ICYMI–በዚህ ክረምት ግንኙነትዎን ከእኛ ጋር ይቀጥሉ!MCPS - የተወደዳችሁ የማህበረሰብ አባላት፣ ለአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ተዘጋጁ!
በዚህ ቅዳሜና እሁድ በሞንትጎመሪ ካውንቲ አንዳንድ ቦታዎች ውርጭ እና ቅዝቃዜ እንደሚኖር፣ እና ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ቀድሞ የጀመረው ፖላር ቮርቴክስ በምስጋና በዓል ሰሞን 'Thanksgiving' የበለጠ ቅዝቃዜ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።
የክረምት የአየር ሁኔታ (በረዶ መጣል) የዕለት ተዕለት መርሐ ግብርዎን እንዳያስተጓጉል፣ ኦፊሴላዊ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያዎች ሳይዘገዩ እንዲደርስዎት ጥቂት ደቂቃዎችን ወስደው እነዚህን ሦስት ቅደምተከተሎች ይከውኑ።
#1 - እርስዎ የሚገኙበትን ወቅታዊ መረጃ 'ParentVUE' ላይ ይመዝግቡ
ሁለት ደቂቃ ወስደው ዋና የኢሜል አድራሻዎን እና የሞባይል ስልክ ቁጥርዎን ይስጡ፦
- ኦንላይን ወይም መተግበሪያ ላይ ParentVUE ይክፈቱ።
- 'My Account' ከፍተው ያስመዘገቡት የስልክ ቁጥርዎ እና የኢሜል አድራሻዎ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ።
- 'Alert MCPS' ጥሪዎች እንዲደርስዎት፣ የድምፅ ቅጅ ማስጠንቀቂያ መልክቶችን፣ የጽሑፍ መልዕክቶችን፣ እና ኢሜሎችን ለማግኘት የሚያስችልዎት ወቅታዊ መረጃ ሊኖርዎት ይገባል።
ParentVUE ለመጠቀም ድጋፍ ከፈለጉ፣ እባክዎ የትምህርት ቤትዎን ዋና ቢሮ ይጠይቁ።
ParentVUE Tips and Tricks for Fall 2026: English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
#2 - MCPS ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከታተሉ
MCPS የሚያስተላልፋቸውን ፈጣን እና ወቅታዊ መግለጫዎችን ለማግኘት፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከታተሉን፦
#3 - የአየር ሁኔታ መግለጫ የቀለም ኮዶችን ይመልከቱ፦
የክረምት የአየር ሁኔታ በትምህርት ቀናት ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድርበት ጊዜ፣ የአሠራር ሁኔታ ውሳኔዎች የቀለም ኮድ መግለጫ ስርዓታችንን በመጠቀም ይፋ ይደረጋሉ፦
- 🟢 አረንጓዴ ኮድ ማለት፦ መደበኛ ሥራዎች ይካሄዳሉ ማለት ነው።
- 🟡 ቢጫ ኮድ ማለት፦ ዘግይቶ ይከፈታል ማለት ነው።
- 🔵 ሠማያዊ ኮድ ማለት፦ተማሪዎች ቀደም ብሎ ይሰናበታሉ ማለት ነው።
- 🟠 ኮድ ኦሬንጅ/ብርቱካንማ ቀለም ማለት፦ ትምህርት ቤቶች ዝግ ይሆናሉ/ቢሮዎች ክፍት ናቸው።
- 🔴 ቀይ ኮድ ማለት፦ የትምህርት ስርዓቱ ተዘግቷል (ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ይሆናሉ ማለት ነው።)
- 🟣 ሐምራዊ ኮድ ማለት፦ በኦንላይን/ቨርቹዋል ትምህርት የሚሰጥበት ቀን ማለት ነው።
እያንዳንዱ የቀለም ኮድ ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት፣ ውሳኔዎች እንዴት እንደሚወሰኑ ለማወቅ፣ እና ለክረምት የአየር ሁኔታ ዝግጅት ለማድረግ እንዲረዳዎት፦ የአየር ሁኔታ መግለጫ 'Weather Onepager' እና የአሠራር ሁኔታ መግለጫ የቀለም ኮዶችን ድረ-ገጽ እንዲመለከቱ እናበረታታዎታለን።
MCPS የስራ ሁኔታ - አስቸኳይ የአየር ጠባይ ሁኔታ መመሪያ እና የቀለም ኮዶች፦ እንግሊዝኛ/English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt /አማርኛ/Amharic
በዚህ የክረምት ወቅት፣ መላው የትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰቦች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ መረጃ የሚያገኙ፣ እና እርስ በርስ እንዲገናኙ ከእኛ ጋር ስለሚተባበሩ እናመሰግናለን! |