classroom

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ሜይ 25 ቀን ስለተካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባና ስለ ዲስትሪክቱ የወደፊት አሠራር ማወቅ የሚያስፈልጋችሁ አምስት አስፈላጊ ነገሮችን እነሆ፦

  1. ለ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ተማሪዎችና ሠራተኞች በመደበኛነት በአካል ለመማር ማስተማር ትምህርት ቤቶች ክፍት ይሆናሉ። የትምህርት ዓመቱ በሜሪላንድ የትምህርት ዲፓርትመንት ከተደነገገው 180 የትምህርት ቀናት የተራዘመ ስለሚሆን ተማሪዎችና ሠራተኞች በሣምንት አምስት ቀን ትምህርት ቤት እንዲከታተሉ ይጠበቃል። ተማሪዎች በሣምንት አምስት ቀን ከአስተማሪዎቻቸው ትምህርት ይሰጣቸዋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ፎል ዳግም የመክፈት ዝርዝር እቅድ ለትምህርት ቦርድ እና ለ (MCPS) ማህበረሰብ ጁን 2021 ይገለጻል። ተማሪዎችና ሠራተኞች በሙሉ ፎል ላይ በአካል ለመማር ሲመጡ በደስታ ለመቀበል ዝግጁ ነን።
  2. MCPS ለቀሪው የትምህርት ዓመት ተማሪዎችና ሠራተኞች በትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ በሚሆኑበት ጊዜ ሁሉ ጭንብል እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ማለት ተማሪዎች በህንጻዎች ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ እና ለመናፈሻ እረፍት ወይም ለአካል ማጎልመሻ ትምህርት (P.E.) ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ ሁሉ ጭምብል ያደርጋሉ ማለት ሲሆን (ማስክ/ጭምብል ማስወገድ የሚቻለው ከፍተኛ ሙቀት እና ወበቅ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ነው። ይህም ከፌደራል፣ ከስቴት እና ከአካባቢው ምክረሃሳቦች ጋር የሚጣጣም ከመሆኑም በላይ ለተማሪዎች ክትባት ገና በመሰጠት ሂደት ላይ መሆኑን ያስገነዝባል።
  3. የኮቪድ-19 ክትባት በመውሰድ የትምህርት ቤቶቻችንን እና የማህበረሰባችንን ደህንነት በመጠበቅ ያግዛሉ። የኮቪድ-19 ክትባት በመውሰድ እና ልጆቻችሁን (12 ዓመትና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው) በማስከተብ እራሳችሁን እና የምትወዷቸውን ሰዎች ከወረርሽኙ ተከላከሉ። 16 ዓመትና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው የሜሪላንድ ነዋሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ለመውሰድ ከሜሪላንድ በርካታ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች በአንዱ ወይም በማናቸውም የካውንቲው የክትባት መስጫ ክሊኒክ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። MCPS በበርካታ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰጡ ክሊኒኮችን ለማሰማራት ከካውንቲው የጤናና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጋር በትብብር እየሠራ ነው። ቀጣዩ ክሊኒክ ጁን 2 በሞንቶጎመሪ ቪሌጅ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል።
  4. ለሠመር ስኩል ፕሮግራሞች ለመመዝገብ እስካሁን ጊዜ ስላለ መመዝገብ ይቻላል። ልጆችዎ በሠመር ወራት የሚደሰቱበትና የሚሠማሩበትን ፕሮግራሞች እየፈለጉ ነው? ለ MCPS የሠመር ፕሮግራሞች የምዝገባ ጊዜ ጁን 4 ስለሚዘጋ ዛሬዉኑ ማስመዝገብዎን ያረጋግጡ! በወረርሽኙ ምክንያት የባከኑ የትምህርት ጊዜያትን ለማካካስ ዲስትሪክቱ የሚያደርጋቸው ጥረቶች አካል በመሆናቸው የሠመር ፕሮግራሞች አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው የደስታ ጊዜ ለማሳለፍ እና በፕሮግራሞች ላይ ለመሳተፍ ለአንደኛና ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚቀርቡት ፕሮግራሞች በሒሳብ፣ በሊተርሲ፣ በስፔሻልስ፣ በአእምሮ ማጎልበት እና ተማሪዎችን ለሚቀጥለው የትምህርት ደረጃ በማዘጋጀት ላይ ያተኮሩ ናቸው። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለምረቃ በሚያበቃቸው የትምህርት ዘርፎች ሁሉ ክሬዲት ለማግኘት የሚያስችሉ እድሎች አሏቸው፤ ይኼውም፦ ለደጋሚ ተማሪዎችና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተማሪዎች ኦርጅናል ክሬዲቶችን፥ እንዲሁም ክሬዲት የሌላቸው አማራጮችን ጭምር በአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚሳተፉበት አማራጮች አሏቸው። እንዴት እንደሚመዘገቡ እነሆ፦
    •   በአካባቢ ትምህርት ቤቶች ለሚሰጡት በ አካል የመማር ፕሮግራሞች (non-Title I)፥ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻቸው፥ እንዲሁም በት/ቤታቸው ድረገጽ ላይ በሚገኘው "Google Form" መመዝገብ ይችላሉ። ወይም ትምህርት ቤታቸውን ማነጋገር ይኖርባቸዋል።
    • ቨርቹወል ፕሮግራሞችሴንትራል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሠመር ትምህርት/central high school summer school፥ እና "Title I programs"፥ የተማሪ ምዝገባ የሚደረገው በ ParentVUE ወይም በ ወረቀት የመመዝገቢያ ቅጽ ይኼውም በኤሌክትሮኒክስ የሚላክ ወይም በልጅዎ ት/ቤት በእጅ የሚሰጥ መሆን አለበት። እንዲሁም ቤተሰቦች በዚህ አድራሻ 850 Hungerford Dr. in Rockville፥ ከማክሰኞ ጁን 1 ጀምሮ እስከ ዓርብ ጁን 4 ከ 8:30 a.m.-–4:30 p.m. በዋናው ጽ/ቤት ማስመዝገብ ይችላሉ።
  5. የ "MCPS Virtual Academy" ማመልከቻዎች ጁን 1 ይከፈታሉ። በሣምንት አምስት ቀን በአካል መማር እንዳለ ሆኖ፥ MCPS በዚህ ፎል ቨርቹወል አካደሚ ይሰጣል። በቨርቹወል አካደሚ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች ሙሉ ጊዜ የቨርቹወል ትምህርት ፕሮግራም ይሰጣል። በፕሮግራሙ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ለመግቢያ ማመልከት ያለባቸው ሲሆን ለመሳተፍ ውሳኔ ማግኘት አለባቸው። የበለጠ መረጃ ለማህበረሰቡ በቅርቡ የሚገለጽ ከመሆኑም በላይ በቨርቹወል አካደሚ/Virtual Academy website ድረገጽ ላይ ይወጣል።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools