mcps logo

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት፦

አዲሱን ኦንላይን የትምህርት ሞዴል የመጀመሪያ ሣምንት አጠናቀናል፣ እና በእርግጥ ተማሪዎቻችንን በጠቅላላ በህንፃዎቻችን እና በመማሪያ ክፍሎቻችን ለማየት ባንችልም፣ በዚህ ሣምንት ከጓደኞቻቸው/ከእኩዮቻቸው እና ከአስተማሪዎቻቸው ጋር የመገናኘት እድል ስለነበራቸው የተወሰነ ማጽናኛ እንደሰጣቸው እናውቃለን።

በዲስትሪክታችን እየተካሄዱ ካሉት አንዳንድ አስገራሚ ሥራዎች ጥቂቶችን እንገልጽላችኋለን፦

  • በዚህ ሣምንት ከ 120,000 በላይ ተማሪዎች ተማሪዎች ከአስተማሪዎቻቸው ጋር በቀጥታ የሚተላለፍ የስብሰባ ጊዜዎችን ተሳትፈዋል
  • ከ 45,000 በላይ "Chromebooks" ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች ተከፋፍለዋል።
  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሚቀጥሉት ሣምንታት የለተማሪዎች የሚከፋፈሉ "mobile wi-fi hotspots" ለመግዛት ከ "Lockheed Martin" የ $25,000 እርዳታ አግኝቷል።
  • ከ 40 በላይ ጣቢያዎች ላይ ከ 546,000 በላይ ምግቦች ተከፋፍለዋል።
  • እስከ 12,000 ሠራተኞች በሙያ ማበልጸጊያ ኮርሶች ላይ ተሳትፈዋል

እነዚህን ተግባሮች በማከናወናችን ደስተኞች ነን፣ ነገር ግን እቅዳችንን ለመከወን እና ተማሪዎች እና ሠራተኞች ኦንላይ ትምህርት ላይ በተሠማሩበት ጊዜ ያጋጠማቸውን አስቸጋሪ ሁኔታ መፍትሔ ለመስጠት ገና የበለጠ መሠራት ያለባቸው ሥራዎች መኖራቸውን እናውቃለን። ምናልባት ያመለጠዎት ከሆነ፣ ለሁለተኛ ሣምንት ያለን ዕቅድ/our plans for week 2 እዚህ ያገኛሉ። ስለ (ኤፕሪል 6-8) ኦንላይን ትምህርት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 4 በሚቀጥለው ሣምንት ምን እንደሚጠበቅ ለመወያየት ቨርቹዋል ውይይት/virtual conversation ይካሄዳል እዚህ መመልከት ይችላሉ።
ወደ ሳምንቱ መጨረሻ ስናመራ የሚከተሉት ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎች ናቸው። ትምህርትን እና ማለማመድን እንቀትላለን እና ለተማሪዎቻችን ትርጉም ያለው የትምህርት ተሞክሮዎችን ለመፍጠር አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን። በዚህ ዓለም አቀፋዊ ቀውስ ውስጥ ስናልፍ እርስበርሳችን መደጋገፋችንን እና ማበረታታችንን መቀጠል ይኖርብናል።

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ

ስለ ማርክ አሠጣጥ

ኤፕሪል 17 ለሚጠናቀቀው ሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ ለተማሪዎች ውጤቶች ይሰጣሉ። ስለ አራተኛው የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ፣ ያሉትን አማራጮች ለመዳሰስ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከስቴት ጋር በቅርበት እየሠራ ነው። ለሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ተማሪዎች የተሰጣቸውን ሥራዎች/assignments ሲያጠናቅቁ መምህራን የተቻለውን ያክል ጥንቃቄ በማድረግ እና ሚዛናዊነት በመጠበቅ ውጤት እንደሚሰጡ ልናረጋግጥላችሁ እንፈልጋለን። የእኛ የጋር ግባችን ስለውጤት አሰጣጥ በተቻለ መጠን ማንኛውንም አይነት ስጋት ለመቀነስ ነው። ስለ አራተኛው የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ የውጤት አሰጣጥ ስለሚኖሩን እቅዶች መረጃ ከእረፍት በኋላ ለማህበረሰቡ እናሳውቃለን።

የስቴት ፈተናዎች

የ ሜሪላንድ የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) ከፌደራል መንግሥት የዚህ ዓመት ፈተና መስጠት እንዲሠረዝ ተፈቅዶለታል statewide administration of the English Language Arts (ELA) and Mathematics Maryland Comprehensive Assessment Program (MCAP) assessments for students in grades 3-8። ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የMCAP ፈተናዎች/MCAP assessments አሰጣጥን በሚመለከት MSDE አማካይነት እየታየ-እየተገመገመ ይገኛል። ዘወትር፣ በመደበኛ ሁኔታ እነዚህ ፈተናዎች በፌደራል "Every Student Succeeds Act" ደንብ ተፈላጊዎች ስለሆኑ፣ በትምህርት ዓመቱ ውስጥ ዝግጅቶች እና ፈተና መሰጠት ተግባራዊ ይሆናል። ስለ ሌሎች የስቴት ፈተናዎች በሚደርሰን ጊዜ መረጃ እንሰጣለን።

ለ 2020 ተማሪዎች መረጃ/ኢንፎርሜሽን

ሲንየሮች ከቤተሰቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር በርካታ ሁነቶችን ለማካሄድ እንደሚጠባበቁ እናውቃለን። Prom፣ yearbook signings፣ እና የመመረቂያ ፕሮግራሞችን እና ድግሶች ለሲንየሮች በጣም የሚደሰቱባቸው ሁነቶች ናቸው። ስለ ተማሪ የአገልግሎት ትምህርት/Student Service Learning (SSL) ሠዓቶች እና ሌሎች በስቴት ተፈላጊ ነገሮች በርካታ ጥያቄዎች እንደሚኖራችሁም እናውቃለን። እነዚህ ሁነቶች በተያዘላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠራት ማካሄድ ይቻል እንደሆነ ስለማናውቅ ስለ ብዙ አስፈላጊ ጥያቄዎች ገና መልስ ባይኖረንም ነገር ግን እዚህ ያለነው እናንተን ለመርዳት እና ለማገዝ መሆኑን እንድታውቁ እንፈልጋለን። ለመመረቂያ ተፈላጊ ነገሮችን በሚመለከት ስቴቱ የተቻለውን አመቺ ሁኔታ/maximum flexibility እንደሚያደግ እናምናለን እና መረጃዎች እንደደረሱን እንደምናሳውቃችሁም ቃል እንገባለን። እባክዎ የእኛን የ2020 ትምህርት ድረ-ገጽ/Class of 2020 webpage ዋና ዋና ማስታወቂያዎችን እና እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ከላይ የተገለጸውን ድረገጻችንን ዘወትር ይጎብኙ።

ለተማሪዎች እና ለወላጆች ቴክኒካዊ ድጋፍ/Technical Support Resources for Students and Parents

ተማሪዎች እና ሠራተኞች በዚህ ሣምንት ከ"Zoom meetings" ለመገናኘት አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደነበሩባቸው ተገንዝበናል። tips and best practices guide "Zoom, as well as additional troubleshooting tips" እንዴት ማገናኘት እንደምትችሉ ፍንጭ የሚሰጥ መመሪያ ልምዶችን አመቻችተናል። ስለ ኦንላይን ትምህርት ፍንጮች እና ጠቃሚ ዶኩመንቶች/"tips and resource documents for online learning" ተጨማሪ መመሪያ በ MCPS Continuity of Learning webpage ሊገኝ ይችላል።