hand sanitizer

ስለ ትምህርት ቤት ደህንነት የጋራ ጥረት/ቁርጠኝነት

ውድ ወላጆች እና አሳዳጊዎች፡-

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎቻችን እና ሠራተኞቻችን ወደ ትምህርት በአካል በሚመለሱበት ወቅት አስተማማኝ ጤናማ አካባቢ ለመስጠት ቁርጠኛ ነው። ትምህርት ቤቶች ከኮቪድ-19 ቫይረስ ስርጭት ነፃ እና ጤናማ አካባቢዎች እንዲሆኑ፣ ሁላችንም የራሳችንን ድርሻ መሥራት አለብን። በአካል ለመማር በመምረጥዎ፥ የትምህርት ቤቶችን ጤንነት-ደህንነት ለመጠበቅ ቁልፍ የሆኑ ጥንቃቄዎችን እና እርምጃዎችን ለመውሰድ ይስማማሉ ማለት ነው።

ይህ ማለት ለተማሪዎቻችን:

  • በትምህርት ቤት እና በአውቶቡሶች ውስጥ ህጉ በሚያዘው መሠረት የፊት መሸፈኛ ጭምብል በትክክል መልበስ
  • ከሌሎች ሰዎች የአካል ርቀትን መጠበቅ
  • እጅን አዘውትሮ መታጠብ እና/ወይም በሣንታይዘር ማፅዳት
  • የበሽታውን ምልክቶች በንቃት ለመለየት እንዲቻል ትምህርት ቤት በሚሰጠው የኮቪድ-19 ምርመራ መሣተፍ * (መረጃው ቶሎ ይወጣል/information coming soon)
  • በየሣምንቱ የጤንነት ማረጋገጫ ቅጽ በትክክል መሙላት
  • በየቀኑ እቤት ውስጥ የሰውነት ሙቀት መጠን መሙላት (ቴርሞሜትር/thermometer በ MCPS አማካይነት ለሁሉም ቤተሰቦች ይሰጣል.)
  • የእርስዎ ልጅ ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክቶች ከታዩበ(ባ)ት ወይም የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ከሆነ(ች) ሰው ጋር በቅርበት ተገናኝቶ(ታ) ከሆነ፥ እቤት መቆየት እና በፍጥነት ለትምህርት ቤት ማሳወቅ

MCPS በርሱ በኩል:

  • ለሁሉም ተማሪዎች እና ለሠራተኞች በሙሉ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችን መስጠትና እንዲጠቀሙ ማድረግ
  • አካላዊ ርቀትን እንዲጠብቁ ማድረግ
  • የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ሳንታይዘር አቅርቦት እና ቶሎ ቶሎ እጆቻቸውን የሚታጠቡበትን እድል መስጠት
  • የህንጻዎችን የአየር ፍሰት እና ማጣሪያዎችን ማሻሻል
  • በአካል ለመማር ለሚመለሱ ቤተሰቦች በሙሉ ቴርሞሜትሮችን/thermometers መስጠት
  • ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች በነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ መስጠት
  • ዘወትር የሚነካኩ አካባቢዎች ላይ በማተኮር ቶሎ ቶሎ ህንጻዎችን ማፅዳት/የህንጻዎችን ንፅህና መጠበቅ
  • በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የጤና ባለሙያ መመደቡን ማረጋገጥ
  • የውኃ ሲስተሞችን አሻሽሎ እንዲሠሩ ማድረግ
  • ንክኪ ሲኖር ቶሎ ክትትል የማድረግ ፕሮቶኮል መከተል

የትምህርት ቤቶቻችን ጤናማ ሁኔታ ተጠብቆ ለመማር ማስተማር ክፍት እንዲሆኑ እነዚህን ወሳኝ ትግበራዎችን እና የጤና አጠባበቅ እርምጃዎችን በመከተል ከእኛ ጋር እንዲተባበሩ እንጠይቃለን።

ወደ ትምህርት ቤቶቻችን ህንጻዎች እንኳን በደህና ተመልሳችሁ መጣችሁ ለማለት በጉጉት እንጠብቃለን።

Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools