Is this email not displaying correctly? View it in your browser

mcps logo

እዚህ ላይ ሁሉም በአንድነት

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

 

 

ዛሬ እሑድ፣ ማርች 22 ነው ። እና አሁን ባለንበት የዓለም ሁኔታ ትንሽ ከአንድ ሣምንት በላይ አሳልፈናል። ከጥቂት ስቴቶች በስተቀር ብዙዎቹ  ትምህርት ቤቶቻቸውን በሙሉ ዘግተዋል፣ በትምህርት ቤቶች፣ በማህበረሰብ እና በአጠቃላይ የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ እንደ መቅሰፍት የሆነ ለውጥ እየተለማመድን ነው።
እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ምን ሊሆን እንደሚችል ወይም እንዴት ሊሆን እንደሚችል አናውቀውም።
ይህ እንዴት እንደሚገለጥም አናውቅም።
በእርግጠኝነት የምናውቀው ግን በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ሁላችንም በአንድ ላይ ነን እና አንድ ላይ መሆናችን የተሻለ ነው።
ለእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ—ለወላጆች፣ ለቤተሰቦች እና ለሠራተኞች— ብዙዎቹ ወላጆችም ስለሆኑ እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ሣምንት ነበር።
በተለይ ለተማሪዎች ከባድ ነበር።
Steve Snyder/editor ሰው እንዲህ ሲል ገልጾታል። በትምህርት ላይ- ያተኮረ ድረገጽ፣ ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንደዚህ ይገልጻል፦
“Students are dislocated/ተማሪዎች ከቦታቸው ተፈናቅለዋል። Educators are scrambling to conceive the classroom as a virtual daily gathering. አስተማሪዎች የሚያሰላስሉት የመማሪያ ክፍልን በየቀኑ ለመሰባሰብ አይነተኛ ቦታ መሆኑን ነው። Parents have been deputized overnight as homeschoolers. ወላጆች በአንድ ጀምበር የቤት ውስጥ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ተሰይመዋል። Advocates are surveying this foreign landscape and raising urgent concerns surrounding issues of equity, inclusion, curriculum, safety, standards and … well … everything else that shapes the functioning of a school community” አቀንቃኞችም ይህንን ውጫዊ ሁኔታ በማጤን ስለ ፍትሃዊነት፣ ስለ አቃፊነት፣ ስለ ከሪኩለም፣ ስለ ደህንነት፣ ደረጃቸውን የጠበቁ አሰራሮች እና ....የትምህርት ቤትን ሥራ ሂደት የሚመለከት ሁሉንም ነገር፣  ስጋቶቻቸውን እያስተጋቡ ናቸው።
እርሱ የጻፈውን አምድ ይመልክቱ
ገና ከስቴት የተገለጸ ባይሆንም፣ ለእኛ ግልጽ እየሆነ ያለው ተማሪዎች እና ሠራተኞች ማርች 30 ወደ ትምህርት ቤት ህንፃዎች እንደማይመለሱ ነው። ቀሪው የትምህርት ዓመት ምን ሊመስል ይችላል? የሚለው እንዳለ ሆኖ፣ ይሄ ገና መልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው።
ስለዚህ፣ አሁን  ባወቅነው ነገር ላይ እናተኮር።
ተማሪዎች የተደራጀ የትምህርት ተግባር እንዲጀምሩ ለማስቻል ማርች 30፣ የመጀመሪያውን የርቀት ትምህርት ሲስተም እንጀምራለን።
ለተለያዩ አይነት በርካታ ተማሪዎች ብዙ የመማሪያ መንገዶችን-ስልቶችን የሚሰጥ ሲሆን በሠራተኞች  እና በተማሪዎች መካከል ምንም እንኳ ከተለመደው አይነት አሠራር የተለየ ቢሆንም በሰው ደረጃ ግንኙነት ለማድረግ የሚያስችል፣ የተለያዩ ስልቶችን የሚሰጥ ሲስተም ነው።
ከቅድመ ምዋእለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ 166,000 ተማሪዎቻችን ህይወት በተወሰነ ደረጃ ጤናማ ሁኔታን የሚፈጥር ሲስተም ነው።
ከአንድ ሳምንት በፊት የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ኬረን ሳልሞን-Dr. Karen Salmon በአስቸኳይ ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ለሁለት ሣምንት እንዲዘጉ ከማወጃቸው በፊት እንኳ፣ በሜሪላንድ ትልቁ የሆነው የትምህርት ሲስተም ሥራው የሚቀጥልበትን ሁኔታ የመንደፍ ሥራ ላይ ተጠምደን ነበር።
የምግብ ማከፋፈያ ሲስተሞችን ዘርግተናል፣ በመደበኛው የትምህርት ቀኖች ምግብ ከሚሰጣቸው ይበልጥ የተለያየ ምግቦችን የሚያገኙ 55,000 አብላጫ ተማሪዎች አሉን።
208 ትምህርት ቤቶችን እና 30 ሌሎች የ MCPS ጣቢያዎችን እንዲሁም ከ 1,500 በላይ አውቶቡሶችን የማጽዳት እና ከጀርም የማንፃት ግብረሃይል ተመድበው ሠርተዋል። 
ለህክምና እና የአስቸኳይ ሁኔታ ሠራተኞች የልጆች እንክብካቤ ጉዳይን በሚመለከት፣ እና  የህክምና እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እየተሰጣቸው ያለ የህክምና እርዳታ መቀጠል ስለሚቻልበት ሁኔታ ከአካባቢ እና ከስቴት የመንግስት ሃላፊዎች ጋር በቅርብ በትብብር ሠርተናል።
ከዚሁ ጋር በአንድ ጊዜ በአንድ ላይ ያከናወናቸው፣ ከጥቂት ሣምንታት በፊት በርካታ የመማሪያ መገልገያዎቻችንን እና አሴቶቻችንን ማቀናጀት ጀመርን—ብዙ ቢኖሩንም፣ በፊት ባልነበረ ሁኔታ፣  ተደራጅተው ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ በታወጀበት ቀን ሥርአት ባለው ሲስተም ለማስተማር የተሰናዱ አልነበሩም። ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ከመታዘዙ ሣምንታት አስቀድመን ሪሶርሶቻችንን ያዘጋጀን በመሆኑ ለተማሪዎቻችን የህትመት እና በአውታረ-መረብ ትምህርት እንዲሰጥ ለማድረግ ችለናል። አሁን ግልጽ እንደሆነው ለሁለት ሣምንት ከትምህርት ቤቶች ህንፃ መለየት ገና የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ያለፈውን ሣምንት ጭምር ጊዜአችንን ሲስተሙን የበለጠ ለማዳበር በማዘጋጀት እየሠራን አሳልፈናል፣ በእያንዳንዱ ቀን ሲስተሙን እየገነባን እንቀጥላለን።
የሠራተኞች ማህበራት በአጋርነት አብረውን በመሥራት ተባብረዋል።
የእኛ 24,000 ባልደረቦቻችን/ሠራተኞቻችን እንደማንኛውም ሰው ይህንን ሁኔታ እየተጋፈጡት ይገኛሉ።
አንዳንዶቹ እንክብካቤ እንዲያደርጉላቸው የሚያጣድፏቸው ልጆች እና የቤተሰብ አባላት አሏቸው።
ሌሎች ወደ ሥራ ቦታዎቻቸው ሄደው ምግብ ለማዳረስ አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር እና ሌሎች ሲስተሞችንም በተቃና ሁኔታ እንዲሠሩ በማስተካከል ያለመታከትና ያለመሰልቸት ደከመን ሳይሉ ሠርተዋል።
እያንዳንዱ እገዛ የሚያደርግ/የምታደርግ ባለሙያ-ፕሮፌሽናል፣ አስተማሪ እና አስተዳዳሪ ስለተማሪዎቹ ይጨነቃል።
ብዙዎቹ ከተማሪዎቻቸው ጋር እየተገናኙ ናቸው።
ክሪስ ሎይድ፣ የመምህራን ማህበር ፕሬዚደንት/Chris Lloyd, president of our teachers’ association፣ በዚህ ሣምንት መግቢያ ላይ ለአባሎቹ የተላከ ብልህነት የተሞላበት መልእክት እነሆ።
"ይህ ወቅት ለእኛ እና ለቤተሰቦች እንዲሁም በእኛ ጥላ ስር ለሚገኙ ለወጣት ምሁራን ሥጋት፣ ጭንቀት፣ ፍርሃት እያስከተለ መሆኑን እገነዘባለሁ። ወደዚህ ሙያ የገባንበት ምክንያት እኛ ግንኙነትን ገንቢዎች ስለሆንን ነው፣ እና እንጠነቀቃለን። ይህ ወቅት በብዙ አቅጣጫ ስብእናችን የሚፈተንበት ጊዜ ነው። ሁኔታዎች ምንም ይሁኑ ምን፣ የትምህርት አስጣጣችን በትክክል እንደሚካሄድ እምነት አለኝ፣ ነገር ግን ግንኙነታችንን በማጠንከር መምራት አለብን–ምክንያቱም የተማሪዎቻችን እና የማህበረሰባችን ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ደህንነት ለእኛ ማንነት መሠረታችን ነው።
“ ስለዚህ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎቻችንን እንዴት በተሻለ መንገድ ማስተማር እንደሚቻል እየሠራን እያለ፣ ከዚህ በፊት ስናደርግ እንደነበረው … ስለ እነርሱ እንደምናስብ እና ስለደህንነታቸው ጥንቃቄ እንደምናደርግ ልጆች እና ቤተሰቦች እንዲያውቁ ይህንን እድል መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል። ይህንን ማድረግም ስብእና ነው፣ እና በዚህ ወቅት እኛን ሙሉእ የሚያደርገንም የእኛ ስብእና ነው።"
በካውንቲያችን፣ በስቴት፣ እና በእርግጠኝነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለፈውን ሣምንት ብዙዎች የራሳቸው ስጋት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት እና የኑሮ ሁኔታ እያለ የማስተማር ፍላጎትን እንዴት ማስኬድ እንዳለባቸው እና ስለ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ደህነት አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚችሉባቸውን መንገዶች እየፈለጉ አሳልፈዋል።
ይህን ሁኔታ እንደማህበረሰብ አብረን እንደምንሻገር እና ስንተባበር የተሻልን እንደምንሆን እናውቃለን።

 

 


Community Image

 

Important Online Resources: