Is this email not displaying correctly? View it in your browser  Date: December 16, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት፦

ተማሪዎች በአካል ስለሚመለሱበት እቅድ ለመነጋገር እና እርምጃ ለመውሰድ በትናንትናው ዕለት (ዲሰምበር 15) የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ተደርጓል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሥራ ባልደረቦች በዚህ ወቅት በካውንቲው ስላለው የጤና ጥበቃ ሁኔታ መረጃዎችንና፣ የወላጆችን ምርጫ/ፍላጎት የሚገልጽ የዳሰሳ ውጤት፣ እንዲሁም ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ህንጻዎች ለመመለስ ምን እንደሚጠበቅ ወቅታዊ መግለጫ ቀርቧል።


View the PowerPoint Presentation and Watch a Recording of the Meeting

በስብሰባው ወቅት ቦርዱ፦

  • የጤና ጥበቃ ሜትሪክሱ የ 14 ቀኖች አዳዲስ ህሙማን ብዛት ከ 100,000 ነዋሪዎች መካከል ከ 15 በታች አዳዲስ ህሙማን እና የምርመራ ውጤቱ ከ 5 ፐርሰንት በታች መሆኑን ለማየት ተችሏል። በጤና አጠባበቅ ሜትሪክስ ማእቀፍ መሠረት ከ 15 ኬዝ በታች ሲሆን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በጤናማ ሁኔታ በርካታ ተማሪዎችን በቡድን ማገልገል የሚያስችል መሆኑ ፀድቋል። እነዚህ ሜትሪክሶች ከስቴቱ እና ከበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) ከተደነገጉት ሜትሪክሶች ጋር የሚጣጣሙ ናቸው።

 

የቦርዱን ውሳኔ ያንብቡ

  • የተማሪዎች አነስተኛ ቡድኖች በአካል ትምህርት ለመጀመር ከ ጃኑወሪ 12 እስከ ፌብሩወሪ 1/2021 የጤና ጥበቃ ሜትሪክስ ሁኔታ እስከሚሟላ ድረስ ይዘገያል።

ውሳኔውን ያንብቡ

  • ከዚህ በታች የተገለጸውን በፈረቃ የመመለስ እቅድ አፅድቋል፦
  • የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን፣ የልዩ ትምህርት ፕሮግራሞችን ተማሪዎች እና የተለዩ የሙያ ቴክኖሎጂ ፕሮግራሞችን የመመለስ ሂደታቸውን ያፋጥናል።
  • አትሌቲክስ እና ከአካደሚክስ ባሻገር የሚካሄዱ አክቲቪቲዎች (Hyperlink) የመጀመሪያዎቹ የተማሪዎች ቡድን ለመማር በአካል ወደ ህንጻዎች በሚመለሱበት ጊዜ በአካል እንዲጀመር ይፈቀዳል።
  • በግለሰብ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተሞክሮዎች እና ድጋፎችን በቀጠሮ እንዲገኙ ያስችላል።

 

ውሳኔውን ያንብቡ

ወደፊት ምን ይጠብቀናል?
ቦርዱ በጤናማ ሁኔታ በአካል ለመማር የጤና አጠባበቅ ሜትሪክሱ መሟላት ይችል እንደሆነ ለመወሰን እንደገና በጃንዋሪ 12/2021 ይሰበሰባል። የጤና ጥበቃ ሜትሪክሱ የሚፈቅድ ከሆነ፣ የመጀመሪያዎቹ የተማሪዎች ቡድን ፌብሩወሪ 1 በአካል ወደ መማር የሚመለሱ ቢሆንም ሌሎቹ የተማሪዎች ቡድኖች በፈረቃ መመለስ የሚጀምሩበትን ቀን ገና ተለይቶ አልተወሰነም።

በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተማሪዎቻችን በአካል የመመለስ ተሞክሮ ምን ሊመስል እንደሚችል የማጠቃለያ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ጋር መስራቱን ይቀጥላል (ለምሳሌ፦ በሳምንት ውስጥ ስንት ቀን ተማሪዎች በአካል ተገኝጠው፡ለመማር እንደሚችሉ፣ የማስተማሪያ ሞዴሎች፣ ወዘተ) ጃኑወሪ 12 የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ ዝርዝሮቹን ለማህበረሰቡ እንገልጻለን።

በሁለተኛው ሴሚስተር ሁሉም ተማሪዎች በጤናማ ሁኔታ በአካል ተመልሰው ወደመማር እንዲመለሱ ለማድረግ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በቁርጠኝነት ይሠራል። በቀጣይነት ስለሚደረግልን ድጋፍ እናመሰግናለን።

 

Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ