MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS አርማ

አበይት ጉዳዮች

ጁን 11, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 

ልናጠናቅቅ ተቃርበናል! የትምህርት ቤቶች የመጨረሻ ቀን — ጁን 18 — በጣም ተቃርቧል! ከመስክ ቀናት እና ከለር ሩጫዎች እስከ ጭብጨባ እና የምረቃ ሥነ ስርአት ድረስ፣ በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የዓመቱን የመጨረሻ ቀናት የማይረሱ ያደርጋቸዋል። እርስዎስ ከትምህርት ቤትዎ ጋር ይህንን ታላቅ የትምህርት ዓመት መጠናቀቅ እንዴት ያዩታል?

ፎተግራፎችዎን በማህበራዊ ሚዲያ #MCPSLastDay በመጠቀም ያጋሩ፣ እና ትምህርት ቤትዎ MCPS ማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች ላይ ሊቀርብ ይችላል። የትምህርት ዓመቱን በርትተን እናጠናቅ እና አብረን ያከናወንናቸውን ነገሮች ሁሉ በጋራ እናክብር!

 
  ነፃ የሠመር ምግብ ጁን 23 ጀምሮ ከ 100 በላይ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጣቢያዎች ላይ ይጀመራል።

MCPS የሠመር የምግብ አገልግሎት ፕሮግራም አካል በመሆኑ ዕድሜያቸው 18 አመት እና ከዚያ በታች ያሉ ልጆች እና ከ 18 አመት እድሜ በላይ የሆኑ አካል ጉዳተኞች በሺዎች የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጆች ያለ ምንም ወጪ የሚሰጥ የተመጣጠነ ምግብ ያገኛሉ። MCPS በዚህ ሠመር፣ ከ 100 በላይ በሆኑ ቦታዎች ላይ ከ12,000 በላይ ተማሪዎች ምግብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  አሁን ማወቅ ያለብዎት — ስለ ሠመር ወቅት ምንባብ

በዚህ ሠመር ወቅት እረፍት ለማድረግና ለመዝናናት ሁሉም ሰው በጉጉት የሚጠብቅ ቢሆንም፣ የመጨረሻው ደወል ስለተደወለ መማር መቆም የለበትም። በሠመር ወቅት በሙሉ ትምሕርት ለመቅሰም ቀላል መንገድ ይፈልጋሉ? ጥሩ መጽሐፍ ይምረጡ።

ተማሪዎች የንባብ ግብ እንዲኖራቸው እና እግረመንገዳቸውን አዳዲስ ታሪኮችን፣ ሀሳቦችን፣ እና ፍላጎቶችን እንዲመራመሩ MCPS ያበረታታል። ምን ማንበብ እንዳለብዎት ሀሳብ ማግኘት ይፈልጋሉ? ለሠመር ወቅት የተዘጋጀው መመሪያ ለእያንዳንዱ የክፍል ደረጃ ምክሮች አሉት፣ እንዲሁም የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት የበለጠ ተጨማሪ መጽሐፍት፣ እንቅስቃሴዎች፣ እና ሽልማቶችን ያቀርባሉ። መልካም የንባብ ጊዜ ይሁንላችሁ!

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

 
  ያልተጠቀሙበት የምሳ አካውንትዎ ላይ ያለ ቀሪ ገንዘብ ሌላ ተማሪን ሊረዳ ይችላል

ወላጆች፦ በተማሪዎ የምሳ አካውንት ውስጥ የተረፈውን ገንዘብ የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለመክፈል መዋጮ ማድረግ እንደሚችሉ ያውቃሉ? ለመለገስ፣ ወላጆች የልጃቸውን የምሳ አካውንት ቀሪ ሂሳብ ለማዋጣት እንደሚፈልጉ የሚገልጽ ኢሜይል እዚህ መላክ ይችላሉ። የተማሪዎን ስም፣ የትውልድ ቀን፣ ለመጨረሻ ጊዜ የተማረበትን ትምህርት ቤት እና የመታወቂያ ቁጥር መጻፍዎን ያረጋግጡ።

 
  የመኸር ወቅት ስፖርት ምዝገባ ጁላይ 13 ይከፈታል

የመኸር ወቅት የስፖርት ምዘናዎች ምዝገባ ሰኞ፣ ጁላይ 13 እኩለ ቀን ላይ ይጀምራል። የመኸር ወቅት/ፎል አትሌቲክስ ቡድኖች ረቡዕ፣ ኦገስት 12 ላይ የሙከራ ጊዜያቸውን ሊጀምሩ ይችላሉ። ለሠመር ኮንዲሽኒንግ የተመዘገቡ ተማሪዎች፣ ለመኸር ወቅት/ፎል ስፖርት ላይ መመዝገብ አለባቸው። ለተለየ መረጃ በአካባቢዎ ትምህርት ቤት የሚገኘውን አሰልጣኝ ያነጋግሩ።

 
  የሠመር እረፍት ጊዜዎን ወደ አገልግሎት ይለውጡት

የሠመር ወቅት የስቴት የምረቃ መስፈርት ለማሟላት "75 ሰዓት" የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ለማግኘት ምቹ ጊዜ ነው! የአሁኑ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች አርብ፣ ጁን 19 ጀምሮ SSL ሰዓቶችን ማግኘት መጀመር ይችላሉ።

በጁን ወር ያሉ እድሎች

 
  ማሳሰቢያ
  • የትምህርት ቦርድ BOE የሥነ ምግባር ፓነል፡ አባል ለመሆን ማመልከቻ የሚቀርብበት ቀነ ገደብ አርብ፣ ጁን 12 ነው።
  • የትምሕርት ቦርድ BOE የኮሙኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴ፡አባል ለመሆን ማመልከቻ እስከ አርብ፣ ጁን 19 እኩለ ቀን ድረስ መቅረብ አለባቸው።
  • ReachHIRE Summer Bridge program፡ በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ይህንን ነፃ ፕሮግራም ከ ጁን 29 እስከ ጁላይ 1 ድረስ የሚያስተናግዱ ሲሆን፣ ከፍ ላሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ ሲንየሮች ድረስ ክፍት ነው። ስለ ወደፊት የትምህርት እና የሙያ አማራጮችን ግንዛቤ ለማግኘት ከባለሙያዎች ጋር የመገናኘት እድሎች አሉ። ይመዝገቡ
  • የወደፊት ዝግጅቶች፦ 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች ስለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማራጮች የበለጠ ለማወቅ የመረጃ ክፍለ ጊዜዎችን እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል። 2027 የመኸር ወራት ጀምሮ፣MCPS በካውንቲው ውስጥ ልዩ ፕሮግራሞችን የማግኘት እድሎችን በማስፋፋት አዲስ የሪጅናል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሞዴል ይጀምራል። ተማሪዎች በፍላጎታቸው መሰረት ለሪጅናል ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሪጅናል ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ይጎብኙቀጣይ ክፍለ ጊዜዎች ጁን 11 እና 15 ይካሄዳሉ 
  • በቅርቡ የሚተገበሩ የሂሳብ ትምህርት ለውጦች፡- ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ፣ MCPS ለሂሳብ ትምህርት የክላስተር ሞዴል ተግባራዊ ያደርጋል። በመማሪያ ክፍል ውስጥ ያለውን የተለያየ ​​የትምህርት ደረጃዎች ለመቀነስ ተማሪዎች እንደየችሎታቸው በተለያየ ቡድን ይደራጃሉ፣ ይህም መምህራን ትምህርትን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲያቅዱ፣ የተማሪዎችን የመማር አቅም እንዲለዩ እና ለተማሪዎች ችሎታ የሚመጥናቸውን ወቅታዊ ድጋፍ እና ማበልጸጊያ እንዲሰጡ የበለጠ ምቹ ያደርገዋል። ጁን 16 የሚደረጉ ቀጣይ ስብሰባዎች
  • መኪና እያሽከረከሩ የትምህርት ቁሳቁሶችን መሰብሰብ:  ዓርብ፣ ጁላይ 24 ከጠዋቱ 9 a.m.–2 p.m. አድራሻው፦ ጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት at Gaithersburg High School, 101 Education Blvd. ጌትስበርግ። ቤተሰቦች ለትምህርት ቤት የሚጠቅሙ መጠነኛ ያገለገሉ ቁሳቁሶችን እና የምግብ መያዣ እቃዎችን በነፃ ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም SNAP ጥቅማጥቅሞች፣ ለነፃ እና ለቅናሽ ዋጋ ምግቦች እና ለሠመር የድጋፍ ፕሮግራሞች የመመዝገብ እድሎች ይኖራሉ። ተማሪዎች ከዝግጅቱ በፊት እና በዝግጅቱ ወቅት ለሚሰጡት የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት የትምህርት ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ
 
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ታሪክ ቅርስ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ይቃኙ

ጁን 27-28 ከእኩለ ቀን ጀምሮ እስከ 4 p.m. 27ኛው ዓመታዊ የታሪክ ቅርስ ቀናት ቅዳሜና እሁድ የአካባቢውን ታሪክ እና ባህል ይቃኙ። ከ 30 በላይ ሙዚየሞች፣ ፓርኮች፣ እና ታሪካዊ ቦታዎች ነፃ የመግቢያ፣ የኤግዚቢሽን፣ የሙዚቃ፣ የማሳያ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲን ታሪካ የቀረጹ ሰዎች እና ቦታዎችን የሚያንፀባርቁ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ያቀርባሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ይውሰዱ

 

በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools