MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ፌብሩዋሪ 26, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  የቅድመ-መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት የመኸር (ፎል) ምዝገባ አሁን ክፍት ነው

2026–2027 የትምህርት አመት የቅድመ-መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት ምዝገባ በኦንላይን ክፍት ነው። እስከ ሴፕቴምበር 1, 2026 ድረስ 3 ወይም 4 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ልጆች አነስተኛ የገቢ መጠን ያላቸው ቤተሰቦች ከሆኑ ነፃ የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት ትምህርት ይሰጣል።

ወላጆች በማርች ወር በኦንላይን ወይም በማህበረሰብ ማዕከሎች በአካል ተገኝተው ማመልከት ይችላሉ ቤተሰቦች ሮክቪል የሚገኘውን የቅድመ-መዋዕለ ሕፃናት/የሄድ ስታርት ቢሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 9 a.m.-4 p.m. መጎብኘት ይችላሉ። አድራሻ፦ 4910 Macon Road in Rockville

በሕዝብ እና በግል ማዕከሎች ስለሚገኙት ነፃ ፕሮግራሞች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ MCPS የቅድመ-ኪንደርጋርተን/የሄድ ስታርት ድረ ገጽ ይጎብኙ ወይም 240-740-4530 ይደውሉ።

 
  አሁኑኑ እርምጃ ይውሰዱ - ዛሬውኑ በመዋዕለ ሕፃናት ያስመዝግቡ

2026-2027 የትምህርት አመት፣ የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ParentVUE ፖርታል ላይ በኦንላይን ይካሄዳል። ሴፕቴምበር 1, 2026 ድረስ 5 ዓመት የሚሞላቸው ልጆች ብቁ ናቸው። ቤተሰብዎ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ ከሆኑ፣ እዚህ PreentVue አካውንት መክፈት ያስፈልግዎታል። አካውንት ከከፈቱ በኋላ፣ መጀመሪያ ሲከፍቱት ማስመዝገብ ይችላሉ። እንዳይዘገዩ፤ ዛሬውኑ ያስመዝግቡ! የምዝገባ ክፍለ ጊዜዎች ከሰኞ፣ ማርች 16 ጀምሮ በአካል ይካሄዳሉ።

 
  ስለ ት/ቤቶች ክልል ጥናቶች የታቀዱ የቦርድ የሥራ ክፍለ ጊዜዎች

የትምህርት ቦርድ የቻርለስ W. ውድዋርድን እንደገና ለመክፈት ተሻሽሎ የቀረበውን አማራጭ B ስሪት እና የቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ማርች መጀመሪያ እና አጋማሽ ላይ ወደ ክራውን ፋርም ለማዛወር ተሻሽሎ የቀረበውን አማራጭ H ስሪት ላይ ለመነጋገር የስራ ክፍለ ጊዜዎችን እያካሄደ ነው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።

ቀደም ሲል የተካሄዱ የህዝብ ውይይቶችን ይመልከቱ፡

 
  ለማሽከርከር ዝግጁ ነዎት? ማርች 17 በአውቶቡስ አሽከርካሪዎች የሥራ አውደርዕይ ላይ ቡድኑን ይቀላቀሉ

MCPS ማክሰኞ፣ ማርች 17 ከጠዋቱ 10:30 a.m.-12:30 p.m. ለአውቶቡስ አሽከርካሪዎች የሥራ አውደርዕይ ያኖራል። የሥራ አውደርዕይ የሚካሄደው ሮክቪል በሚገኘው የትራንስፖርት አገልግሎት ዲቪዥን በሚከተለው አድራሻ ነው፦ Division of Transportation Services, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville.

የአውቶቡስ ሹፌር ለመሆን መሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች፦

  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲፕሎማ ወይም GED።

  • እድሜ ቢያንስ 21 ዓመት።

  • ንጹህ (በጥፋተኝነት ያልተመዘገበ) የመኪና ማሽከርከር ታሪክ፣ በመንጃ ፈቃድ ላይ ከአንድ ነጥብ በላይ የሌለው/የሌላት።

  • ቢያንስ የሶስት አመት የመኪና መንዳት ልምድ እና U.S. ውስጥ ቢያንስ አንድ አመት የመኪና መንዳት ልምድ ያለው/ያላት

  • ሁሉንም የቅድመ-አገልግሎት ስልጠና እና የፈተና መስፈርቶችን ማሟላት የሚችል/የምትችል።

ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች MCPS Careers portal ላይ አስፈላጊ መረጃ የሚሰጥ መገለጫ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ 240-740-6080 ይደውሉ ወይም ኢሜይል ይላኩ።

 
  የማሰላሰልና እውቅና የሚሰጥበት ወር

MCPS የጥቁሮችን ታሪክ ወር እያከበረ ሲሆን፣ የትምህርት ቦርዱ ይህንንየወደፊቱ መሪ የተሰኘ ቪዲዮ አቅርቧል፣ ሞኒክ አሽተን/Monique Ashton፣ የሮክቪል ከንቲባ ሆነው ያገለገሉ የመጀመሪያዋ ጥቁርና ላቲኖ ሴት። በዚህ ልዩ ዝግጅት፣ አሽተን ስለ አመራር፣ ስለ ውክልና እና ለሌሎች በሮችን ስለመክፈት ኃላፊነት ያንፀባርቃሉ። በድፍረትና በዓላማ መምራት ምን ማለት እንደሆነ ይገልጻሉ።

እና፣ በኦዴሳ ሻነን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፓራኢጁኬተር የሆነችውን ናታሊ ጄኒፈርን/Natlie Jenifer ያግኙ፣ ቁርጠኝነቷ የተመሠረተው ከጠንካራ ቤተሰብ የወረሰችው እና እያንዳንዱ ተማሪ “aha” ጊዜውን በአግባብ እንዲጠቀም ለመርዳት የምትሰራ ናት። 

 
  የወደፊት ዝግጁነት እዚህ ይጀምራል፡ የሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት ወር

ፌብሩዋሪ የሥራ እና የቴክኒክ ትምህርት (CTE) ወር ሲሆን፣ የዘንድሮውን ጭብጥ በማጉላት፣ ስለ ወደፊት ዝግጁነት እዚህ ይጀምራል፡ ቀጣዩስ ነገር ምንድነው CTE በወሩ ውስጥ፣ ተማሪዎች የሙያ መንገዶችን እየዳሰሱ ቃኝተዋል፣ እና ለወደፊታቸው የሚያስፈልጋቸውን እውቀት እና ክህሎቶች በመገንባት የትምህርት ልምዶች ላይ ተሳትፈዋል። MCPS CTE ፕሮግራሞች ተማሪዎች በኢንዱስትሪዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው የምስክር ወረቀቶችን በማግኘት እና በነባራዊው ዓለም የትምህርትና የዕውቀት ልምዶች ላይ በመሳተፍ ስለ ችግር አፈታት፣ በትብብር መሥራት እና የዲጂታል ሊተርሲ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ይረዷቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  ማሳሰቢያ
  • የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ሰኞ፣ ማርች 9 ይጀመራል። ስለ ምዝገባ መረጃ ለማግኘት፣ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ካውንስለር ማነጋገር አለባቸው። ስለ መርሃ ግብሮቹ እና ክፍያዎችን በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ያንብቡ። 

  • ጊዜያዊ/ኢንትሪምስ ማርች 6 ይካሄዳል፡ ወደ ሦስተኛው የማርክ መስጫ ጊዜ አጋማሽ ጫፍ እየተቃረብን ነው። የቅርብ ጊዜ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በማርክ መስጫው የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ባሉት የትምህርት ቀናት ብዛት ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል። በዚህም ምክንያት፣ መምህራን ለማስተማር ወደ ክፍል የሚገቡበት የጊዜ ገደብ እስከ ማክሰኞ፣ማርች 3 እንዲሆን ተስተካክሏል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

  • SAT የትምህርት ቀን፡ MCPS ረቡዕ፣ ማርች 11 በትምህርት ቤት ዓመታዊ SAT ፈተና ያካሂዳል። ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪዎች (2023-2024 የትምህርት አመት ለመጀመሪያ ጊዜ 9ኛ ክፍል የገቡ ተማሪዎች) በዚህ ቀን SAT ፈተና መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። MCPS ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተማሪዎችን ወጪ ይሸፍናል። 

  • የሕዝብ ትምህርት አገልግሎት ሽልማቶች፦ የትምህርት ቦርድ ዓመታዊ ሽልማት የመጨረሻ ቀን ሰኞ፣ ማርች 9 ነው።

  • ያገለገሉ መኪኖችን እና ኮምፒውተሮችን ይግዙ፦ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 28 ከጠዋቱ 9-11 a.m. በደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሽያጭ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Damascus High School, 25921 Ridge Road in Damascus.

 
  ስለ 2026-2027 የት/ቤቶች የቀን መቁጠሪያ/ካላንደር አሁን ማወቅ ያለብዎት፦

ለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት የእቅድ ዝግጅት ለመጀመር በጣም አልፈጠነም/አልቸኮልንም። የትምህርት ቦርድ በቅርቡ የትምህርት አመት 2026–2027 ኦፊሴላዊ የቀን መቁጠሪያ ማጽደቁ ይታወቃል። የተማሪዎች የሽግግር ቀን ሰኞ፣ ኦገስት 24 ይካሄዳል፣ የትምህርት አመቱም ከማክሰኞ፣ ኦገስት 25 እስከ ጁን 16 ድረስ ይቀጥላል። 

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

 
  ትኩረት የሚስቡ ነገሮች፣ ዘፈኖች እና የትዕይንቶችን ፡ በአቅራቢያዎ የሚካሄዱ የመዝናኛ ትርኢቶችን ይቃኙ!

ቀጥታ ቲያትር ማየት ዳግም ተመልሷል! ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙዚቃ እና አሊስ ኢን ዎንደርላንድ እስከ ፍሮዝን፣ አኒ፣ ጁንየር እና ሌሎችም፣ በአቅራቢያዎ የሚገኙ ትርኢቶችን ለማግኘት Fine Arts calendar ወይም የትምህርት ቤትዎን ድረ ገጽ ይመልከቱ። 

እንዲሁም፣ በዚህ አመት አዲስ የሚቀርብ፣ ማርች እና ኤፕሪል ወር ላይ የሚመጣ፣ የሁሉም ካውንቲ የማህበረሰብ የስነጥበብ ትርኢቶቻችን እንዳያመልጥዎት — በአንድ ጂኦግራፊያዊ አካባቢ የሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስራቸውን አብረው እንዲያሳዩ ያስችላቸዋል፣ ይህም ወጣት አርቲስቶች MCPS የስነጥበብ ትምህርታቸውን ሲቀጥሉ የወደፊት ህይወታቸው ምን ሊመስል እንደሚችል እንዲገነዘቡ የሚያስችላቸውን ድባብ ይፈጥራል። 

ምናልባት ካመለጠዎት፣ ከስምንት የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎችን የዳንስ ትርኢት የሚያሳየውን አመታዊውን የዳንስ ትርኢት ፎቶዎች ይመልከቱ። 

 
  በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
 
  ከበረዶ ቀናት በኋላ የተደረጉ 2025–2026 የትምህርት ቀን መቁጠሪያ/ካላንደር ለውጦች

የትምህርት ቦርድ ፌብሩዋሪ 19 ባካሄደው የሥራ ስብሰባ ላይ 2025–2026 የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ/ካላንደር ላይ ቴክኒካዊ ለውጦችን/ማሻሻያዎችን አጽድቋል። የትምህርት ቤቶች የመጨረሻ የትምህርት ቀን አርብ፣ ጁን 26 ይሆናል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።

 

ስለ ትምህርት በጀት የውይይት መድረኮች ማርች 4 እና 11 ይካሄዳሉ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል ዊል ጃዋንዶ ሁለት አዳዲስ የትምህርት በጀት መድረኮችን ያካሄዳሉ። MCPS ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር እና የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጄርሜይን ዊሊያምስ ጭምር ይሳተፋሉ። መድረኮቹ የሚካሄዱት፦

  • ረቡዕ፣ ማርች 4፣ከቀኑ 6:30 p.m., በሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

  • ረቡዕ፣ ማርች 11፣ ከቀኑ 6:30 p.m., በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
    ይመዝገቡ/RSVP
    ስለ ዝግጅቱ አጭር የመግለጫ ጽሑፍ

 

ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች

  • ስልክ ያቁሙ፣ ትኩረት ይስጡ፦ በሚል ርዕስ የእግረኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ትምህርት ሰጪ የሆነ 30 ሰከንድ ቪዲዮ ያዘጋጁ። በእግር ስትጓዙ፣ መኪና፣ ወይም ብስክሌት ስትነዱ በስልክዎ ላይ ሳይሆን በአካባቢዎ ዙሪያ ላይ ማተኮር አስፈላጊመሆኑን ይገንዝቡ። በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። Macbook Air ወይም በመቶዎች የሚቆጠሩ የስጦታ ቪዛ ካርድ ማሸነፍ ይችላሉ። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 28ነው።

  • «ከንቲባ ብሆን ኖሮ»/If I Were Mayor” የድርሰት ውድድር፡ የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች በሜሪላንድ ሙኒሲፓል ሊግ በሚካሄደው “ከንቲባ ብሆን ኖሮ…” የተሰኘ የድርሰት ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። የመጨረሻው ቀን፦ ሐሙስ፣ ማርች 5 ነው።

  • Latina Legacy Conference፡- ለላቲኖ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሴት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ይህ ኮንፈረንስ ቅዳሜ፣ ማርች 7 በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register

  • የማት ፓፒርሜስተር ሽልማት/The Matt Papirmeister Award፡ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኪነጥበብ/አርት ተማሪዎች ክፍት ነው። የገንዘብ ሽልማት፡ $3,500 ዶላር፣ $3,000 ዶላር እና $2,500 ዶላር ተዘጋጅቷል። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን እሑድ፣ ማርች 15 ነው።

  • BWI አየር ማረፊያ የወጣቶች የስነጥበብ ጋለሪ፡- ከሜሪላንድ የስነጥበብ ትምህርት ማህበር ጋር በመተባበር፣ አየር ማረፊያው በዚህ የጸደይ/ስፕሪንግ ወቅት ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) የስነጥበብ ትርኢት ያስተናግዳል። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን እሑድ፣ ማርች 1 ነው።

  • አስተማማኝ የቪዲዮ ውድድር "Keeping It Safe Video Contest"፡ ውድድሩ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ከ 21 ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ተማሪዎች የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች እና አስከፊ ጉዳቶች 30 ሰከንድ ቪዲዮ ፈጥረው/አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።

  • Sober Vibes Essay Contest: የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ሲንየሮች ከፕሮም በፊት፣ በፕሮም ወቅት፣ ወይም ከዚያ በኋላ መጠጥ እንዳይጠጡ አሳማኝ የመወዳደሪያ ድርሰት እንዲጽፉ ይበረታታሉ። ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።

  • የሜሪላንድ የትምህርት ቤቶች ደህንነት ማዕከል 2026 የስነጥበብ ትርኢት ያዘጋጃል፡ የዘንድሮው ጭብጥ፣ ለወደፊት ዝግጁ የሆኑ ትምህርት ቤቶች፣ 3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ደህንነት ለእነሱ ምን ማለት እንደሆነ ያላቸውን አመለካከት እንዲያጋሩ ጥሪ ያቀርባል። የመጨረሻ ቀን፡ እሑድ፣ ሜይ 31 ነው።  

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2025 Montgomery County Public Schools