አበይት ጉዳዮች
ማርች 12, 2026
|
|
|
እንሰማዎታለን፡ የእርስዎ ድምጽ እና ልምድ አስፈላጊ ነው!– ይህንን አስፈላጊ የዳሰሳ ጥናት ይሙሉ |
|
ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን! በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ፣ MCPS ጉልህ የሆኑ የአሠራር ለውጦችን እና ፈረቃዎችን ተግባራዊ አድርጓል — የተደረጉት ለውጦች የትምህርት ውጤት አሰጣጥ፣ ደህንነት (በትምህርት ቤቶች ውስጥ የፖሊስ መገኘትን ጨምሮ)፣ የተማሪዎች የስነምግባር ደንብ፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምሳ ሰዓት ክፍት እንደሚሆን እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሞባይል ስልኮች አጠቃቀምን የመሳሰሉ የተለያዩ ርዕሶችን የሚመለከቱ ናቸው። ከዛሬ ጀምሮ፣ MCPS ለቤተሰቦች፣ ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች አስፈላጊ በሆኑት በእነዚህ በርካታ ጉዳዮች ላይ የዳሰሳ ጥናቶችን እያሰራጨ ነው፤ በተግባር እንዴት ለእርስዎ እንደሚሠራ ማወቅ እንፈልጋለን።
የዳሰሳ ጥናቱ እዚህ ይገኛል። ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ጥያቄዎችን አያገኝም። ከአንድ በላይ በሆነ ቡድን አባል ከሆኑ (ለምሳሌ፦ ወላጅ የሆኑ ሰራተኛ፣ የዳሰሳ ጥናቱን ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲሞሉ እና የተለያዩ ጥያቄዎች ሊደርሱዎት ይችላል፣ ነገር ግን የልጅዎን ትምህርት ቤት እና የሥራ ባልደረባ መሆንዎን የሚያመለክት ወላጅ እንደሆኑ አንድ ጊዜ እንዲገልጹ ይጠየቃሉ፣ እና ኢሜይልዎን ይጠየቃሉ)።
|
|
|
|
|
|
ቦርዱ የድንበር ጥናት አማራጮችን እየገመገመ ስለሆነ ማርች 26 የመጨረሻ ውሳኔ ድምጽ ይሰጣል። |
|
MCPS ከትምህርት ቤት ወሰኖች እና ከረጅም ጊዜ የመገልገያ ኢንቨስትመንቶች ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ዕቅዶችን ማስፋፋቱን ይቀጥላል። በዛሬው የትምህርት ቦርድ የስራ ክፍለ ጊዜ ስብሰባ ላይ የጸደይ/የስፕሪንግ የድንበር ጥናት፣ የዲስትሪክቱ አመራሮች የሱፐርኢንቴንደንቱን ምክረ ሃሳቦች ጨምሮ አዳዲስ መረጃዎችን ገምግመዋል እንዲሁም በቦርዱ አባላት እና በማህበረሰቡ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። ቦርዱ ማርች 26 በወሰን ጥናቶች ላይ የመጨረሻ እርምጃ ለመውሰድ ቀጠሮ ተይዟል፣ 2027–2028 የትምህርት አመት የሚከናወኑ ማሻሻያዎችን አጽድቋል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
የአራተኛ ሩብ ዓመት የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ቅድመ እይታ |
|
የአራተኛው ሩብ ዓመት የሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም/ሥርዓተ ትምህርት፣ ተማሪዎች እያንዳንዱን የማርክ መስጫ ወቅት የሚያጠኗቸውን ዋና ዋና ጭብጦች እና ጽሑፎችን በአንድ ገጽ አጠቃላይ እይታ የሚሰጥ ሲሆን አሁን ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
MCPS በሚቀጥለው ሳምንት ወላጆች/አሳዳጊዎች ቁሳቁሶቹን አስቀድመው እንዲያዩ የማህበረሰብ ስብሰባ ያካሂዳል። ይህ ስብሰባ ረቡዕ፣ ማርች 18 ከቀኑ 7-8:30 p.m. ሮክቪል በሚገኘው ሪቺ ፓርክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል።
አድራሻ፦ Ritchie Park Elementary School, 1514 Dunster Road in Rockville
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
አዲሱ STEM እና የስነጥበብ ትኩረት በዚህ አመት ብሔራዊ የኮሌጅ ትርኢት ላይ ያተኩራል። |
|
አመታዊው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ብሔራዊ የኮሌጅ መግቢያ ካውንስሊንግ ማህበር ብሔራዊ የኮሌጅ ትርኢት ከኤፕሪል 21-22 ቦይድስ በሚገኘው የአድቬንቲስት የጤና እንክብካቤ ፊልድሃውስ/ Adventist HealthCare Fieldhouse in Boyd ይካሄዳል። ይህ ነፃ ዝግጅት ከ 250 በላይ ኮሌጆችንና ዩኒቨርሲቲዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ ለኮሌጅ መግቢያ መረጃ ለሚፈፈልጉ ቤተሰቦችም ግብዓቶችን ይሰጣል።
በዚህ ዓመት አዲስ የሆነ፣ ትርኢት በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ፣ እንዲሁም በአፈጻጸም እና በምስል ስነጥበባት ልዩ ፕሮግራሞች ያሏቸው ኮሌጆችን እና ዩኒቨርሲቲዎችን ያቀርባል። ትርኢቱ በሁለቱም ቀናት ከጠዋቱ 9፡45 a.m. እስከ 1 p.m. የሚካሄድ ሲሆን በትምህርት ቤቶቻቸው ለሚማሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው።
አውደ ርዕዩ ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 21 ከቀኑ 6:30–8 p.m. ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ክፍት ነው። ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤት ካውንስለርዎን ወይም በት/ቤት የኮሌጅ እና የስራ ፍለጋ አማካሪዎን ያነጋግሩ። የምሽቱ ዝግጅት አውደ ጥናትን ያካትታል፡- “የኮሌጅ ማመልከቻ ሂደት፡ የጊዜ ማዕቀፍ እና ግብዓቶች” በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ።
የአድቬንቲስት የጤና እንክብካቤ ፊልድሃውስ አድራሻ የሚከተለው ነው፦ Adventist HealthCare Fieldhouse is located at 18031 Central Park Circle in Boyds.
ተጨማሪ መረጃ
|
|
|
|
|
|
Lace Up for a Cause/ለአንድ ዓላማ የጫማ ክርዎትን ይሰሩ: የበላይ ተቆጣጣሪ ሸፍል በመጪው ኤፕሪል 11 |
|
የቀን መቁጠሪያያዎት ላይ ምልክት ያድርጉ እና ስአንድ ዓላማ ስኒከር ጫማዎች ይሰሩ! የመጀመሪያው የሱፐርኢንቴንደንቱ ሸፍል ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ወደ ቦህረር ፓርክ ይመጣል።
የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለማስወገድ እንዲረዳ የMCPS የትምህርት ፋውንዴሽን የመመገቢያ ፕሮግራምን ለመደገፍ የማህበረሰብ እና የንቅናቄ ጠዋት ላይ ይቀላቀሉን። ምዝገባው ከ 30 ዶላር ጀምሮ ሲሆን የሩጫ ልብስ፣ ቲሸርት እና የዝግጅት ቀን እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ!
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
አሁን ማወቅ ያለብዎት፦ የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ |
|
3 እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እና MCPS ለመጀመር ዝግጁ የሆነ(ች) ልጅ ወላጅ ነዎት? የቅድመ—መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት 4 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች — እና አንዳንድ 3 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች - በንባብ፣ በሂሳብ እና በማህበራዊ ልማት የመጀመሪያ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ይረዷቸዋል። ብቁነት የሚወሰነው በእድሜ እና በቤተሰብ የገቢ መጠን ነው። ልጅዎ በሴፕቴምበር 1 እድሜው(ዋ) 5 ዓመት የሚሞላው/የሚሞላት ከሆነ፣ ለሙሉ ቀን ኪንደርጋርተን ይመዝገቡ። የማስመዝገቢያ ጊዜው አሁን ነው!
Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
|
|
|
|
|
|
አንድም ጨዋታ እንዳያመልጥዎት! የጸደይ/ስፕሪንግ የስፖርት ወቅት በቅርቡ ይጀመራል |
|
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጸደይ/የስፕሪንግ ስፖርት ወቅት አርብ፣ ማርች 20 ይከፈታል። ቲኬቶችንና ወቅታዊ የመግቢያ ቲኬቶችን Go Fan ላይ መግዛት ይቻላል።
|
|
|
|
|
|
የጸደይ/የስፕሪንግ ማጠቃለያ |
- *አዲስ* NAACP የወጣቶች ጉባኤ፡ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18፣ ከጠዋቱ 10 a.m. - እስከ 2 p.m. በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Richard Montgomery High School ይካሄዳል። ይህ ነፃ ዝግጅት ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ስለ አመራር ክህሎት አውደ ጥናቶችን፣ የተማሪዎች የፓናል ውይይቶችን እና ሀሳብን የማንፀባረቅ እና የማቀንቀን ዘመቻ እድሎችን ይሰጣል። ምሳ፣ ትራንስፖርት፣ እና SSL የአገልግሎት ሰዓት ይሰጣል።
- RespectFest፡ ስለ ጤናማ ግንኙነት፣ የፍቅር ጓደኝነት ጥቃትን መከላከል፣ እና ስምምነት ግንዛቤ ያግኙ። እስከ ማርች 14 ድረስ ቨርቹዋል አውደ ጥናቶች እና እሁድ፣ ማርች 15 ከቀኑ 1-4 p.m በዊተን ኮሚኒቲ ሴንተር በአካል የሚደረጉ ፌስቲቫሎች።
- የእግረኛ ደህንነት ስለመጠበቅ የኪነጥበብ ውድድር፡ ሰኞ፣ ማርች 16 ይከፈታል። ከኪንደርጋርተን እስከ 5ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የእግረኞችን ደህንነት ስለመጠበቅ የሚያሳዩ የጥበብ ስራዎችን እንዲሰሩ ይበረታታሉ። የመጨረሻው ቀን ዓርብ፣ ኤፕሪል 17 ነው።
- MoComCon፦ ከማርች 20 እስከ 21 ባለው ጊዜ ውስጥ በጀርመንታወን ቤተ መጻሕፍት እና ጀርመንታወን በሚገኘው ብላክሮክ የኪነጥበብ ማዕከል ዝግጅቶች ስለሚኖሩ ኮሚክስ እና የፈጠራ ሚዲያዎችን ያስሱ።
- "Girl Power Contest" ውድድር፡ 5 አመት እድሜ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጃገረዶች ክፍት ነው፣ ማን አነሳሳሽ እና ለውጥ ለማምጣት እንዴት እንደቻለች ይንገሩን? ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።
- የማህበራዊ ፍትህ ትርኢት፡- የወንጀል ፍትህ ማሻሻያ፣ በሴቶች መብቶች፣ በአካባቢ ፍትህ፣ እና የዘረኝነት ፍትህ ዙሪያ ከባለሙያ ተናጋሪዎች እና ድርጅቶች ጋር ይገናኙ። SSL ሰዓቶች ይሰጣሉ። ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ከጠዋቱ 10:30 a.m. እስከ ምሽቱ 1 p.m. በዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል።
- ለምርጫ ውድድር ዘመቻ ሰራተኞች ይፈለጋሉ፦ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 2026 የስቴት ፕራይመሪ ምርጫ ውድድር በምርጫ ሰራተኛነት ማገልገል ይችላሉ። ተማሪዎች ለሰሩበት ለእያንዳንዱ ሙሉ ቀን እስከ $250 ወይም እስከ 25 የSSL ሰዓታት ማግኘት ይችላሉ። አመልካቾች የአሜሪካ ዜጎች፣ የሜሪላንድ ነዋሪዎች፣ ቢያንስ 16 ዓመት የሞላቸው እና ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው። ሁለት ቋንቋ የሚናገሩ ተማሪዎች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ።
- አስተማማኝ የቪዲዮ ውድድር "Keeping It Safe Video Contest"፡ ውድድሩ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ከ 21 ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ተማሪዎች የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች እና አስከፊ ጉዳቶች 30 ሰከንድ ቪዲዮ ፈጥረው/አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።
- "Sober Vibes Essay Contest" የድርሰት ውድድር፡- እኩዮች ከፕሮም በፊት፣ በፕሮም ወቅት፣ ወይም በኋላ አልኮል እንዳይጠጡ አሳማኝ የሆነ ድርሰት በጽሑፍ አዘጋጅተው መወዳደር ይችላሉ። ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።
- የደህንነት ቀንን ለማክበር ማስታወሻ ያዙ፡- ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 11 a.m. እስከ 3 p.m. ድረስ በዚህ ነፃ ዝግጅት ላይ ስለ እግረኞች ደህንነት፣ ወደ ትምህርት ቤት የሚወስዱ ለደህንነት አስተማማኝ መንገዶች እና ስለ ቪዥን ዜሮ ፕሮግራም ግንዛቤ ያገኛሉ። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville.
|
|
|
|
|
|
ለተራዘመ የትምህርት ዓመት ብቁ ለሆኑ የልዩ ትምህርት ተማሪዎች አገልግሎት ይሰጣል። |
|
በሠመር ወራት፣የተራዘመ የትምህርት ዓመት (ESY) አገልግሎት ለማግኘት ብቁ የሆኑ የልዩ ትምህርት ተማሪዎች አገልግሎት ያገኛሉ። ESY አገልግሎቶች የመደበኛው ትምህርት ዓመት ማራዘሚያ ሲሆኑ ከፍተኛ የትምህርት መቅሰም መቀዛቀዝን ለመከላከል እና በእረፍት ጊዜ የክህሎቶችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የታለሙ ናቸው። ESY ፕሮግራም ከጁላይ 7 እስከ ኦገስት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ይካሄዳል። 6 (በቀን ስድስት የትምህርት ሰዓት)። ESY የሠመር አገልግሎቶችን ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ የሚችሉ ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች መረጃ በቀጥታ ከትምህርት ቤቶቻቸው ያገኛሉ።
|
|
|
|
|
|
ማሳሰቢያ |
|
|
|
|
|
በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ |
- የሚያውቁት ሰው አሸናፊ እንደሆን ይመልከቱ!፡የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ 11 ከፍተኛ ትጋት ያላቸው ሰራተኞቹን አክብሮት ሰጥቷቸዋል።
- ቀጣዩ መቆሚያ፣ ስቴቶች፡ አምስት MCPS ትምህርት ቤቶች ለስቴት አቀፍ MESA STEM ውድድር አልፈዋል።
- ተማሪዎች ታሪክ ይሰራሉ፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በካውንቲው የታሪክ ቀን ላይ የምርምር ውጤታቸውን ያሳያሉ።
- የአይንስታይን ዳንስ ከለብ፦ የአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዳንስ ክለብ 2026 የሪጅናል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዳንስ ፌስቲቫል ጋላ ኮንሰርቶች ላይ ሁለት ኦሪጅናል ስራዎችን እንዲያቀርብ ተመርጧል።
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|