የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ጃኑዋሪ 22, 2026

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

በረዶ እየመጣ ነው፦
ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ

(ክሬዲት፡ ብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት – ጃኑዋሪ 22, 2026 ጥዋት 4:10 a.m.,)

የሳምንቱን መጨረሻ የአየር ሁኔታ ትንበያ በቅርበት እየተከታተልን ነው፣ እርስዎም እንደሚከታተሉ እናውቃለን። በአየር ሁኔታ ትንበያ መሠረት የሚያዳልጥ/የሚያሟልጭ በረዶ ከቅዳሜ ረፋድ ጀምሮ እስከ ሰኞ ጥዋት ድረስ እንደሚወርድ እየተነበዩ ናቸው (ብዙ በረዶ ሊሆን ይችላል)። ሁላችንም እንደምናውቀው፣ በረዶ መንገዶችን ወደ አንሸራታችነት እና እጅግ ቀዝቃዛ ሁኔታ እንደሚቀይር የህንፃዎችን (ቧንቧዎችን እና የማሞቂያ ሲስተሞችን ጨምሮ) ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ይቀይራል።

እንደተለመደው የተማሪዎች እና የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ሁኔታው በትምህርት ቤቶች ወይም በቢሮ ስራዎች ላይ የመዘጋት፣ ዘግይቶ መክፈት፣ ወይም የጊዜ ሰሌዳ ማስተካከያ የማድረግ ለውጦችን እንድናደርግ የሚያስገድዱ ከሆነ፣ በኢሜል እና በአጫጭር የጽሑፍ መልእክቶች፣MCPS ድረ ገጽAlert MCPS፣ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በአካባቢ ሚዲያዎች፣ MCPS-TV እና በትምህርት ቤት ዋና ድረ ገጾች ላይ በፍጥነት እናሳውቃለን። በተጨማሪም ቤተሰቦች በትክክል ሁኔታዎችን እንዲያውቁ ለመርዳት በቀለም ኮድ የመግለጽ ሲስተም መጠቀም እንቀጥላለን።

እባክዎን ዛሬ ስለ ምግብ ስርጭት እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች የተላከውን የማህበረሰብ መልእክት ይመልከቱ።

የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ መጨረሻ፡ 50 በመቶ/ፐርሰንት ደንብን መገንዘብ

የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ መጨረሻ፦
50 በመቶ/ፐርሰንት ደንብን መገንዘብ

የማርክ መስጫ ክፍለጊዜው (ጃንዋሪ 23) ሊያበቃ ስለተቃረብን፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ተማሪዎች ኮርሶቻቸውን እንዴት በተሳካ ሁኔታ ችሎታቸውን ማሳየት እንደቻሉ ሲገመግሙ፣ ስለ 50 በመቶ/ፐርሰንት ደንብ ጥቂት ማስገንዘቢያዎችን መስጠት እንፈልጋለን። 50 በመቶ/ፐርሰንት የሚያገኙት ተማሪዎች የሥራቸውን ትክክለኛነት ወይም ጥራት ለማሻሻል ከመምህራን ድጋፍ እና/ወይም ጣልቃ ገብነት ድጋፍ መጠየቅ ይችላሉ።

መምህር ዜሮ የሚመድበው በሚከተሉት ምክንያት ነው፦

  • ተማሪ የመምህር ድጋፍ እና/ወይም ጣልቃ ገብነት ድጋፍ የማይፈልግ ወይም ድጋፍ ካልጠየቀ(ች) ወይም ምንም አይነት ስራ ያልሠራ(ች) ከሆነ።
  • መምህሩ ተማሪው(ዋ) የተግባሩን መሰረታዊ መስፈርቶች ለማሟላት እንዳልሞከረ(ች) በግምገማ ከወሰነ።
  • ተማሪው በአካዳሚክ የማጭበርበር ድርጊት ውስጥ የተሳተፈ(ች) ከሆነ።

መምህራን ማንኛውንም ድጋፍ እና/ወይም የድጋፍ ጣልቃ ገብነት ይመዘግባሉ፣ ይህም በክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጭ የሚሰጥ ድጋፍን፤ እንደገና ማስተማርን፣ ወይም እንደገና መገምገምን ሊያካትት ይችላል። የውጤት ስሌቱ (Grade Calculator) ተማሪዎች በተለያዩ የቤት ስራዎች ላይ ያላቸውን አፈፃፀም ሲገመግሙ ጠቃሚ መሳሪያ ሊሆን ይችላል።

የትምህርት ውጤቶች፣ የቤት ስራዎች፣ እና የአስተማሪ ግብረመልስ በማንኛውም ጊዜ ParentVUE ላይ ክትትል ማድረግ እንደሚችሉ ያስታውሱ።

ለኮሌጅ ትምህርት ገንዘብ ይፈልጋሉ? FAFSA Can ሊረዳዎት ይችላል

ለኮሌጅ ትምህርት ገንዘብ ይፈልጋሉ?
FAFSA Can ሊረዳዎት ይችላል

የሚመረቁ ሲኒየር ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች፦ በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ኦንላይን ዝግጅቶች ወቅት የገንዘብ ድጋፍ እርዳታ መጠየቅ ይችላሉ።

የፋይናንስ እርዳታ ቢሮ "Office of Financial Aid" ቤተሰቦች በሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ለመርዳት አውደ ጥናቶችን እያካሄደ ነው።

  • የኮሌጅ ክፍያ፦ ክፍለ ጊዜዎቹ የሚጀምሩት ማርች 11፣ ሜይ 4 እና ጁን 10 ከቀኑ 6 p.m. ላይ ነው። ይመዝገቡ
  • ገንዘብ ይፈልጋሉ?: ክፍለ ጊዜዎቹ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 10፣ 17 እና 24 እንዲሁም ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 12፣19 እና 26 ይካሄዳሉ። በእነዚህ ክፍለ ጊዜዎች ቤተሰቦች FAFSA ወይም MHEC One-App (FAFSA ብቁ ላልሆኑ) ቅጾችን ለመሙላት ይረዷቸዋል። ይመዝገቡ

ተጨማሪ መረጃ

ስለ ነጻ የፌዴራል የተማሪ እርዳታ ማመልከቻ (FAFSA) እና ስለ ሜሪላንድ ስቴት የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ (MSFAA) የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? በኮሌጅኤት ዳይሬክሽንስ "Collegiate Directions" ስፖንሰር በሚደረጉት የወላጅ አውደ ጥናቶች መካከል በአንዱ ለመሣተፍ ያስቡበት። በእነዚህ ክፍለ ጊዜዎች ለጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት እና ተከታታይ ክፍለ ጊዜዎችን አንድ ለ አንድ 1፡1 ድጋፍ የማግኘት እድል ያገኛሉ።

ቀኖቹን ያስታውሱ፦ Rhythm and Story: Dance, Drumline Showcases & Film Festivalክብረ በዓል ይካሄዳል።

ቀኖቹን ያስታውሱ፦ Rhythm and Story: Dance, Drumline Showcases & Film Festivalክብረ በዓል ይካሄዳል።

ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪ ዳንሰኞች፣ ሙዚቀኞች፣ እና ፊልም ሰሪዎች የሚታዩበት በፌብሩዋሪ ወር የሚካሄዱ ሶስት ዝግጅቶች ይቀርባሉ፦

  • የዳንስ ትርኢት፦ ይህ 12ኛ አመታዊ ዝግጅት አርብ፣ ፌብሩዋሪ 20 ከቀኑ 7-8:30 p.m. ሲልቨር ስፕሪንግ ካምፓስ የሞንትጎመሪ ኮሌጅ የባህል ስነጥበባት ማዕከል ይካሄዳል። አድራሻ፦ Montgomery College’s Cultural Arts Center at the Silver Spring campus (7995 Georgia Avenue in Silver Spring) ለሕዝብ የሚቀርቡ ትኬቶች ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 14 ላይ ይገኛሉ።
  • Drumline Showcase፦ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 27 ከቀኑ 6 p.m. ላይ ኬንሲንግተን በሚገኘው አልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Albert Einstein High School, 11135 Newport Mill Road in Kensington. ይህ ዝግጅት፣ በቤት ውስጥ የሚካሄድ ሲሆን ከ10 በላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት "drumlines" ያካትታል። ቲኬቶች የሚሸጡት $5 ዶላር ሲሆን በር ላይ ይገኛሉ።
  • የወጣቶች ፀረ-ዘረኝነት ፊልም ፌስቲቫል/Youth Anti-Racist Film Festival፦ ይህ ዝግጅት በማይኖሪቲ ምሁራን ፕሮግራም እና Listen Tell Media ሚዲያ ስፖንሰር የተደረገ ሲሆን፣ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 21 ከጠዋቱ 10 a.m.–noon እስከ ቀትር ድረስ በተማሪዎች የተሰሩ ፊልሞችን በሞንትጎመሪ ኮሌጅ የባህል አርት ማዕከል በሚከተለው አድራሻ ያቀርባል። አድራሻ፦ Montgomery College, Cultural Arts Center (7995 Georgia Avenue in Silver Spring). ፌስቲቫሉ በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የተፈጠሩ እና የተዘጋጁ ፊልሞች በመሆናቸው በትምህርት ቤቶች እና በማህበረሰቦች ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚጥሩ ተስፋ ይደረጋል። ትኬቶችን ይግዙ ወይም ስፖንሰር ያድርጉ
የትምህርት ቦርድ በሦስት ፖሊሲዎች ላይ የሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ጠይቋል

የትምህርት ቦርድ በሦስት ፖሊሲዎች ላይ የሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ጠይቋል

የትምህርት ቦርድ በሦስት ፖሊሲዎች ላይ አስተያየት እንዲሰጥባቸው እየጠየቀ ነው፦

የረቂቅ ፖሊሲውን ቋንቋ ይገምግሙ እና አስተያየት ይስጡ።

የዛሬ ማታ "Special Ed Advisory Meeting" ቴራፒዩቲክ እና አካታች ካምፖችን ያቀርባል

የዛሬ ማታ "Special Ed Advisory Meeting" ቴራፒዩቲክ እና አካታች ካምፖችን ያቀርባል

የዚህ ወር የልዩ ትምህርት ዜጋ አማካሪ ኮሚቴ/Special Education Citizens Advisory Committee (SECAC) ስብሰባ ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 22 ከቀኑ 7 p.m. ላይ በዙም/Zoom ይካሄዳል። ንግግር አድራጊዎቹ ስለ ቴራፑቲክ ካምፖች እና አካታች የማህበረሰብ ካምፖች መረጃ የሚያካፍሉ የማህበረሰብ አጋሮችን ያካትታሉ። የዙም/Zoom ስብሰባ ሊንክ እዚህ ይገኛል።

ወደ ስፖርት ጨዋታ ይግቡ፡ የስፕሪንግ/የጸደይ ስፖርት ምዝገባ የሚጀመረው ጃኑዋሪ  26 ነው

ወደ ስፖርት ጨዋታዎች ለመግባት ይመዝገቡ፦
የስፕሪንግ/የጸደይ ወቅት የስፖርት ምዝገባ ጃንዋሪ 26 ይጀመራል።

ParentVue የስፕሪንግ/ጸደይ አትሌቲክስ ምዝገባ ፖርታል ሰኞ፣ ጃንዋሪ 26 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እኩለ ቀን ላይ ይከፈታል። ስለ ParentVue የመክፈቻ እና መግቢያ ፖርታል መረጃ MCPS ድረ ገጽ ላይ ይገኛል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስፕሪንግ/ጸደይ ስፖርቶች ቤዝቦል፣ የሴቶች ጂምናስቲክ፣ የወንዶች እና የሴቶች ላክሮስ፣ የሴቶች ሶፍትቦል፣ የወንዶች እና የሴቶች ቴኒስ፣ የወንዶች እና የሴቶች ትራክ እና የመስክ ፉክክር፣ የወንዶች እና የሴቶች መረብ ኳስ/ቮሊቦል እና ተጓዳኝ ሶፍትቦል የመሳሰሉትን ያካትታሉ። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስፖርቶች የወንዶችና የሴቶች እግር ኳስን ያካትታሉ።

የመጪው ትውልድ አዳዲስ መሪዎች ፕሮግራም ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው

የመጪው ትውልድ አዳዲስ መሪዎች ፕሮግራም
ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሴቶች ኮሚሽን ቅዳሜ ጃንዋሪ 31 ከጠዋቱ 11:30 a.m.-5 p.m. ድረስ 2026 የሴቶች ሕግ አውጪ መግለጫ ሮክቪል በሚገኘው ሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲስ ያስተናግዳል፣ አድራሻ፦ Universities at Shady Grove, 9630 Gudelsky Drive in Rockville.

ይህ ዝግጅት ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ስለ መጪው ትውልድ የመሪነት ፕሮግራም፣ በአመራር ክህሎት እና ችሎታ ማዳበር እና በሲቪክ ተሳትፎ ላይ ያተኩራል። አራት ክፍለ ጊዜዎች አሉ፤ ከቀኑ 2፡30-3፡15 p.m. (መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች) እና ከቀኑ 4፡45 p.m. (መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች)። ይመዝገቡ

ለተማሪዎች ማሳሰቢያዎች እና እድሎች

ለተማሪዎች ማሳሰቢያዎች እና እድሎች

HBCU Fair፦ በዚህ ዝግጅት ላይ ለመሣተፍ ይመዝገቡ፤ ዓርብ፣ ፌብሩዋሪ 13 ከቀኑ 6-8:30 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ The Universities at Shady Grove, 9630 Gudelsky Drive in Rockville. MCPS በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ቀደም ብሎ ተማሪዎች የሚለቀቁ ወይም ት/ቤት የመዘጋት ሁኔታ ካጋጠመው፣ እነዚያ የትምህርት ቀናት ወደ ቨርቹዋል የትምህርት ቀን ይዛወራል።

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጅንየር እና ሲንየር ተማሪዎችSummer RISE ምዝገባ፦ እስከ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 17 ድረስ ክፍት ነው። ይህ ፕሮግራም ተግባራዊ እና በሙያ ሥራ ላይ የተመሰረተ የመማር ልምድ ይሰጣል።

SMOB ፋይል የሚደረግበት ጊዜ፦ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች እስከ ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 29 5 p.m. ድረስ በእጩነት መቅረብ ይችላሉ።

"Choose Respect Video Contest" የቪዲዮ ውድድር፦ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ይህ ውድድር ታዳጊዎች በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች የፍቅር ጓደኞቻቸው ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት በተመለከተ ግንዛቤን የሚያበረታታ ኦርጅናል ቪዲዮ በፈጠራ አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ያበረታታል። ቪዲዎችን የሚያዘጋጁት በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ያስገኛል። የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ፌብሩዋሪ 15 ነው።

የጌትስበርግ መጻሕፍት አውደ ርዕይ የግጥም ውድድር/Gaithersburg Book Festival Poetry Contest: የዚህ ዓመት መወዳደሪያ ርእስ “What Is Humanity?” የተሰኘ ነው። የሚሳተፉ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ መሆን አለባቸው። የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ፌብሩዋሪ 20 ነው።

"Maryland Association for Environmental and Outdoor Education Scholarships" ለተመራቂ ሲንየር ተማሪዎች፣ MAEOE በኮሌጅ ወይም በማህበረሰብ ኮሌጅ በኢንቫይሮሜንታል መስኮች ማጥናት ለሚፈልጉ እጩዎች ሶስት የ $1,500 ዶላር የነፃ ትምህርት ዕድሎችን ይሰጣል። ማመልከቻዎች እስከ ሰኞ፣ ማርች 2 መቅረብ አለባቸው።

ስለ ውሃ ንፅሕና የፖስተር ዝግጅት ውድድር፡ ይህ ውድድር ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ ክፍል (K-12) ላሉ አርቲስቶች ክፍት ሲሆን ተሳታፊዎች ስለ ውሃ ንፅሕና እና ደህንነትን አስፈላጊነት በጉልህ የሚያሳይ ፖስተር በፈጠራ አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጠይቃል። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን እሑድ፣ ማርች 15 ነው። የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ያቅርቡ።

"Keeping It Safe Video Contest" የቪዲዮ ውድድር፦ ውድድሩ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ተማሪዎች 21 ዓመት እድሜ በታች የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች እና ጉዳቶች የሚገልጽ የ 30 ሰከንድ ቪዲዮ አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል። ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።

World Food Prize፦ የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ኢስተርን ሾር ኤክስቴንሽን 4-H ቡድን በሜይ ወር በሚካሄደው የሜሪላንድ የወጣቶች የዓለም የምግብ ሽልማት ላይ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን እንዲሳተፉ ጋብዟል። ይህ ዝግጅት ከምግብ ዋስትና ጋር በተያያዙ ወሳኝ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ የምርምር፣ የፅሁፍ፣ እና የአመራር ክህሎቶችን ለማሳደግ እድል ይሰጣል። ለመሣተፍ የጽሑፍ ድርሰት ያስፈልጋል እና እስከ ማክሰኞ፣ ማርች 31 ድረስ መቅረብ አለበት።

Sustainability Poster Contest፦ ሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች የኢነርጂ ቁጠባን፣ የቆሻሻ ቅነሳን እና ኃላፊነት የተሞላበት መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን ግንዛቤ ለማሳደግ በዚህ አመታዊ ውድድር ላይ መሳተፍ ይችላሉ። አዲሱን የዲጂታል አርት ይመልከቱ! የመጨረሻው ቀን ዓርብ፣ ኤፕሪል 3 ነው።

በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

  • ለፔይንት ብራንች ት/ቤት የማነቃቂያ እና ተነሳሽነት ድጋፍ፦ DARCARS አውቶሞቲቭ ግሩፕ ባለፈው ሳምንት ተማሪዎችን የጎበኘ ሲሆን $3,000 ዶላር ቼክ እና 500 የጀርባ ቦርሳዎችን ጋር ከጠንካራ የስራ እና የታማኝነት መልእክት ጋር አስተላልፏል።

  • ከ 40ዎቹ አንዷ፡ በፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት አሊሳ ዩ፣ በአገሪቱ ውስጥ ካሉት እጅግ ጥብቅ የሳይንስ እና የሂሳብ ውድድሮች አንዱ በሆነው የ 2026 የሬጄኔሮ ሳይንስ ታለንት ላይ ከተመዘገቡት 40 የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች አንዷ በመሆን ተመርጣለች።

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2026 Montgomery County Public Schools