አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ሴፕተምበር 25, 2026

የቦርድ ስብሰባ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ (ቦርዱ)፣ ሴፕቴምበር 24 በተካሄደው የስራ ስብሰባ ላይ፤ ስለ ተማሪዎች ደህንነት፣ ስለ ይግባኝ እና ችሎቶች አፈጻጸም፣ እንዲሁም በትምህርት ቤት የሚዘጋጁ የጉዞ እንቅስቃሴዎችን በሚመለከቱ ሶስት የቦርድ ፖሊሲዎች ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ የቀረቡ ሀሳቦች ላይ ውሳኔ አሳልፏል። በተጨማሪም ቦርዱ «በትምህርት ሣምንት ውስጥ ለብሔራዊ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች/አርትስ» እውቅና የሰጠ ሲሆን፣ ለኪነ-ጥበብ ትምህርት አስተዋጽኦ ላበረከቱት የጄምስ ሁበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ መምህራን እና አስተዳዳሪዎች አድናቆትና እውቅና ሰጥቷቸዋል።

ፖሊሲ JPG: ስለ ደህንነት | ፖሊሲ BLB: ስለ ይግባኝ አቀራረብ እና ይግባኝ ሰሚ ችሎት | ፖሊሲ IPD: ስለ ተማሪዎች የመስክ ጉዞ | በትምሕርት ሣምንት ስለ ብሔራዊ ስነጥበብ/አርትስ


በተማሪዎች ደህንነት ፖሊሲ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች

ቦርዱ ፖሊሲ JPG – ደህንነት፡ አካላዊ እና የአመጋገብ ጤና ላይ ቴክኒካዊ ማሻሻያዎች አድርጓል።

የፖሊሲ ማሻሻያው ከሜሪላንድ ህግ ጋር የተሣለጠ በመሆኑ፤ በዚህ ደንብ መሠረት በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች አለርጂ ለሚሆንባቸው የምግብ ንጥረ ነገሮች የመጋለጥ አደጋን ለመቀነስ የሚያስችሉ መመሪያዎችን እንዲያዘጋጁ ይጠይቃል። እነዚህ ማሻሻያዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ኃላፊነት ያለበትን ክፍልም ይመለከታሉ።

ማሻሻያዎቹ ቴክኒካዊ ይዘት ያላቸው በመሆናቸው፣ ቦርዱ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት አላደረገም።

ፖሊሲ JPG ማሻሻያዎችን ያንብቡ


የይግባኝ አሰራር ቀልጣፋ ተደራሽነት እንዲኖር ማድረግ

ቦርዱ ፖሊሲ BLB (ይግባኝ እና ይግባኝ ሰሚ ችሎት አሠራር ደንብ) ላይ በቀረቡት የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ሀሳቦቹ ለህዝብ አስተያየት እንዲቀርቡ የመጀመሪያ ደረጃ ውሳኔ አሳልፏል።

የቀረቡት ማሻሻያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የይግባኝ ጥያቄዎችን ቴክኒካዊ መስፈርቶች ከአሁኑ አሰራር ጋር ማጣጣም።

  • በይግባኝ ሂደት ውስጥ ለሚሳተፉ ግለሰቦች ይበልጥ ግልጽ የሆነ መመሪያ መስጠት።

  • የይግባኝ አቤቱታዎች በብቃት እና በወቅቱ እንዲስተናገዱ መደገፍ።

  • ከእንግሊዝኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ መናገር በይግባኝ አሰራር ሂደት ለመሳተፍ እንቅፋት መሆን እንደሌለበት ግልጽ ማድረግ።

ቦርዱ የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት፣ በታቀዱት የፖሊሲ ለውጦች ላይ የህዝብ አስተያየቶችን ይቀበላል።

የቀረቡትን BLB ፖሊሲ ማሻሻያዎች ያንብቡ 


ከክፍል ውጭ የመስክ ጉዞዎች እና የተማሪዎችን ጉዞ በሚመለከት የቀረቡ ማሻሻያዎች

ቦርዱ "ፖሊሲ IPD – የጥናት ጉዞ ፕሮግራሞች፣ የመስክ ጉብኝቶች እና የተማሪዎች ድርጅት ጉዞዎች" ፖሊሲ ላይ በቀረቡት የማሻሻያ ሀሳቦች ዙሪያ የመጀመሪያ ደረጃ እርምጃ የወሰደ ሲሆን፣ ፖሊሲውን ለህዝብ አስተያየት እንዲቀርብ ወስኗል።

የቀረቡት ማሻሻያዎች፣ ፖሊሲውን ከአሁኑ MCPS አሰራሮች ጋር ለማሣለጥ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች በሚዘጋጁ ጉዞዎች ላይ የሚጠበቁ ነገሮችን ለማብራራት የሚያግዝ ሲሆን እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የመስክ ትምህርታዊ ጉብኝቶችን እና የተማሪዎችን ጉዞ ከመማር-ማስተማር ሂደቱ ጋር በግልጽ ማገናኘት።

  • ስለ ዓለም አቀፍ ጉዞ ይበልጥ ግልጽ የሆነ መመሪያ መስጠት።

  • የጥቅም ግጭቶችን መፍታት።

  • አድልዎ ማስወገድን የሚገልጽ መግለጫ ማካተት።

ከቀረቡት ማሻሻያዎች አንዱ፣ የመስክ ጉዞዎችን እንደ ማበረታቻ የመጠቀም ልማድን የሚያስቀር ነው። የፖሊሲ ማኔጅመንት ኮሚቴው፣ በተለይም ተማሪዎችን ለማነሳሳትና ለመሸለም የሚደረጉ የማክበር ወይም የማስተዋወቅ ጉዞዎች ካላቸው ሚና አንጻር፤ የመስክ ጉዞዎች ከትምህርት ሂደት ጋር እንዲተሳሰሩ የማድረግና አደጋ የሚያስከትሉ ተግባራትን የመቀነስ ግቦችን እንዴት ማመጣጠን እንደሚቻል ከማህበረሰቡ አስተያየት እየጠየቀ ነው።

የቀረቡትን IPD ፖሊሲ ማሻሻያዎች ያንብቡ 


በትምህርት ሣምንት ውስጥ ብሔራዊ የኪነ-ጥበብ ሥራ/አርት ማክበር

ዕውቅና መስጠት

ከሴፕቴምበር 13 እስከ 19 የነበረው የትምህርት ጊዜ "ብሔራዊ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች/አርትስ ሣምንት" ሲሆን፣ ይህም በህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኪነ-ጥበብ ትምህርት ያለውን ሚና እውቅና ለመስጠት እና ለማክበር የተዘጋጀ ወቅት ነበር።

ቦርዱ ባካሄደው የስራ ስብሰባ ላይ፣ የቦርድ አባል ላውራ ስቱዋርት/Laura Stewart የጄምስ ሁበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን፣ መምህራንን እና አስተዳዳሪዎችን የኪነ-ጥበብ ትምህርትን ለማሳደግ የረዱ ማህበረሰብ መሆናቸውን በጉልህ አንፀባርቀዋል።

የብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የኪነጥበብ ትምህርት ዲስፕሊን፣ ትብብር፣ እና ሂሳዊ አስተሳሰብን እንዴት እንደሚያዳብር በማሳየታቸው እና ለተማሪዎች ራስን መግለጽ እና የመደሰት እድሎችን መስጠት በመቻላቸው እውቅና ሰጥተዋቸዋል።

የዘንድሮው ሀገር አቀፍ መሪ ቃል "እያንዳንዱ ተማሪ፣ እያንዳንዱ ማህበረሰብ"/“Every Student, Every Community” ፣ ተማሪዎችና ማህበረሰቦች በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የመሳተፍ ዕድል ማግኘታቸውን የማረጋገጥን አስፈላጊነት ያንፀባርቃል።

video


ቀጣይ ስብሰባዎች

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 8፣ የቦርድ የስራ ስብሰባ (12:00 p.m.)

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15፣ የካፒታል በጀት እና CIP የመጀመሪያ ደረጃ ገለጻ የስራ ክፍለ-ጊዜ #1 (ጠዋት 4:00 a.m.) 

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 22፣ የቦርድ የስራ ስብሰባ (4፡00 p.m.)

ቦርዱ MCPS የኬብል ቻናሎች እና YouTube ላይ ሁሉንም ወርሃዊ የቦርድ ሥራ ስብሰባዎች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች የስፓንሽኛ ትርጉም ይቀርባል። በተጨማሪም፣ በአካል የተገኙ ተሳታፊዎች ለማንኛውም ስብሰባ የትርጉም አገልግሎቶችን መጠየቅ ይችላሉ። ጥያቄዎች ከስብሰባው ቢያንስ 10 ቀናት ቀደም ብለው መቅረብ አለባቸው። ስብሰባዎቻችንን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እና ማህበረሰባችን እንዲገናኝ ለማድረግ በጉጉት እንጠብቃለን!


ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ። 

Facebook፣ Instagram፣ Bluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org