አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ኖቨምበር 20, 2026

የትምሕርት ቦርድ መልእክት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ኖቬምበር 19 ባካሄደው ስብሰባ፣ ለትምህርት ቤት ግንባታ፣ ለህንጻ ማሻሻያዎች እና ለወደፊት የመሠረተ ልማት ፍላጎቶች የሚውል በጀት ጭምር፣ በስድስት ዓመት የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ላይ ዋና ዋና ማሻሻያዎችን አጽድቋል። በስብሰባው ላይ፣ MCPS የቀድሞ ተማሪ ኤሪክ ካርፔንተር-ግራንታም እና ቤተሰቡ ስለ "Eric’s ID Law" መጽደቅ ላደረጉት የማቀንቀን አገልግሎት እውቅና የተሰጠ ሲሆን፤ በተጨማሪም የትምህርት ዲስትሪክቱ ሱፐርኢንቴንደንት ያቀረቡትን አዲስ "Student Butterfly Identifier Program" (በተማሪዎች መታወቂያ ላይ የቢራቢሮ ምልክት መለጠፍ) አስተዋውቀዋል። ይህ ፕሮግራም ጃንዋሪ 2027 በሙከራ ደረጃ ይጀመራል። ቦርዱ በተጨማሪም 'የሜሪላንድ ብሉ ሪባን ትምህርት ቤቶች' ተብለው የተሰየሙትን ሶስት የሞንት ጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን፣ እንዲሁም በጎልፍ ስፖርት የስቴት ሻምፒዮን የሆኑትን የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን እውቅና ሰጥቷል። በስብሰባው ላይ ከተነሱት ሌሎች ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦ «Blueprint for Maryland’s Future» ማዕቀፍ ውስጥ ስለሚሰጥ የሙያ ሥራ ምክር አገልግሎት የተደረገ ውይይት፣ ለትምህርት አመት 2027–2028 የቀረበው የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያ ግምገማ፣ እና ከቦርድ አባልነታቸው ለሚለቁ ሦስት አባላት ላበረከቱት አገልግሎት እውቅና መስጠት ይገኙበታል።

CIP ወቅታዊ መረጃ | የትምህርት ቤት ቀን መቁጠርያ/ካለንደር | የሙያ ምክር አገልግሎት | ብሉ ሪባን ትምህርት ቤቶች | የጎልፍ ሻምፒዮኖች | 'Eric’s ID Law'{ | የቦርዱ እውቅና | መጪዎቹ ስብሰባዎች


ስለ ካፒታል በጀት እና የትምህርት ቤት ግንባታ ወቅታዊ መረጃዎች

ቦርዱ ለበጀት ዓመት 2028 የትምህርት ቤት ግንባታ እና ለህንጻዎች ማሻሻያ የሚውል $581.6 ሚልዮን የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ አጽድቋ፤። በተጨማሪም ቦርዱ የስድስት ዓመት የትምህርት ቤት ግንባታ ዕቅድ (የበጀት ዓመት 2027–2032) ማሻሻያ ያጸደቀ ሲሆን፣ በዚህም አጠቃላይ ዕቅዱን $25 ሚሊዮን በመጨመር ወደ $1.879 ቢሊዮን ዶላር ገደማ አድርሶታል።

የጸደቀው ዕቅድ፣ ዋና ዋና የትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ እንዲከናወኑ ማድረግ፣ የትምህርት ቤት ሕንጻዎችን ማሻሻል እንዲሁም MCPS ዕለታዊ ሥራዎቹን ማከናወን ላይ ያተኩራል።

አንዳንድ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

የትምህርት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማስቀጠል በተመለከተ፦ ደማስከስ፣ ኢስተርን፣ ኖርዝውድ፣ ቻርልስ W. ውድዋርድ እና ቀደም ሲል ክራውን ፋርም ይባል የነበረው ቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሳሰሉት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች የተያዘላቸውን የጊዜ ሰሌዳዎች ጠብቆ ያስቀጥላል።

MCPS የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ለመደገፍ፦ ቦርዱ፣ የትምህርት ሥርዓቱን ሥራዎች ከመደገፍ አንፃር አዲስ እና ማዕከላዊ መጋዘን ለመሥራት $23 ሚሊዮን ዶላር፤ እንዲሁም ለትላልቅ የትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች እና ለተጣመረው MCPS ዋና መሥሪያ ቤት አጋሮችን ለመምረጥ $2 ሚሊዮን ዶላር መድቧል።

የበትምህርት ቤት ሕንፃዎችን ማሻሻል፦ ቦርዱ ለመንግስት ያቀረበው የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ፣ እንደ ማሞቂያና አየር ማቀዝቀዣ ሲስተሞች፣ ጣራዎች፣ መጸዳጃ ቤቶች፣ እና የእሳት አደጋ ማስጠንቀቂያዎች የመሳሰሉ አስፈላጊ የሕንፃ ማሻሻያዎች ላይ ያተኮሩ 22 ፕሮጀክቶችን ያካትታል።

የትምህርት ቤት መገልገያዎችን ፍላጎቶች ስለመደገፍ፦ ቦርዱ በሮዛ M. ፓርክስ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚካሄደው HVAC ፕሮጀክት $15 ሚሊዮን ዶላር ጭምር ለስቴት የበጀት ድጋፍ $75.8 ሚሊዮን ዶላር ጥያቄ እንዲቀርብ አጽድቋል።

የጸደቀው የካፒታል በጀት ጥያቄ፣ ለግምገማ ወደ ካውንቲው ሥራ አስፈጻሚ እና ወደ ካውንቲው ካውንስል ይቀርባል።


የትምህርት አመት 2027–2028 የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያ ላይ የተደረገ ውይይት

ቦርዱ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ያቀረቡትን የትምህርት ዓመት 2027–2028 የትምህርት ቤት ቀን መቁጠርያ ረቂቅ የተመለከተ ሲሆን፣ ለማጽደቅ የቀረበው ጥያቄ ግን ተቀባይነት አላገኘም። የቀን መቁጠሪያ ለመጨረሻ ከመጽደቁ በፊት በሚቀጥለው ስብሰባ ላይ ተጨማሪ ውይይት ይደረጋል፤ እንዲሁም ሂደቱ ወደፊት ሲቀጥል ቦርዱ ለቤተሰቦች ወቅታዊ መረጃ ያጋራል።

የቀረበውን ይመልከቱ፦ የትምሕርት ቤት ቀን መቁጠሪያ ውይይት ቪዲዮ


የሜሪላንድ የወደፊት ዕቅድ (Blueprint for Maryland’s Future)፦ የሙያ ምክር አገልግሎት ፕሮግራም ወቅታዊ መረጃ

ቦርዱ MCPS አመራሮች እና WorkSource Montgomery ያቀረቡትን «የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሙያ ሥራ ምክር አገልግሎት ፕሮግራም (MoCo CAP)» ፕሮግራም ገለጻ ተቀብሏል። ይህ ፕሮግራም «Blueprint for Maryland’s Future» በተሰኘው ሰነድ ስር የሚካተት እና በስቴት መንግስት እንዲተገበር የተደነገገ ተነሳሽነት ነው። ፕሮግራሙ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሙያ ስልጠና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ ይህም የተለያዩ የሙያ አማራጮችን እንዲያስቡ እና ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ ስለሚኖራቸው ህይወት እቅዶችን እንዲያጤኑ ይረዳቸዋል።

አቀራረቡ የፕሮግራሙን በርካታ ዘርፎች ያካተተ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

  • የሙያ ሥራ ምክር አገልግሎት፦ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ገለጻዎች፣ በአነስተኛ ቡድን ውይይቶች፣ በግል ምክርና ስልጠና፣ በተጋባዥ እንግዶች ንግግሮች እና በኮሌጅ ጉብኝቶች አማካኝነት የሙያ ትምሕርት የሚያገኙበት መንገድ ይመቻቻል።

  • የፕሮግራም ፋይናንስ ድጋፍ፦ ለበጀት ዓመት 2027 ከሚገኘው ወደ $9.93 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የስቴት የበጀት ድጋፍ ለ፦ WorkSource Montgomery፣ MCPS፣ እና ለሞንትጎመሪ ኮሌጅ እንዴት እንደሚከፋፈል።

  • የተማሪዎች የእቅድ ዝግጅት፦ ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ ሊከተሏቸው የሚችሏቸውን አማራጮች እንዲለዩ የሚያግዙ፣ ስለ ሥራ መስኮች ፍለጋ እና ስለ ስድስት ዓመት እቅድ ዝግጅት ባላቸው ተሳትፎ ላይ የሚሰጡ ወቅታዊ መረጃዎች።

  • የፕሮግራም ወቅታዊ መረጃዎች፦ ስለ ተማሪዎች የዳሰሳ ጥናቶች፣ የተሳትፎ መጠን፣ እንዲሁም ለሙያ ዝግጁነት ጥረታቸው እውቅና ያገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የተመሰረቱ መረጃዎች።

ቦርዱ ውይይት ባደረገበት ወቅት፣ አባላቱ የሚከተሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ጥያቄዎችን አንስተዋል፦ የሙያ ምክር አገልግሎቶች በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ምን ያህል ወጥ በሆነ መንገድ እየተተገበሩ እንደሆነ፤ በሙያ አማካሪዎች፣ በትምህርት ቤት ካውንስለሮች እና በሌሎች ሰራተኞች መካከል ኃላፊነቶች እንዴት እንደሚቀናጁ፤ እንዲሁም አዲሱ የስድስት ዓመት ዕቅድ ለቤተሰቦች እንዴት እንደሚገለጹ ትኩረት በመስጠት ተነጋግሮባቸዋል። የቦርድ አባላቱ፦ ፕሮግራሙ ለተማሪዎች እንዴት ተደራሽ እንደሆነ በተሻለ ለመረዳት፤ የተማሪዎችን ተሳትፎ እና ውጤት—በተለያዩ የተማሪ ቡድኖች መካከል ያሉ ልዩነቶችን ጭምር—መከታተል አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውበታል።

አቀራረቡን ይመልከቱ


ሶስት የሜሪላንድ ሰማያዊ ሪባን ትምህርት ቤቶችን እውቅና መስጠት

ቦርዱ፣ የትምህርት ዓመት 2026–2027 የሜሪላንድ ብሉ ሪባን 'Blue Ribbon' የላቀ ትምህርት ቤት ማዕረግ የተሰጣቸውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) መካከል ሦስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች—ቤቨርሊ ፋርምስ (Beverly Farms)፣ ትራቪላ (Travilah) እና ሰመርሴት (Somerset)—አድናቆት ተሰጥቷቸዋል።

የቦርድ አባላት ካርላ ሲልቬስትሬ እና ጁሊ ያንግ፣ እንዲሁም የቦርድ ምክትል ፕሬዚዳንት ብሬንዳ ዎልፍ፣ የእያንዳንዱን ትምህርት ቤት ስኬት የሚገነዘቡ እና የሚያወድሱ መግለጫዎችን ሰጥተዋል። የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን፤ በተማሪዎቻቸው፣ በሰራተኞቻቸው፣ በቤተሰቦች እና በትምህርት ቤት ማህበረሰቦቻቸው ስም እውቅናውን ለመቀበል ከቦርዱ ጋር ተገኝተዋል።

እያንዳንዱ ትምህርት ቤት፣ ከመላው የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ላሳዩት ቁርጠኝነትና ጥረት እውቅና ተሰጥቶታል፦

ሰመርሰት

ሰመርሰት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፦ ርዕሰ መምህርት ትራቪስ ዊብ እና የሰመርሰት ማህበረሰብ፤ ለልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላሳዩት ቁርጠኝነት፣ በትምህርት ሂደት ላይ ስለሚከተሏቸው አስተዋይ አቀራረቦች፣ «No Place for Hate» ፕሮግራም አማካኝነት ጉልበተኝነትን ለመከላከል ላደረጉት ጥረት፣ እንዲሁም ከአካባቢ ጥበቃ ትምህርት ጋር በተያያዘ ለፈጠሩት አጋርነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ትራቪላህ

ትራቪላህ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፦ ርዕሰ መምህር ዶ/ር ካሪን ዎከር እና የትራቪላህ ማህበረሰብ፤ በተግባር ላይ የተመሰረተ ትምህርትን፣ ከቤት ውጭ የሚሰጥ ትምህርትን፣ የተፈጥሮ አካባቢ ዘላቂነትን እንዲሁም የተማሪዎችን ተሳትፎ ለማሳደግ ላሳዩት ቁርጠኝነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በቨርሊ ፋርምስ

በቨርሊ ፋርምስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፦ ርዕሰ መምህር ስወርድዜውስኪ እና የበቨርሊ ፋርምስ ማህበረሰብ፤ በትምህርታዊ ስኬት ላይ ትኩረት በማድረጋቸው፣ በትምህርት ውጤት ረገድ የሚታዩ ልዩነቶችን በማጥበብ፣ በዲጂታል ደህንነት፣ በመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ሊተርሲ፣ እንዲሁም ተቀባይነት ያለው ምቹ የትምህርት ቤት ድባብ በመፍጠር ረገድ ላሳዩት ጥረት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ቦርዱ ለሦስቱም ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና ቤተሰቦች በዚህ እውቅና ምክንያት እንኳን ደስ አላችሁ ይላል!


የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስቴት የጎልፍ ሻምፒዮናዎችን ስለማክበር

የስቴት ሻምፒዮን

ቦርዱ የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወንዶችንና ሴቶችን ያካተተ የጎልፍ ቡድንን እንዲሁም ተማሪ አትሌት አንዲ ግሪንበርግን በስቴት ሻምፒዮና ውድድሮች ላስመዘገቡት ድል እውቅና ሰጥቷቸዋል። ቡድኑ 4A/3A ወንዶችንና ሴቶችን ያካተተ የቡድን ሻምፒዮና አሸናፊ ሲሆን፣ ግሪንበርግ ደግሞ በሴቶች የግል ውድድር ሻምፒዮናነቱን አሸንፋለች፤ ይህ ስኬት MCPS የመኸር ወቅት ስፖርቶች የመጀመሪያዎቹ የስቴት ሻምፒዮን ድሎች ናቸው።

የስፖርተኞቹን ስኬት ለማክበር በተገኙት ዋና አሰልጣኝ ጄምስ ማንዙራኒስ፣ የአትሌቲክስ ዳይሬክተር ቢል ቶዝ እና የዋልት ዊትማን ርዕሰ መምህር ግሬግ ሚለር ጋር በመሆን፣ የቦርድ አባል ተማሪ ልዑል ዳዊት የእውቅና መግለጫ ሰጥቷል።

ለተማሪ አትሌቶች፣ ለአሰልጣኞች፣ እና ለመላው የዋልት ዊትማን ትምህርት ቤት ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ!


ስለ "Eric's ID Law" እውቅና መስጠት እና በተማሪዎች መታወቂያ ላይ የቢራቢሮ ምልክት የሚደረግበትን ፕሮግራም ማስተዋወቅ

"butterfly program"

ቦርዱ እና ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ቶማስ W. ቴይለር፤ MCPS ተማሪ የነበሩትን ኤሪክ ካርፔንተር-ግራንታምን (የጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የትምህርት ዓመት 2023 ተመራቂ) እና እናታቸውን ሊንዳ ካርፔንተር-ግራንታምን፣ በግልጽ የማይታዩ የአካል ጉዳተኛ ሰዎች ያላቸውን ድጋፍ በመስጠት እና በመሟገት ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥቷቸዋል።

በስብሰባው ወቅት የቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን ለቤተሰቡ " Eric's ID Law" የተሰኘ የመታወቂያ ህግ በመደገፍ ያላቸውን ተሟጋችነት የሚዘከር ደንብ አቅርበዋል፣ ይህም የሜሪላንድ ነዋሪዎች በመንጃ ፈቃዶቻቸው እና በስቴት መታወቂያዎቻቸው ላይ የቢራቢሮ ምልክት በፈቃደኝነት እንዲጨምሩ ያስችላቸዋል።

ፕሮግራሙ በተከበረበት ወቅት፣ ጃንዋሪ 2027 ለሙከራ የሚጀመረው MCPS አዲሱ "የተማሪዎች መታወቂያ የቢራቢሮ ምልክት ፕሮግራም" ይፋ እንደሚደረግ ተካቷል። ይህ ተነሳሽነት፣ በፕሮግራሙ የሚሳተፉ ተማሪዎች የቢራቢሮ ምልክትን በትምህርት ቤት መታወቂያ ካርዶቻቸው ላይ የማሳየት አማራጭ እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ቦርዱ የካርፔንተር-ግራንታም ቤተሰብ የሚያደርጉትን ማቀንቀን፣ እንዲሁም በግልጽ የማይታይ የአካል ጉዳተኝነት ስላላቸው ግለሰቦች ግንዛቤን ለማሳደግ እና ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያደርጉትን ጥረት በአድናቆት ይገነዘባል።

ተጨማሪ ያንብቡ  |   ለማክበር የተደረገውን ኩነት ይመልከቱ

watch on instagram


የሦስት የቦርድ አባላትን አገልግሎት ማክበር

የቦርድ አባላት

የኖቬምበር 19 ስብሰባ፣ ለትምህርት ቦርድ አባላት ካርላ ሲልቬስትሬ፣ ብሬንዳ ዎልፍ እና ጁሊ ያንግ የመጨረሻው የትምህርት ቦርድ የሥራ ስብሰባ ነበር። ይህንን ወሳኝ ምዕራፍ ማሰብ፣ ተማሪ የቦርድ አባል የሆነው ልዑል ዳዊት ሦስቱ አባላት ስብሰባውን በራሳቸው እንዲያጠናቅቁ ጋበዛቸው፤ ይህም ለአገልግሎታቸውና ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ ትርጉም ያለው አጋጣሚ ፈጥሯል።

እያንዳንዱ አባል ለቦርዱ ልዩ የሆነ የኋላ ታሪክ እና አመለካከትን ያስታወሰ ሲሆን፣ ለሕዝብ ትምህርት እና ለተማሪዎች ስኬት ያላቸውን ቁርጠኝነትም አጋርተዋል።

  • ካርላ ሲልቬስትሬ በቦርዱ ውስጥ ለሁለት የአራት ዓመት የስራ ዘመናት ያገለገሉ ሲሆን፣ በትምህርት ፖሊሲ፣ በማህበረሰብ ተሳትፎ እና ለወጣቶች በመሟገት ረገድ ያላቸውን ልምድ አበርክተዋል። በተጨማሪም ለሁለት የስራ ዘመናት የቦርድ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል፤ በዚህም በትምህርት ቤቶች፣ በቤተሰቦች እና በሰፊው ማህበረሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

  • ብሬንዳ ዎልፍ በቦርዱ ውስጥ እያንዳንዳቸው አራት ዓመት የፈጁ ሁለት የስራ ዘመናትን ያገለገሉ ሲሆን፣ በትምህርት፣ በሲቪል መብቶች እና በህዝብ አገልግሎት ዘርፎች ከአራት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀ ልምድ ይዘው የመጡ ናቸው። እንደ ቦርድ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትነታቸው፣ በትምህርት ፍትሃዊነት፣ ተጠያቂነት፣ እንዲሁም በመላው ሞንትጎመሪ ካውንቲ ለሚገኙ ተማሪዎች እድሎችን በማስፋት ላይ ትኩረት አድርገዋል።

  • ጁሊ ያንግ እንደ መምህር፣ የትምህርት መረጃ ተንታኝ፣ እንዲሁም የኮሌጅ እና የሙያ አማካሪ በመሆን በዘርፉ ካካበቱት 20 ዓመታት በላይ ልምድ በመነሳት፣ በቦርዱ ውስጥ ለአራት ዓመታት ያህል አገልግለዋል። በቦርዱ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ፣ ሁሉም ተማሪዎች—በተለይም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ወይም ልዩ ቡድኖች ውስጥ የሚመደቡ ተማሪዎች—ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጓቸውን ግብዓቶችና ድጋፍ ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተዋል። እንዲሁም የቦርድ ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል።

ኖቬምበር 19 ከእነርሱ ጋር የመጨረሻ የሥራ ስብሰባ የተካሄደበት ቀን ቢሆንም፣ ይፋዊ የሥራ ጊዜያቸው እስከ ኖቬምበር 30 ድረስ ይቀጥላል። ቦርዱ ዲሰምበር 3 በሚያደርገው ስብሰባ፣ ከኃላፊነታቸው የሚለቁትን አባላት በይፋ እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፣ በዚሁ ስብሰባ ላይም አዲስ የተመረጡት ሦስት የቦርድ አባላት ሥራቸውን ሲጀምሩ አቀባበል ይደረግላቸዋል።

ቦርዱ፤ ወ/ሮ ሲልቬስትሬ፣ ወ/ሮ ዎልፍ እና ወ/ሮ ያንግ ለህዝብ ትምህርት እንዲሁም ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ ላበረከቱት የዓመታት አገልግሎት፣ ላሳዩት አመራር፣ እና ለነበራቸው ቁርጠኝነት ምስጋናውን ያቀርባል።


ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ሐሙስ፣ ዲሴምበር 3፣ የአዲሱ ቦርድ አባላት ቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት (4፡00 p.m.)

  • ሐሙስ፣ ዲሴምበር 10፣ የኃላፊዎች ምርጫ (9፡00 a.m.)
    የምደባ ሥነ ሥርዓት (12፡30 p.m.)
    የቦርድ የስራ ስብሰባ (1፡00 p.m.)

  • ሐሙስ፣ ዲሴምበር 17፣ ከተማሪ መሪዎች ጋር ስብሰባ (6፡00 p.m.)

ቦርዱ MCPS የኬብል ቻናሎች እና YouTube ላይ ሁሉንም ወርሃዊ የቦርድ ሥራ ስብሰባዎች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች የስፓንሽኛ ትርጉም ይቀርባል። በተጨማሪም፣ በአካል የተገኙ ተሳታፊዎች ለማንኛውም ስብሰባ የትርጉም አገልግሎቶችን መጠየቅ ይችላሉ። ጥያቄዎች ከስብሰባው ቢያንስ 10 ቀናት ቀደም ብለው መቅረብ አለባቸው። ስብሰባዎቻችንን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ እና ማህበረሰባችን እንዲገናኝ ለማድረግ በጉጉት እንጠብቃለን!


ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ። 

Facebook፣ Instagram፣ Bluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org