አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ኦገስት 21, 2026

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ኦገስት 20 ባካሄደው ስብሰባ ላይ ለትምህርት ቤት የገንዘብ ድጋፍ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች፣ በሜሪላንድ የወደፊት እቅድ ውስጥ እንዲካተቱ፣ ስለ ትምህርት ቤት ግንባታ፣ ስለ አስተማሪዎች ቅጥር እና በሥራ ላይ እንዲቆዩ ማስቻል፣ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ የመማሪያ አካባቢዎችን ለመጠበቅ ስለሚያስፈልጉ ሁኔታዎች በመዘርዘር 2027 ዓ.ም ወደ ሥራ አስፈጻሚ እንዲቀርብ ወስኗል። ቦርዱ በአሁኑ ወቅት ባለው SMOB የቀረበውን ስለ 50ኛው ተማሪ የቦርድ አባል ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ አጽድቋል። ቦርዱ ለመጀመሪያው የትምህርት ቀን ዝግጅት፣ የዲስትሪክቱን 211 የትምህርት ተቋማት፣ $3 ቢሊዮን ዶላር የጥገና ባጀት ጉድለት እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ጥገናን ለማጠናከር የተደረጉ ጥረቶችን በማንፀባረቅ ስለ MCPS መገልገያዎች እና ጥገና ወቅታዊ መረጃ አግኝቷል።

በዚህ መኸር/ፎል ወቅት 2026 የሠመር ተመራቂዎችን እና የትምሕርት ጉዟቸውን ለመጀመር ወደ MCPS አዲስ የሚገቡ የመዋእለ ህጻናት ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው አስፈላጊ የሆኑ ወሳኝ ክንውኖች ተደርገዋል።

ሕግ የማስፈፀም መድረክ | ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) የምርጫ ጊዜ ሠሌዳ | MCPS መገልገያዎች እና ጥገና | የሚካሄዱ ሥነ ስርአቶች | አስፈላጊ ቀናት |


በትምህርት አመት 2027 ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሕጋዊ ተግባራት

ቦርዱ በትምሕርት አመት 2027 ቅድሚያ በመስጠት ለሕጋዊ የውሳኔ ሰጭ አካል የሚቀርቡ ጉዳዮችን አጽድቋል፣ ለመጪው የሜሪላንድ የሕግ አውጪ ክፍለ ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እና ግቦቹን በመንደፍ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች በማቀንቀን ረገድ ያለውን ሚና አረጋግጧል።

መድረኩ በቂ እና ፍትሃዊ የትምህርት ቤት ባጀት፣ ስለ ሜሪላንድ የወደፊት ትልም/Blueprint ፣ ስለ ትምህርት ቤት ግንባታ እና የካፒታል ገንዘብ ድጋፍ፣ የአካባቢ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነትን ስለመጠበቅና ማክበር፣ ስለ አስተማሪዎች ቅጥር እና በሥራቸው ላይ መቆየት የሚያስችላቸውን ሁኔታ ማመቻቸት እና ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የመማሪያ አካባቢዎችን መጠበቅ ላይ ያተኩራል። ቦርዱ ከልዩ ትምህርት ፋይናንስ፣ የላቀ ትምሕርት ደረጃ ምደባ (AP)፣ እና ዓለም አቀፍ የባካሎሬት (IB) የፈተና ወጪዎች፣ ስለ አካባቢ የሰው ኃይል ሙያዊ እድገት የቦርድ ትብብር መስፈርቶች፣ የቅድመ-መዋእለ ህጻናት ፓራፕሮፌሽናል ሙያ ነክ ሠነዶች፣ እና የትብብር ፋይናንስ ጋር የተያያዙ የተወሰኑ ሕጋዊ ለውጦችን ተመልክቷል።

በማጠቃለያም፣ መድረኩ በትምህርት ቤት ግንባታ ላይ እምቅ ለመማር የተገነባ 2.0 ፕሮግራም እና ታሪካዊ የትምህርት ቤት ሕንፃዎችን በደንብ አሳድሶ ለመጠበቅ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲመደብ ይጠይቃል።

2027 ለውሳኔ ሰጪ አካል መየቀረበውን ይመልከቱ


50ኛው ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) ምርጫ ለማድረግ የተዘጋጀ የጊዜ ሠሌዳ

በዲስትሪክቱ አስተዳደር ውስጥ የተማሪዎች ድምጽ እንደ ዋና አስፈላጊ አካል ይቀጥላል። የቦርዱ 49ኛ ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) ልዑል ዳዊት ባቀረቡት ሀሳብ መሰረት፣ ቦርዱ የሚቀጥለው የተማሪዎች ተወካይ የሚመረጥበትን የጊዜ ሰሌዳ በይፋ አጽድቋል፦

  • ጃኑዋሪ 4–28, 2027 እጩዎች የመወዳደር ፍላጎታቸውን የሚያቀርቡበት ጊዜ
  • ፌብሩዋሪ 10, 2027 ተወዳዳሪ እጩዎች የሚለዩበት ጊዜ
  • ፌብሩዋሪ 11 እስከ ኤፕሪል 27, 2027 ኦፊሴላዊ የምረጡኝ ዘመቻ ጊዜ
  • ኤፕሪል 27–28, 2027፡ አጠቃላይ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ

ይህ ምርጫ MCPS ከሜሪላንድ የተማሪዎች ምክር ቤት ማህበር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሪጅን ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ በዲስትሪክቱ ውስጥ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች 50ኛውን ተማሪ የትምሕርት ቦርድ አባል (SMOB) በቀጥታ እንዲመርጡ ያስችላቸዋል።

ተማሪ መሪዎች ፖሊሲን እንዴት እንደሚቀርጹ ለማወቅ፣ MCPS የተማሪ አመራር ገጽ ይጎብኙ።


ቦርዱ ስለ MCPS መገልገያዎችና ጥገና ወቅታዊ መረጃ አግኝቷል

211 አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ተቋማትን ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ምቹ የመማሪያ አካባቢዎች አድርጎ መጠበቅ ቀላል ስራ አይደለም። MCPS 26.5 ሚሊዮን ካሬ ጫማ የመማሪያ ቦታን እንዴት እንደሚያስተዳድር በዝርዝር በመግለጽ የዲስትሪክቱ አመራሮች የትምህርት አመት 2027 አጠቃላይ የጥገና እና ኦፕሬሽን እቅድ አቅርበዋል።

የትምህርት ቤት ሕንፃ አማካይ እድሜ አሁን 30.1 ዓመት ሲሆን፣ ዲስትሪክቱ ወደ $3 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የዘገየ የጥገና ውዝግብ እያመለከተ ሲሆን የካፒታል ግንባታ መተካትን በመደበኛነት ለማስኬድ በዓመት በግምት $560 ሚሊዮን ዶላር ይፈልጋል።

ስለ ጥገና አስፈላጊነት ከሪፖርት የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፡

  • 76,000+ የሥራ ትዕዛዞች፡2026 የበጀት ዓመት ላይ ብቻ አጠቃላይ የጥገና ጥያቄዎች ቀርበዋል።
  • በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ማሻሻያዎች፡ ለተሻሻለ ክትትል እና ለሕዝብ ተደራሽነት አዲስ የኮምፒዩተር የስራ ትዕዛዝ አስተዳደር ስርዓትን ከተበላሸ በኋላ ለመጠገን ከመጠበቅ ይልቅ አስቀድሞ አስፈላጊነቱን በመመርመር ተገቢ ጥገና ወደማድረግ መሻገር ያስፈልጋል።
  • የረጅም ጊዜ ስልቶች/ስትራቴጂዎች፡ የተማሪዎችን የሥራ ልምምድ እድሎች ማስፋት፣ የሠመር ወቅት ካፒታል ማሻሻያዎችን መተግበር፣ እና ያረጁ ህንፃዎች ውስጥ ኃይል ቆጣቢ ሥርአት መዘርጋት።

ስለ ትምሕርት ቤቶች ሕንጻዎች እና ስለ ጥገና ኦገስት 20 የተካሄደ ውይይት ይመልከቱ


ሥነ ሥርዓቶች እና የተሰጡ እውቅናዎች

የትምህርት አመት 2026 የሠመር ተመራቂዎች

የትምሕርት ዓመት 2026 የሠመር ተመራቂዎች

ኦገስት 12, 2026፣ ከመላው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የተውጣጡ የትምሕርት አመት 2026 ተመራቂ ተማሪዎች ወደሚመረቁበት መድረክ ተጉዘዋል። ተመራቂዎች ዲፕሎማቸውን ተቀብለው ከቦርድ አባል ካርላ ሲልቬስትሬ እና ከሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴይለር ጋር ተጨባብጠዋል፣ ከቤተሰብ እና ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ይህንን ታላቅ ምዕራፍ አክብረዋል።

የሠመር የምረቃ ዘገባዎችን ኢንስታግራም ላይ ይመልከቱ

የቦርድ አባል ሲልቬስትሬ/Board Member Silvestre ከ 90 ዎቹ ጠንካራ ተመራቂዎች መካከል ሦስቱን አጉልተው ገልጸዋል፤ እነሱም ካይደን ጋሪ (ከዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)፣ ኬይሪ ዲያዝ (ከሼርዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) እና ካሲ ሊን ካርተር (ከሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) ናቸው። በቁርጠኝነታቸው ልንኮራባቸው ይገባል፤ በዓለም ላይ ሁሉንም ዓይነት ስኬትና መልካም ዕድል እንመኝላቸዋለን! ለ 2026 ተመራቂዎች፣ እንኳን ደስ አላችሁ!

ዶ/ር ላኪሻ ላሽሊ እና የትምሕርት ክፍል ቡድን እንዲሁም የፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ዶ/ር ሻዋን ቲ. ሮቢንሰን ተመራቂዎቻችንን በደስታ ስለተቀበሉ እና የትምሕርት አመት 2026 የሠመር ምረቃ ሥነ ሥርዓትን ስላስተናገዱ ልዩ ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

ለመዋዕለ ሕፃናት ተዘጋጁ

ለመዋዕለ ሕፃናት ተዘጋጁ

የቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን የወደፊት የመዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎቻችን የመጀመሪያውን የትምህርት ዓመት በጠንካራ ሁኔታ ለመጀመር ሲዘጋጁ እውቅና ሰጥተዋል። በዚህ መኸር/ፎል ከ 9,000 በላይ የመዋለ ህጻናት ተማሪዎች ወደ MCPS እንደሚገቡ ይጠበቃል፣ ፕሬዝዳንት ሪቬራ-ኦቨን ወደ ትዊንብሩክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚመጡ ተማሪዎች፣ ከርዕሰ መምህር ሞኒካ ኬልነር እና ከትምህርት ቤቱ ሰራተኞች ጋር ልዩ ምስጋና አቅርበዋል።

ቦርዱ እነዚህ አዳዲስ የመዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች ሲያድጉ ለማየት ይጓጓል፣ እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ MCPS ት/ቤቶች ሲገቡ በስኬት፣ በብቃት እና በደስታ የተሞላ ጉዞ እንዲኖራቸው እንመኛለን!

Cubs RAWR አድምጡ


MCPS አስፈላጊ ቀናት፦

ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢቶች፦ በዚህ ቅዳሜ፣ ኦገስት 22 የትምህርት አመት 2026–2027 ለማስጀመር በተዘጋጁት ስድስት የሪጅናል ትርኢቶቻችን በአንዱ እንገናኛለን። ቤተሰቦች ስለ ትራንስፖርት፣ ስለ ቴክኖሎጂ፣ ስለ ልዩ ትምህርት፣ ስለ ብዝሃ ቋንቋ አገልግሎቶች፣ ስለ አእምሮ ጤና እና ሌሎች ማዕከላዊ ቢሮዎች ላይ የሚገኙ እውቀት ያላቸውን MCPS ሰራተኞችን በቀጥታ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ድጋፍ ሊሰጧቸው ይችላሉ! ትምህርት ቤትዎን እና በአቅራቢያዎ ወደ ት/ቤት የመመለሻ ትርኢት የሚካሄድበትን ቦታ ያግኙ፦

  • አልበርት አንስታይን፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (አልበርት አንስታይን፣ ቤቴስዳ-ቼቪ ቼዝ፣ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ ኖርዝዉድ፣ ዋልት ዊትማን ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
  • ፔይንት ብራንች፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (ጄምስ ሁበርት ብሌክ፣ ፔይንት ብራንች፣ ሼርውድ፣ ስፕሪንግብሩክ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
  • ዊተን፣ ከቀኑ 3–6 p.m. (ጆን ኤፍ. ኬኔዲ፣ ዋልተር ጆንሰን፣ ዊተን/ቶማስ ኤዲሰን፣ ቻርለስ W. ውድዋርድ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
  • ሪቻርድ ሞንትጎመሪ፣ ከቀኑ 1–4 p.m. (ዊንስተን ቸርችል፣ ሪቻርድ ሞንትጎመሪ፣ ሮክቪል፣ ቶማስ S. ውተን ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
  • ጌትስበርግ፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (ጌትስበርግ፣ ኮሎኔል (ዛዶክ ማግሩደር፣ ኩዊንስ ኦርቻርድ፣ ዋትኪንስ ሚል ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
  • ሴኔካ ቫሊ፣ ከቀኑ 3–6 p.m. (ክላርክስበርግ፣ ደማስከስ፣ ኖርዝዌስት፣ ፑልስቪል፣ ሴኔካ ቫሊ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)

ነፃ ክትባቶች በፔይንት ብራንች፣ ጌትስበርግ፣ እና ሴኔካ ቫሊ ት/ቤቶች ይሰጣሉ። ወላጆች/አሳዳጊዎች ልጃቸው ክትባት ለመውሰድ ብቁ ለመሆን ወቅታዊ የክትባት ማስረጃ ቅጂ ይዘው መምጣት አለባቸው። ቤተሰቦች ስለ ነፃ የክትባት ግብዓቶች እና ቦታዎችን ለማወቅ በአልበርት አንስታይን፣ በዊተን፣ እና በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ት/ቤቶች የመረጃ ጠረጴዛዎች ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የሽግግር ቀን፦ ሰኞ፣ ኦገስት 24 ሁለተኛው አመታዊ የሽግግር ቀናችን ነው! ወደ መዋእለ ህጻናት፣ 6ኛ ክፍል፣ 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች፣ እንዲሁም በማንኛውም ክፍል ወደ MCPS አዲስ ለሚገቡ አንዳንድ የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያው ሙሉ ቀን ይሆናል። ከርዕሰ መምህራንና ከመምህራን ጋር ይገናኛሉ፣ የትምህርት ቤታችሁን ሕንፃዎች ይጎበኛሉ፣ ልምምዶችን ይጋራሉ፣ ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ይገናኛሉ፤ እና ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 የትምህርት ቤቶች ይፋዊ የመጀመሪያ ቀን ከመጀመሩ በፊት የማህበረሰብ ስሜት ማዳበር ይችላሉ። ስለ ሽግግር ቀን የበለጠ ይወቁ፡ እንግሊዝኛ | ስፓኒሽ

ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 ለሁሉም ተማሪዎች በሁሉም ክፍሎች የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀን ነው። እንኳን ደህና መጣችሁ!

ከመጀመሪያው ደወል እስከ መጨረሻው ደወል ድረስ ለተማሪዎች ክፍል ውስጥ ሞባይል ስልክ መጠቀም አይፈቀድም፦ MCPS ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ለትምሕርታቸው ትኩረት እንዲሰጡ እና እርስ በርስ እንዲገናኙ የሚያግዝ አዲስ የሞባይል ስልክ ደንብ ተግባራዊ እያደረገ ነው። የግል ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በሙሉ በትምህርት ቀን ውስጥ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች— ከመጀመሪያው ደወል ጀምሮ ተማሪዎች እስከሚለቀቁበት የመጨረሻ ደወል ድረስ - በተማሪዎች እጅ እንዳይቀመጡ ይደረጋል። ይህ የትምህርት ሥራ መስተጓጎሎችን ይቀንሳል፣ ተማሪዎች በመማር ላይ በትኩረት እንዲሳተፉ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ያግዛል ተብሎ ይታመናል።

ለቤተሰብ ተስማሚ የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር፦ ለትምሕርት አመት 2026-2027 አዲስ የተዘጋጀ፣ይህ የቀን መቁጠሪያ ከመደበኛው የቀን መቁጠሪያ ይልቅ ቀላል እና ተደራሽ በሆነ ቅርጸት ተተክቷል። ተማሪዎች ትምህርት ቤት ሲሆኑ፣ ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን ሲኖራቸው፣ እንዲሁም የክረምት/ዊንተር እና የጸደይ/ስፕሪንግ ዕረፍት ሲኖራቸው፣ ቤተሰቦች አስቀድመው እንዲያቅዱ እና የማየት ችግር ላለባቸው ተጠቃሚዎች ሁሉ ማንበብ እንዳይቸግራቸው ለመርዳት ቀላል ተደርጓል።


ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ሰኞ፣ ኦገስት 31፣ ልዩ የማህበረሰብ ኮሚቴ (10:00 a.m.)
  • ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 1፣ የስትራቴጂክ እቅድ ኮሚቴ (10:00 a.m.)
  • ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 8፣ የፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ስብሰባ (ከሰዓት በኋላ 3፡00 p.m.)
  • ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 10፣ የቦርድ የሥራ ክፍለ ጊዜ (12:00 p.m.)

ቦርዱ በ MCPS የኬብል ቻናሎች እና YouTube ላይ ሁሉንም ወርሃዊ የቦርድ ሥራ ስብሰባዎች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች የስፓንሽኛ ትርጉም ይቀርባል። በተጨማሪም፣ በአካል የተገኙ ተሳታፊዎች ለማንኛውም ስብሰባ የትርጉም አገልግሎቶችን መጠየቅ ይችላሉ። ጥያቄዎች ከስብሰባው ቢያንስ 10 ቀናት ቀደም ብለው መቅረብ አለባቸው። ስብሰባዎቻችንን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እና ማህበረሰባችን እንዲገናኝ ለማድረግ በጉጉት እንጠብቃለን!


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች ላይ አስተያየት በመስጠት ይሳተፉ። 

FacebookInstagramBluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org