
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ (ቦርዱ) ኦክቶበር 8 በተካሄደው ስብሰባው ላይ፣ MCPS የወደፊት ሁኔታን የሚወስኑ በርካታ ጉዳዮችን ተወያይቷል፤ ከእነዚህም መካከል የተማሪዎች ቁጥር እየቀነሰ መሄድ፣ የትምህርት ቤት ወሰኖች፣ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች እና ለተማሪዎች ተደራሽ እድሎች ይገኙበታል። MCPS የአንደኛ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የመዝጋት ወይም የማዋሃድ/የማጣመር ሁኔታዎችን ለማጥናት ያቀደውን አካሄድ ያቀረበ ሲሆን፣ በዚህ ሂደት ላይ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቡ በቅርብ ወራት ውስጥ አስተያየታቸውን የሚሰጡባቸው በርካታ ዕድሎች ይዘጋጃሉ። ቦርዱ 2027–28 እና 2028–29 የትምህርት ዘመናት የተዘጋጁትን ረቂቅ ካለንደሮች የተመለከተ ሲሆን፣ በአካባቢያዊ እና በሪጅናል የትምህርት መርሃ ግብሮች ላይ ስለታቀዱ ለውጦችም ወቅታዊ መረጃዎችን አግኝቷል፤ እነዚህም አዳዲስ «ሴንተር ፕሮግራሞች» (Center Programs) እና በመላው ካውንቲው ልዩ የትምህርት መርሃ ግብሮችን የማግኘት ዕድል ማስፋፋትን ያካትታሉ። በተጨማሪም፣ ቦርዱ ስለ ቤት ውስጥ ጥቃት ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን እውቅና የሰጠ ሲሆን፣ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦች ስለሚሰጡ ድጋፎችም በጉልህ ተወያይቷል። በዚህ አምድ ላይ፣ ስለ ሴንተር ፕሮግራሞች እና የማመልከት ሂደትን በተመለከተ MCPS Around the Table የመጀመሪያ ክፍል፣ የላቲን-ሂስፓኒክ ቅርስ ወርን በምግብ፣ በባህላዊ ጨዋታ፣ እና በውይይት የሚያሣይ አዲስ EdTalk ታገኛላችሁ።
የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች የወሰን ጥናት | ረቂቅ 2027–28 & 2028–29 የትምህርት ቤት ካለንደሮች | ስለ አካባቢ የጥናት ፕሮግራሞች እና ሪጅናል ፕሮግራሞች | MCPS ሴንተር ፕሮግራሞች | EdTalk | የቤት ውስጥ ጥቃት ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር | MCPS Around the Table
በካውንቲው ውስጥ የተማሪዎች ቁጥር እየቀነሰ መሄዱ እየቀጠለ ስለሆነ፣ MCPS የአንደኛ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የመዝጋት እና የማጣመር ሁኔታዎችን እንዴት እንደሚያጠና ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀት ጀምሯል።
ማወቅ ያለብዎት ነገር እነሆ፦
ለምን አሁን? ዲስትሪክቱ የተማሪዎች ምዝገባ ሁኔታ እየቀነሰ መሄዱን፣ ሪሶርሶች/መገልገያዎች በፍትሃዊነት መከፋፈላቸውን፣ እና ትምህርት ቤቶች ለአካባቢው ማህበረሰብ ተገቢ የሆነ መጠን እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ ሲል፤ የተማሪዎች ምዝገባ ሁኔታ ላይ የሚታዩ ለውጦችን እና የትምህርት ቤት ህንጻዎችን አጠቃቀም ሁኔታ እየገመገመ ይገኛል።
MCPS የሚመለከታቸው ነገሮች ምንድናቸው? በቦርድ ፖሊሲ እና በሜሪላንድ ደንቦች የተወሰኑ ምክንያቶች፤ እነዚህም የተማሪዎች የምዝገባ ሁኔታ፣ የህንጻው ዕድሜና ሁኔታ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ጣምራ ትምህርት የሚሰጡ ት/ቤቶች እና የሕብረተሰብ/ዘር ስብጥር በጥናቱ ውስጥ ይካተታሉ፤ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተገደበ አይደለም።
የማህበረሰብ አስተያየት፦ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት አስተያየቶቻቸውን ለመስጠት በርካታ እድሎች ይኖሯቸዋል። በሁለት ዙር የማህበረሰብ ተሳትፎ እንደሚደረግ የታቀደ ሲሆን፥ በእያንዳንዱ የተሳትፎ ዙር4 የበይነመረብ አውድ/ቨርቹዋል እና 6 በአካል በመገኘትየሚካሄዱ ናቸው። የመጀመሪያው ዙር ኦክቶበር 19–ኖቨምበር 2, 2026የሚቀጥለው ዙር ኖቨምበር 30–ዲሰምበር 11, 2026ይካሄዳል።
ቀጥሎስ ምን ይደረጋል?ፌብሩዋሪ 4, 2027 ከሱፐርኢንተንደንት የሚቀርቡ ምክረ-ሀሳቦች ይጠበቃሉ። በመቀጠልም ፌብሩዋሪ፣ ማርች፣ እና ኤፕሪል ወራት የህዝብ አስተያየትና ውይይት መድረኮች ይካሄዳሉ፤ ኤፕሪል 15, 2027ቦርዱ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ እቅድ ተይዟል።
የበለጠ ማወቅ ስላለብዎት ጉዳዮች እና MCPS ሰራተኞች ለቦርዱ ያቀረቡትንይመልከቱ።
ቦርዱ ስለሚቀጥሉት ሁለት የትምህርት ዓመታት እያሰበ ሲሆን፣ ለቤተሰቦች እና ለሰራተኞች አስፈላጊ ቀናትን በሚመለከት የበለጠ እርግጠኝነት እንዲኖር ከማድረግ አኳያ የተዘጋጁትን ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎችን/ካለንደሮችን እየገመገመ ነው።
መታየት ያለባቸው ጥቂት ነገሮች፦
አስቀድሞ-ማቀድ፦ MCPS የትምህርት ቤቶች መክፈቻና መዝጊያ ቀናትን፣ የክረምትና የጸደይ ዕረፍቶችን እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቀናትን በተመለከተ ለቤተሰቦችና ለሰራተኞች በቂ የቅድመ-ማሳወቂያ ጊዜ ለመስጠት እንዲቻል፣ የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያዎችን/ካለንደሮችን በአንድ ጊዜ ለሁለት ዓመታት የማጽደቅ ዕቅድ እየታሰበበት ነው።
የስቴቱ መስፈርቶች፦ ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎቹ/ካለንደሮች በቅርቡ የተሻሻሉትን MSDE መስፈርቶች ያሟላሉ፤ እነዚህም ቢያንስ 180 የመማሪያ ቀናትን፣ የግዴታ የመማሪያ ሰዓቶችን፣ እንዲሁም ተማሪዎች ያመለጧቸውን ትምህርቶች ለማካካስ የሚሰጡ ቀናትን «ጁንቲንዝ» (Juneteenth) በዓል በፊት መጠናቀቅ እንዳለበት ተካቷል።
ሌሎች በበረዶ ምክንያት የሚያጋጥሙ የትምህርት ክፍለ-ጊዜ መስተጓጎሎች፦ የቀረቡት ዕቅዶች በፀደይ ወቅት የሚካካሱ ቀናትን ያካተቱ ሲሆን፣ እጅግ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ተጨማሪ መስተጓጎሎችን የሚያስከትል ከሆነ ደግሞ በይፋ የተፈቀደ ኦንላይን (virtual) ትምህርት አማራጭ ይኖራል።
አስተያየትዎን ይስጡ፦ የህዝብ አስተያየቶች ኦክቶበር እና ኖቨምበር 2026 ወቅት ይሰበሰባሉ፤ ቦርዱ ኖቨምበር 19 ቀን 2026 በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የመጨረሻው ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
MCPS በአካባቢው ትምህርት ቤቶች የሚሰጡትን ፕሮግራሞች በማጠናከር እና ሪጅናል ፕሮግራሞችን ይበልጥ ወጥ እና ተደራሽ በማድረግ ላይ በማተኮር፣ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት መርሃ ግብሮች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ይፋ አድርጓል።
ይህ ለቤተሰቦች ምን ማለት እንደሆነ፦
መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፦ MCPS በየቀኑ 60 ደቂቃ የሂሳብ ትምህርት እንዲሰጥ MSDE ያስቀመጠውን መስፈርት ተግባራዊ ማድረግ ለጊዜው አቁሟል።
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፦ የታቀዱት ለውጦች የትምህርት መስመሮችን ለመከተል ቀላል ይሆናል፣ መምህራን በተከታታይነት ማስተማር የመቻላቸውን ሁኔታ ያሻሽላል፣ የጋራ ምዝገባዎችን ይፈጥራሉ፤ እንዲሁም On-level፣ Honors፣ AP፣ IB እና Dual Enrollment የመሣሰሉ የትምሕርት አሰጣጥን ግልጽ ትርጓሜዎችን ያስቀምጣሉ።
ሪጅናል ፕሮግራሞች፦ MCPS እንደ STEM፣ የህክምና ሳይንስ ዘርፍ (Medical Exploration)፣ አመራር፣ ስነ-ጥበብ እና ዓለም አቀፍ ትምህርት የመሳሰሉ ልዩ ፕሮግራሞችን ተደራሽነት ለማስፋት በስድስት የተወሰኑ ሪጅኖች ተዘጋጅቷል።
ተማሪዎ8ኛ ክፍል ተማሪ ከሆነ(ች)፣ ,አዲሶቹ MCPS ሴንተር ፕሮግራሞች (Center Programs) ምን እንደሆኑ እና ለቤተሰብዎ ምን አማራጮች እንደሚኖሩ እያሰቡ ሊሆን ይችላል።
EdTalk:፡ MCPS ሴንተር ፕሮግራሞች
የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንትግሬስ ሪቬራ-ኦቨን (Grace Rivera-Oven) ስለ አዲሱ የሴንተር ፕሮግራሞች (Center Programs) ከአካዳሚክ ፕሮግራሞች ክፍል አስተባባሪ አንጃሊ ዌልስ (Anjali Wells) እና ከኮንሶርሺያ እና አፕሊኬሽን ፕሮግራም አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር ጂኒ ፍራንክሊን (Jeannie Franklin) ጋር ውይይት አድርገዋል። 8ኛ ክፍል ተማሪዎች በአካባቢያቸው የሚገኙ የተለያዩ የአራት ዓመት የአካዳሚክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞችን እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ ያብራራሉ።
የትምሕርት ቦርድ እና የሞንትጎምሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ሰራተኞች "የቤት ውስጥ ጥቃት ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር" ያከበሩ ሲሆን፣ የቦርድ አባላት እና ሰራተኞችም ድጋፋቸውን ለመግለጽ ሐምራዊ ቀለም ያላቸውን አልባሳት ለብሰው ተገኝንተዋል። ይህ እውቅና መስጠት፤ ግንዛቤን ለማሳደግ፣ በቤተሰብ ውስጥ በሚፈጸም ጥቃት የተጎዱትን ለመደገፍ፣ እንዲሁም ሰዎች ድምፃቸውን ለማሰማትና እርዳታ ለመጠየቅ ደህንነት የሚሰማቸው ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል።
MCPS ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ከጥብቅና አገልግሎቶች፣ ከደህንነት እቅድ ዝግጅት፣ እና ጤናማ ግንኙነትን ከሚያበረታቱ ግብዓቶች ጋር ለማገናኘት፣ Family Justice Center እና Choose Respect Montgomery ከመሳሰሉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፕሮግራሞች ጋር ይተባበራል። ለፈጣን ድጋፍ፣ Montgomery County Crisis Center በስልክ ቁጥር240-777-4000 24/7 አገልግሎት ይሰጣል፤ እንዲሁም National Domestic Violence Hotline 1-800-799-SAFE (7233) ወይም START የሚለውን ቃል ወደ 88788 በመላክ መድረስ ይቻላል።
ሁሉም ሰው ተጨማሪ መረጃ እንዲያገኝ፣ ድምፁን እንዲያሰማ እና ከተጎጂዎች ጎን በመቆም አብሮነቱን እንዲገልፅ እናበረታታለን።
ወደ MCPS Around the Table የመጀመሪያው ክፍል እንኳን በደህና መጡ!
በዚህ ልዩ የላቲኖ-ሂስፓኒክ ቅርስ ወር ዝግጅት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ MCPS ማህበረሰባችንን የሚያበለጽጉትን ባህሎች፣ ወጎች እና ጣዕመ ዜማዎች ያከብራል።
MCPS የምግብ እና የአመጋገብ አገልግሎት ክፍል (DFNS) በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የሚቀርቡትን፣ በላቲኖ-ሂስፓኒክ ባህል የተዘጋጁ የምግብ አይነቶችን ያስተዋውቃል፤ ይህም በቅርቡ MCPS የምግብ ዝርዝር ውስጥ የሚካተት አዲስ ምግብን ያካትታል።
ከዚያም፣ ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት እና ካርላ ሲልቬስትሬ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አባል፣ ከማስፓናዳስ ፈጣሪ ጋር ኢምፓናዳስን ኩሽና ገብተው ምግብ ይሠራሉ። ምግቡን በጋራ እያዘጋጁ፣ ምግብ ለማህበረሰባችን እጅግ አስፈላጊ ስለሚሆን ባህል፣ ወጎች እና ታሪኮች በተመለከተ ይወያያሉ።
በትምህርት ቤቶቻችን ከሚቀርቡት ምግቦች አንስቶ ከትውልድ ወደ ትውልድ እስከሚተላለፉት ወጎች ድረስ፣ "MCPS Around the Table" በምግብ፣ በባህል እና በውይይት አማካኝነት ሰዎችን አንድ ላይ ያሰባስባል።
ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ፣ የካፒታል በጀት እና CIP የመጀመሪያ ደረጃ ገለጻ እና የስራ ክፍለ-ጊዜ ቁጥር 1 (ጠዋት 10:00 a.m.)
ሐሙስ፣ ኦክቶበር 22፣ የቦርድ የስራ ስብሰባ (4፡00 p.m.)
ሰኞ፣ ኦክቶበር 26፣ የካፒታል በጀት እና CIP የመጀመሪያው የህዝብ አስተያየት የሚደመጥበት ችሎት (5፡00 p.m.)
ቦርዱ MCPS የኬብል ቻናሎች እና YouTube ላይ ሁሉንም ወርሃዊ የቦርድ ሥራ ስብሰባዎች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች የስፓንሽኛ ትርጉም ይቀርባል። በተጨማሪም፣ በአካል የተገኙ ተሳታፊዎች ለማንኛውም ስብሰባ የትርጉም አገልግሎቶችን መጠየቅ ይችላሉ። ጥያቄዎች ከስብሰባው ቢያንስ 10 ቀናት ቀደም ብለው መቅረብ አለባቸው። ስብሰባዎቻችንን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እና ማህበረሰባችን እንዲገናኝ ለማድረግ በጉጉት እንጠብቃለን!
በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ።
Facebook፣ Instagram፣ Bluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org