Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Dec. 23, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፡-

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለተማሪዎቻችን፣ ለቤተሰቦች እና ለሠራተኞቻችን የሞቀ ሰላምታ ያቀርባል።

በዚህ አስቸጋሪ ዓመት ውስጥ ማህበረሰባችን በአስገራሚ ሁኔታ ባሳየው ዘላቂ ጥንካሬ፣ መንፈሰ ጠንካራነት እና የርኅራኄ ስሜት በጣም ተገርመናል። በዚህ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እያለን የሚሰጠው የቨርቹወል ትምህርት ለሁላችንም እጅግ ፈታኝ ነው። 2021 ለሁሉም ሰው የተሻለ ዓመት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።

የመጪው ዓመት ተስፋችን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በተቻለ ፍጥነት በደህና ሁኔታ ወደ ትምህርት ቤት ህንፃዎች እንዲመለሱ ለማድረግ ነው። ወደ ቀድሞው መደበኛና ጤናማ ሁኔታ ተመልሰን በወረርሽኙ ወቅት የተሰጡትን ትምህርቶች በመውሰድ በትምህርት ሥርዓታችን ላይ አስፈላጊውን ማሻሻያ እናደርጋለን። ለማመስገን የሚገባን ብዙ ነገር አለ፤ ይበልጡን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ተማሪዎች እንዲማሩ ለመርዳት ለምታደርጉት ሁሉ ከልብ ልናመሰግናችሁ እንፈልጋለን።

መላውን የትምህርት ቦርድ በመወከል መልካም ጤንነት የተሞላበት የክረምት እረፍት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

Brenda Wolff
President, Board of Education
ብረንዳ ዎልፍ
የትምህርት ቦርድ ፕሬዚደንት

Karla Silvestre
Vice President, Board of Education
ካርላ ሲልቨስትር  
የትምህርት ቦርድ ምክትል ፕሬዚደንት