁሉንም አይነት የኪነጥበብ ስራዎችን እንዲሰሩ ትመራለች፣ አንዳንዶቹም ለትምህርት ቤቱ ገንዘብ ለማሰባሰብ ይሸጣሉ። በጣም ተፈላጊ/የሚሸጡ እቃዎች፡- በተማሪዎች የተሰሩ የጽህፈት መሳሪያዎች።
-
የላቲን ዳንስ መድረኩን አንጸባርቋል፡- በስትራትሞር በሚገኘው የሙዚቃ ማዕከል የተደረገው አመታዊ የሙዚቃ ውድድር፣ የሚያጓጓ እና አስደናቂ ትርኢቶች የተሞላበት ምሽት ነበር።
-
ትምህርት ቤቶችን ወደ ቤት ማገናኘት፡ MCPS ቤተሰቦች በልጆቻቸው የትምህርት፣ እድገት እና በአጠቃላይ ደህንነት ላይ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ ብሔራዊ የቤተሰብ ተሳትፎ ወር አክብሯል።
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
|
|