MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS አርማየሠመር እትም

አበይት ጉዳዮች

ጁን 25, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 

የመጨረሻ የትምሕርት ውጤቶች ተዘጋጅተዋል!: የሪፖርት ካርዶች እስከ ጁን 29 ድረስ ParentVue ላይ ይገኛሉ፣ እና እስከ ጁን 30 ድረስ በፖስታ ወደ ቤት ይላካሉ።

 
  ከ 100 በላይ በሆኑ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጣቢያዎች ነፃ የሠመር ምግብ አገልግሎት ይሰጣል።

በሺዎች የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጆች MCPS የሠመር ምግብ አገልግሎት ፕሮግራም ላይ ምግብ ያገኛሉ፣ ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በታች ላሉ ልጆች እና ከ 18 ዓመት በላይ ለሆኑ አካል ጉዳተኞች ያለ ምንም ወጪ የሚሰጥ የተመጣጠነ ምግብ ይቀርባል። MCPS በዚህ ሠመር፣ ከ 100 በላይ በሆኑ ቦታዎች ላይ ከ12,000 በላይ ተማሪዎች ምግብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በተጨማሪ ያንብቡ እና በአቅራቢያዎ የምግብ አገልግሎት የሚሰጥበትን ቦታ ያግኙ።

 
  ተያይዟል፡ የሠመር ትምህርት እና ግብዓቶች መመሪያ

ለሠመር የተዘጋጀ የሠመር ወራት እንቅስቃሴዎችን ለማሰስ የሚጠቀሙበት ዲጂታል መመሪያ በውስጥ፣ ስለ ሠመር ንባብ ውድድር እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት የምንባብ ዝርዝሮችን በየደረጃው ያገኛሉ።

ማንበብ ለምን ያስፈልጋል? ለእርስዎ/ለእናንተ ጥሩ ነው! ይህ መመሪያ እንደሚከተለው ሊረዳዎት ይችላል፦

  • የንባብ ግብ ያዘጋጁ — በሚያነቡት የመጽሐፍት ብዛት ወይስ ምን ያህል ሰዓት እንደሚያነቡ? ምርጫዎን ይውሰዱ!
  • ምን ያህል እንዳነበቡ እድገትዎን ይመዝግቡ/ይከታተሉ።
  • በአዲሱ የትምህርት ዓመት መጠቀም የሚያስችል ጠንካራ የንባብ ልማዶችን ገንባ(ቢ)። 

በ 2026 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት የሠመር ንባብ ውድድር ላይ በመሳተፍ አስደሳች ሽልማቶችን ማግኘት እንደምትችሉ አትርሱ!

ይህ ብቻ አይደለም። መመሪያው ብዙ ተጨማሪ ነገሮች አሉት! በሚከተሉት ቋንቋዎች ይመልከቱ፦

 
  በሞቃት ቀናት፣ SSL ሰዓቶችን ለማግኘት አመቺ መንገዶች ይኖራሉ

የሠመር ወቅት የስቴት የመመረቂያ መስፈርትን 75 ሰዓት ለማሟላት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ለማግኘት ምቹ ጊዜ ነው። የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች SSL ሰዓት ለማግኘት የተማሪ አገልግሎት መጀመር ይችላሉ።

ጁላይ ወር ያሉት እድሎች

 
  በርካታ ድምጾችን ማክበር፣ አንድ ሀገር — መልካም 250ኛ ዓመት፣ አሜሪካ!

በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሚገኙ ተማሪዎች የዩናይትድ ስቴትስን 250ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የሚከበርበትን MCPS Celebrates Many Voices, One Nation an eBook የተሰኘ ዘይቤ በመጠቀም የአገራችንን ታሪክ ለመተረክ እያገዙ ናቸው። ከዘፈኖችና ጭፈራዎች እስከ ግጥሞችና ስዕሎች ድረስ በተማሪዎች የተዘጋጁ ስራዎችን ያካተተው ስብስብ አገራችንን የበለጠ ጠንካራ የሚያደርጉ በርካታ ድምጾችን፣ ልምዶችን እና ማህበረሰቦችን ያንፀባርቃል። eBook ይመልከቱ እና የተማሪዎቻችንን የፈጠራ ችሎታ ያድንቁ።

 
  MCPS የወላጅ አካዳሚ፡ ለመዋዕለ ሕፃናት፣ ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይዘጋጁ

በተማሪዎ የትምህርት ጉዞ ውስጥ ለቀጣዩ ትልቅ እርምጃ ይዘጋጁ። ልጅዎ መዋእለ ህጻናት ለመጀመር፣ ወደ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመሸጋገር ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመጀመር እየተዘጋጀ(ች) ቢሆንም፣ እነዚህ ወሳኝ ክስተቶች ደስታን፣ አዳዲስ እድሎችን እና ብዙ ጥያቄዎችን ያስከትላሉ።

MCPS Parent Academy በተከታታይ ትምህርት እርስዎን ለመርዳት ዝግጁ ነው። ጠቃሚ መረጃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና ለቀጣዩ ዓመት መረጃ እንዲያገኙ፣ በራስ መተማመን እንዲሰማቸው እና ዝግጁ እንዲሆኑ የተነደፉ ግብዓቶችን ለማግኘት የሽግግር አውደጥናት ቀረጻዎችን እና አቀራረቦችን ይመልከቱ።

የተቀረጹትን እና ለውይይት የቀረቡትን ይመልከቱ። 

 
  ተማሪዎች በዓመታዊ "Girl Power Contest" ውድድር ከፍተኛ ሽልማቶችን አግኝተዋል

ስድስት የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች "Montgomery County Commission for Women’s" ለዘጠነኛው አመታዊ በአል ስላቀረቡት ዝግጅት ሽልማት አግኝተዋል። ተሳታፊዎች ማን በተምሳሌትነት እንዳነሳሳቸው የሚገልጹ ድርሰቶችን፣ ግጥሞችን፣ ስዕሎችን ወይም ዘፈኖችን ማቅረብ ይችላሉ። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የተገነባ ቤት ውስጥ ይግቡ

ከቶማስ ኤዲሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሪዎች የተገነባው ይህ ቤት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪዎች ኮንስትራክሽን ትሬዲንግ ፋውንዴሽን፣ ጋር በመተባበር በግንባታ ፕሮግራም የተዘጋጁ በተግባር እየሠሩ የመማር እና ለሙያ ዝግጁ የመሆን ክህሎቶችን ያንፀባርቃል ይመልከቱ

 
  የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በብሔራዊ የታሪክ ቀን ውድድር ሽልማት አግኝተዋል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በኮሌጅ ፓርክ፣ ሜሪላንድ በተካሄደው 2026 ዓ.ም የብሔራዊ የታሪክ ቀን ውድድር ላይ ከሦስት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ስምንት ተማሪዎች እውቅና አግኝተዋል። እነዚህ ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ የታሪክ ቀን ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፣ በስቴት ደረጃ ለመወዳደር ተንቀሳቅሰዋል፣ እና ውጤታቸውም በሀገር አቀፍ መድረክ ላይ ለመወዳደር ብቁ አድርጓቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  ማሳሰቢያ
  • ቅርስ የሚዘከርበት ቀናት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ታሪክ ከጁን 27 እስከ 28 ከቀትር እስከ p.m. ከ 30 በላይ ሙዚየሞች፣ ፓርኮች፣ እና ታሪካዊ ቦታዎች ነፃ የመግቢያ፣ የኤግዚቢሽኖች፣ ቀጥታ የሚቀርብ ሙዚቃ፣ አውደ ርዕይ እና ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ያቀርባሉ።
  • Regeneron Science Talent Search፡የትምሕርት አመት 2027 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት STEM ውድድር የምርምር ውጤቶችን ለማቅረብ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ክፍት ነው። ማመልቻው ሐሙስ፣ ኖቨምበር 5 ከቀኑ 8 p.m. በኦንላይን መቅረብ አለበት።
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools