MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS Logo

አበይት ጉዳዮች

ሴፕተምበር 24, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  ስለ ወደፊቱ ማቀድ፦ መረጃ፣ ውይይት፣ እና የማህበረሰብ ድምፅ

40 ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ MCPS የተማሪዎች ምዝገባ ቁጥር እየቀነሰ ነው። በዚህም ምክንያት፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ቦታ ሲኖራቸው፣ ሌሎች ማህበረሰቦች ግን አሁንም በማደግ ላይ ናቸው። ይህ ማለት፥ ትምህርት ቤቶቻችንን እና የተለያዩ ተቋሞቻችንን እንዴት እየተጠቀምንባቸው እንዳለ በካውንቲው ደረጃ በጥልቀት የምንመረምርበት፣ እንዲሁም ለሁሉም ተማሪዎች የተሻለ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ የምናቅድበት ጊዜ አሁን ነው ማለት ነው።

ትምህርት ቤቶቻችንን እና ውስን ሀብታችንን በብቃት መጠቀም ማለት፣ ተማሪዎች በጣም በሚፈልጓቸው ዘርፎች ላይ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ላይ ማዋል ማለት ነው፤ እነዚህም ጠንካራ የማስተማር ሂደት፣ ውጤታማ የትምሕርት ፕሮግራሞች፣ እንዲሁም እያንዳንዱ ተማሪ እንዲያድግና እንዲሳካለ(ላ)ት የሚያግዙ አገልግሎቶችና ድጋፎችን መስጠት ማለት ነው። በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች እጅግ ጥሩ የሆኑ የትምሕርት ተሞክሮዎችን እንድናቀርብ ያግዘናል።

መታወቅ ያለበት አስፈላጊ ነገር፦ ይህ ስራ በሁለት የተለያዩ ደረጃዎች በሁለት አመት ውስጥ ይከናወናል።

በዚህ የትምህርት አመት፥ MCPS በመላው ካውንቲው የሚገኙ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ይገመግማል፤ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን የመዝጋት እና የማጣመር ዕድሎችን ለመመልከት የሚያስችል ግልጽ እና አሳታፊ አሰራር ይዘረጋል።

አንድ ትምህርት ቤት የመዘጋት ወይም ከሌላ ትምህርት ቤት ጋር የመጣመር ዕድል ከቤተሰቦች አስፈላጊ ጥያቄዎችን እንደሚያስነሳ እናውቃለን። ምንም ዓይነት ውሳኔዎች አልተወሰኑም፤ እንዲሁም ይህ ሂደት ትምህርት ቤቶችን በሚመለከት አስቀድሞ የተወሰነበት ጉዳይ አይደለም። ሥራው የሚጀምረው በመረጃ፣ በመመዘኛዎች እና ከማህበረሰቡ ጋር በሚደረጉ ውይይቶች እና በሚሰበሰብ አስተያየት ነው። ተጨማሪ መረጃ እንዴት ማግኘት እና አስተያየት መስጠት እንደሚችሉ ይወቁ።

 
 

 
  የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማዕከል ፕሮግራሞች፦ የመኸር ወቅት ማሳያ ዝግጅቶች በኦክቶበር ወር ይጀመራል

MCPS ልዩ ትኩረት የሚሰጥባቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማዕከል ፕሮግራሞች ተደራሽነትን እያሰፋ ሲሆን፣ ይህም በየአካባቢ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጥልቅ እና ጠንካራ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ከማቅረብ ጎን ለጎን፣ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከፍላጎታቸውና ከዝንባሌአቸው ጋር የተሳሰሩ ፕሮግራሞችን የመከታተል ተጨማሪ እድሎችን እንዲያገኙ ያደርጋል። የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ቤተሰቦች ሐሙስ፣ ኦክቶበር 1 በሚጀመሩት የመኸር ወቅት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስተዋወቂያ ዝግጅቶች አማካኝነት መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ። እነዚህ ዝግጅቶች ተማሪዎችና ቤተሰቦች ትምህርት ቤቶችን ለመጎብኘት፣ ስለ ፕሮግራሞችና ትምህርቶች መረጃ ለማግኘት፣ ከሰራተኞች ጋር ለመገናኘት እንዲሁም ለፍላጎታቸውና ለዓላማቸው የሚስማማውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቆይታ በተመለከተ ማሰብና ማሰላሰል ለመጀመር ጥሩ አጋጣሚ ናቸው። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  አሁን ያውቃሉ — በየቀኑ ትምሕርት ላይ መገኘት አስፈላጊ ነው።

በየቀኑ ትምህርት ቤት ውስጥ ከመሆን የበለጠ አስፈላጊ ነገር የለም። በየቀኑ ትምህርት ቤት መገኘት ተማሪዎች እንዲማሩ፣ ጓደኝነት እንዲመሠርቱ፣ በሚተማመኑባቸው አዋቂዎች ዘንድ ግንኙነት እንዲፈጥሩ እና በሚወዷቸው ተግባራት ላይ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣቸዋል። ከሁሉም በላይ፣ በአካል መገኘት የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፤ እንዲሁም አቅማቸውን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም የሚችሉበት እድል ይሰጣቸዋል። ወላጆች እና ቤተሰቦች፣ እባካችሁ ልጃችሁ በየቀኑ ትምህርት ቤት መገኘት እንዳለበ(ባ)ት እና ለመማር ዝግጁ መሆኑ(ኗ)ን አረጋግጡ።

ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ: English | Spanish |አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese

 
  MCPS ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሂስፓኒክ ቅርስ ወር በደመቀ ሁኔታ ይከበራል

MCPS ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ባህልን፣ ማንነትን፣ እና ማህበረሰብን በማክበር የሂስፓኒክ ቅርስ ወርን እየዘከሩ ነው። ፎተግራፎችን ይመልከቱ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ያንብቡ። የሂስፓኒክ ቅርስ ወር እስከ ኦክቶበር 15 ድረስ የሚከበር ስለሆነ ትምህርት ቤትዎ ወይም ቢሮዎ በዓሉን እንዴት እያከበራችሁ እንደሆነ ለማሳወቅ አሁንም ጊዜ አለ። መልእክት ይላኩልን፤ እና 'The Bulletin' ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን ላይ ሊቀርብልዎት ይችላል!  

 
  የበለፀገ፣ የተፋጠነ፣ እና ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች የሚሰጡ የትምህርት እድሎችን ይቃኙ።

ቤተሰቦች በዚህ የመኸር/ፎል ወቅት በሚካሄደው የተፋጠነ እና የበለጸገ ትምህርት (AEI) የቤተሰብ ዌቢናር ተከታታይ ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ባለ አራት ክፍል ተከታታይ ቨርቹዋል የትምሕርት ማበልጸግ እና የተፋጠነ እድሎችን፣ ተሰጥኦ እና ችሎታ ያላቸው ተማሪዎችን መለያ፣ የግንዛቤ (ኮግኒቲቭ) ችሎታ ፈተና (CogAT) እና የወላጅ አቀንቃኝነት በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ለቤተሰቦች መረጃ እና ግብዓቶች ይሰጣሉ።

ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ፦ English | Spanish |አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese

 
  ለኮሌጅ የሚደረግ ድጋፍ፦ የኮሌጅ ኤግዚቢሽኖች፣ የገንዘብ ድጋፍ እና FAFSA እገዛ
  • MCPS፣ Career Council, Inc. እና College Fairs USA፤ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በአካል የሚካሄድ የኮሌጅ አውደ ርዕይ (College Fair)፣ አርብ ኦክቶበር 9 ከጠዋቱ 9:30 a.m እስከ 12:30 p.m. ጌትስበርግ በሚገኘው ቦኸረር ፓርክ እንደሚያዘጋጁ ለማሳወቅ እንወዳለን። በትምህርት ቀን በኤግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች በኦንላይን መገለጫቸውን እንዲሞሉ የሚያስችል አገናኝ ሊንክ ያገኛሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ካውንስለር ማነጋገር አለባቸው። የአውደ ርዕዩ መግለጫ/Fair Flyer:/እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish
  • ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲንየር ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው፦ የኮሌጅ ምዝገባ እና የነፃ ትምህርት ዕድል (scholarship) ማመልከቻ የማቅረቢያ ወቅት እየተጀመረ ስለሆነ፣ ስለ ኮሌጅ ማመልከቻ ሂደት እና ስለ ፋይናንሻል ኤይድ (የገንዘብ ድጋፍ) ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት MCPS የኮሌጅ እና የሙያ ቃኚዎች (College and Career Navigators) ዝግጁ መሆናቸውን አስታውሱ። ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፤ ለኮሌጅ ትምህርት ትክክለኛውን መንገድ ስለመምረጥ፣ የድርሰት ጽሁፍ ስራዎችን (essays) ስለማዘጋጀት እና ስለ 'Common App' አጠቃቀም ለቤተሰቦች መመሪያ ለመስጠት የተለያዩ በአካል የሚከናወኑ እና በኦንላይን የሚሰጡ ወርክሾፖችን እያዘጋጁ ናቸው።የሚቀርበው ምን እንደሆነ ይመልከቱ!
  • ሞንትጎመሪ ኮሌጅ ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 3፣ ከጠዋቱ 10 a.m እስከ 2 p.m. ድረስ "FAFSA Day" ዝግጅት ያቀርባል፤ ተጨማሪ ይወቁ። 
 
  አዲስ SSL ቅጾች እዚህ ይገኛሉ፦ ተማሪዎች ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ፡

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤት (MCPS) ተማሪዎች በሙሉ ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያስፈልጋቸዋል። MCPS = SSL ቅጾችን፣ ወሳኝ በሆኑ አዳዲስ የጊዜ ገደቦች እና የተሻሻሉ አገናኝ ሊንኮችን አሻሽሏል።

በቅጹ ላይ የተደረጉ ቁልፍ የሆኑ ለውጦች

  • MCPS ቅጽ 560-51 (SSL የተግባር ማረጋገጫ ቅጽ) 
    • በተሻሻለው ቅጽ መሠረት፣ ድርጅቶች የአካዳሚክ ዝግጅት እና የአገልግሎት ተግባር ዝርዝሮችን አለባቸው። ተማሪዎች የተገነዘቡትን እና ያስተዋሉትን የቀሰሙትን ትምህርት ነክ ሀሳባቸውን ለመግለፅ እንዲችሉ የበለጠ ተጨማሪ ቦታ ተሰጥቷል።
  • MCPS ቅጽ 560-50 (የግል SSL መጠየቂያ)

SSL አስተባባሪዎች እስከ አርብ፣ ሴፕቴምበር 25 ድረስ ለተከናወኑ አገልግሎቶች የበፊት SSL ቅጾችን ይቀበላሉ። ከአርብ፣ ሴፕቴምበር 25 በኋላ የሚከናወን ማንኛውም አገልግሎት በአዲሶቹ ቅጾች መመዝገብ አለበት።

 
  MCPS አትሌቲክስ ጨዋታ ውስጥ ይቀጥሉ!

2026–2027 የትምህርት አመት ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችን የያዘ "R.A.I.S.E. Report" በመከታተል MCPS አትሌቲክስ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ! ስለ JV ወጣት ሴቶች ፍላግ ፉትቦል (flag football) መጀመር፣ ስፖርታዊ ጨዋነት እና የተመልካቾች ደህንነት፣ የተማሪ-አትሌቶች አመራር ሚና፣ የስፖርት ህክምና፣ የአሰልጣኝነት እድሎች፣ አዳዲስ የስፖርት አስተባባሪዎች እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ዝርዝር መረጃ ያግኙ። ተማሪ-አትሌት፣ አሰልጣኝ፣ ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ደጋፊም ብትሆኑ፣ በትምህርት ቤቶች መካከል በሚደረጉ የስፖርት ውድድሮች ለሚታደሙ ሁሉ የሚሆን አጓጊ ነገር ይኖራል።

 

ማሳሰቢያዎች፦

  • የቅዳሜ ትምህርት/Saturday School፦ የማጠናከሪያ ትምህርት ክፍለ-ጊዜ ቅዳሜ፣ ሴፕቴምበር 26፣ ከጠዋቱ 8:30 እስከ 11:00 a.m. ይጀመራል! ቅዳሜ ጠዋት ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል (K-12ኛ) ላሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮግራሞች የሚካሄዱ ሲሆን ንባብ፣ የቋንቋ ስነ ጥበብ፣ ሂሳብ፣ የፈተና ዝግጅት፣ እና ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ የመሳሰሉ STEM ማበልጸጊያዎች ላይ ያተኩራሉ። ክፍያው በዓመት $100 ነው (FARMS ተጠቃሚዎች $50)፤ እንዲሁም ወደ ማዕከሎቹ ለማድረስ MCPS አውቶቡሶች አገልግሎት ይሰጣሉ።በተጨማሪ ተማሩና ኣመልክቱ።
 
  ከመማሪያ ክፍል ውጭ
  • የወጣቶች ታወን ሀውስ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ስብሰባ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 29 ከቀኑ 6 p.m. ሮክቪል በሚከተለው አድራሻ፦ Council Office Building, Third Floor, 100 Maryland Avenue in Rockville ወይም በዙም ይካሄዳል። የሚሳተፉ ተማሪዎች ጥያቄዎቻቸውን እና ስጋቶቻቸውን ማቅረብ እና ከካውንቲው አመራሮች ጋር በሚደረግ ውይይት መሳተፍ ይችላሉ። ለመሣተፍ ይመዝገቡ. 
  • ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣት ሴቶች የመኸር/Fall ክፍለ ጊዜ፦ ይህ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጠው ነፃ፣ የኦንላይን፣ 10-ሳምንት የሚፈጅ የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ሴፕቴምበር 28 በሚውልበት ሳምንት ይጀመራል። ትምህርቶች ማክሰኞ ከቀኑ 7 p.m.,፣ ረቡዕ ከቀኑ 4፡30 p.m. ወይም ረቡዕ ከቀኑ 8 p.m. ላይ ይካሄዳሉ ይመዝገቡ። የበለጠ መረጃ ያግኙ:እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish
  • Design + Build at Blackrock Center for the Arts፦ ይህ ነፃ ፕሮግራም BlackRock Center for the Arts የአካባቢ ጥበቃን የሚያጎለብት የመሬት ገጽታን በመንከባከብ ላይ ያተኩራል፤ ይህም የአካባቢ እፅዋትንና ዛፎችን ያካትታል። ከኦክቶበር 3 ጀምሮ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሴኔካ ክሪክ (Seneca Creek) የውሃ ተፋሰስን ለማሻሻል የሚረዳ ፕሮጀክት በመንደፍና በመትከል ስድስት ተከታታይ ቅዳሜዎችን ያሳልፋሉ። ተማሪዎች እስከ 18 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት (SSL) ማግኘት ይችላሉ።ያመልክቱ 
  • Latina Legacy Conference፡ ይህ ለላቲኖ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጀ ዝግጅት፣ አርብ ኦክቶበር 30 ቀን ከጠዋቱ 10 a.m.-1 p.m. ሮክቪል በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል። አድራሻው፦ 15 W. Gude Drive in Rockville. ርዕሶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ የላቲና ሴቶች ደህንነት እና የአእምሮ ጤና፤ በትምህርት ዘርፍ ያሉ ላቲና ሴቶች፤ የላቲና ሴቶች የአማካሪነት (mentorship) ተሳትፎ፤ እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህ እና የላቲና ተማሪዎች ድምፅ። ለመመዝገብ፣ ተማሪዎች እስከ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ድረስ ምክትል ርዕሰ መምህራቸውን ማነጋገር አለባቸው።
  • ለአሜሪካ ያለዎትን ራዕይ ያጋሩ፡ 5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ፕሬዚዳንታዊ ንግግር በመጻፍና በማቅረብ እስከ $1,000 ሽልማት ማግኘት ይችላሉ። "ንግግሩን" ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተመረጡ በማሰብ የበዓለ ሲመት ንግግራቸውን 2-3 ደቂቃ በሚፈጅ ቪዲዮ እንደሚያቀርቡ ያበረታታል። ለዴሞክራሲያችን ምርጥ ነው የምትሉትን አንድነትን የሚያበረታታ ራዕይ አቅርቡ።ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ መወዳደሪያው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ አርብ፣ ኦክቶበር 30ነው።
  • *NEW* Smokey Bear Poster Contest: 7ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲወዳደሩ ተከፍቷል። የሜሪላንድ የደን ልማትና ጥበቃ አገልግሎት 120ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ፣ 7ኛ ክፍል ተማሪዎች የእሳት አደጋ መከላከል ወርን አስመልክቶ "Smokey Bear" የተሰኘ የፖስተር ውድድር አዘጋጅቷል። ተማሪዎች "የዱር ሰደድ እሳትን መከላከል የሚችሉት እርስዎ ብቻ ነዎት!"/“Only YOU can prevent wildfires!” የሚለውን ታዋቂ መልእክት መነሻ በማድረግ ኦሪጅናል የጥበብ ሥራ ፈጥረው እንዲወዳደሩ ተጠይቀዋል። የዱር ሰደድ እሳት ደህንነትን እና የደን ጥበቃን ለመዳሰስ መወዳደሪያው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ ሰኞ፣ ኖቬምበር 2ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
  • *NEW* Capital Weather ከመዋዕለ-ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ህጻናትን፤ ስለ አየር ሁኔታ፣ ስለ ወቅቶች፣ በአየር ንብረት ወይም በተፈጥሮ ተመስጠው የፈጠሯቸውን ኦሪጅናል የጥበብ ሥራዎች «Kids Art Showcase» እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። ለሚቀጥሉት በርካታ ወራት ውስጥ በየሳምንቱ አንድ ግቤት (entry) በመምረጥ፣ ከትንበያ ጋር capitalweather.com፣ Capital Weather መተግበሪያ፣ በዜና መጽሔቶች (newsletters) እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያቀርባሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
 

ዜና አምድ

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools