ማርች 16 በጆርጅያ (Georgia) ስለተካሄደው ግድያ ከቦርድ ፕሬዚደንት Wolff እና ከሱፐርኢንተንደንት Smith የተሰጠ መግለጫ

የሚከተለው መግለጫ የተሰጠው ሮብ፣ ማርች 17 ነው:

በጆርጅያ (Georgia) በተፈጸመው ቅጥ ያጣ ግድያ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች እና ጓደኞች እንዲሁም ወዳጆች ልባዊ ሃዘናችንን እንገልጻለን። ሃሳባችን ከእነርሱ ጋር መሆኑንም እንገልጻለን። ምክንያቱ ምን እንደሆነ ገና ያላወቅን ቢሆንም፣ የጉዳቱ ሠለባ ከሆኑት አብዛኛዎቹ የኤዥያ ዝርያ ያላቸው ናቸው።

የምናውቀው ነገር ቢኖር በዩናይትድ ስቴትስ ስለ ኤዥያውያን ያለው የጥላቻ ወንጀል እያደገ መሄዱን ነው። ይኼ አይነት ባህርይ አስቀያሚ እና ተቀባይነት የሌለው ነው። ፍትኃዊነት እና መከባበር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፕበሊክ ስኩልስ (MCPS) ዋነኛው እሴት በመሆኑ በጠቅላላ ተማሪዎች እና ሠራተኞች እነዚህን እሴቶች መከተል እና የማህበረሰባችንን ብዝሃነት ማክበር ይጠበቅባቸዋል።

አንድም ተማሪ ማስፈራራት ወይም ጥቃት ከደረሰበት-ከደረሰባት፣ ለትምህርት ቤት ሠራተኛ እንዲናገር-እንድትናገር ወይም ስለ ደረሰበ(ባ)ት ዛቻና ማስፈራራት ቅጽ እንዲሞላ-እንድትሞላ እናሳስባለን።

ከኤዥያውያን ተማሪዎች ጋር ህብረት ስለመገንባት ጠቃሚነት እና በሠላማዊ ሁኔታ እንዴት በጋራ መሥራት እንደሚቻል ግንዛቤ ለማግኘት እያንዳንዱ ግለሰብ ይህንን "Waymaking" የተሰኘ ትምህርት ሰጪ የሆነ ውይይት እንዲመለከት እናበረታታለን።


ከዚህ በታች ይበልጥ ሪሶርሶች ይገኛሉ።



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools