Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Nov. 11, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከጃኑወሪ 2021 ጀምሮ በአካል ለመማር የመመለስ ማዕቀፍ በጊዜያዊነት አጽድቋል የመመዘኛው አውታር ኖቨምበር 6 ለትምህርት ቦርድ የቀረበ ሲሆን በአካል በፈረቃ ለመማር ስለመመለስ የዲስትሪክቱን እቅድ ይዘረዝራል። እርስዎም ኖቨምበር 10 ውይይቱን እዚህ ሊመለከቱ ይችላሉ እንዲሁም የፓወርፖይንት ስላይዶችን እዚህ ይመለከቷል።

ምን ማወቅ እንዳለብዎት፦

 • MCPS በጥንቃቄና ጤናማ የሆነ፣ በአካል በፈረቃ ለመማር ስለ መመለስ  የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ ሜትሪክስ ዳሽቦርድ አዘጋጅቷል።

 • የጥንቃቄ ሜትሪክሱ ከተሟላ፥ ዲስትሪክቱ ከጃኑወሪ 12/2021 ጀምሮ አንዳንድ ተማሪዎች በአካል እንዲማሩ ማምጣት ይጀምራል። የመጀመሪያው የመመለስ ሁኔታ በይበልጥ የሚያተኩረው ልዩ ትምህርት በሚሰጣቸው እና ሙያዊ የቴክኖሎጂ ትምህርት (CTE) ፕሮግራሞችን በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ነው። ከተመረጡ እነዚህ ቤተሰቦች እንዲያውቁት ይደረጋል።

 • ሰፋ ያለ የተማሪዎች ቡድኖች ከፌብሩወሪ 1/2021 ጀምሮ በፈረቃ ይጀምራሉ።

 • በአካል ተመልሶ መማር ለማይፈልጉ ቤተሰቦች ቨርቹወል የመማር አማራጭ ይኖራቸዋል።

 • በሁለተኛው ሴሚስተር ልጃቸው በተለይ በ ቨርቹወል ትምህርት ላይ ብቻ እንዲቆይ-እንድትቆይ ወይም በአካል ተገኝቶ መማር እና ቨርቹወል መማርን በጣምራ ማስኬድ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች ዳሰሳው አሁን ተጀምሯል

 • በአካል የመማር ተሞክሮ የሚከተሉትን ሦስት ሞጁሎች ያካትታል፦
  • ለቨርቹወል ትምህርት የአካል ድጋፍ። ማቀናበር፥ ግንዛቤ መስጠት፥ እና ቨርቹወል የኮርስ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ረገድ ተማሪዎች ከሠራተኞች ድጋፍ ያገኛሉ።
  • ጣምራ ትምህርት። ተማሪዎች በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ በአካል እየተማሩ ከርቀት ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በጣምራ ይሳተፋሉ ።
  • ቀጥተኛ መመሪያ። ተማሪዎቹ ለአንድ የተለየ ኮርስ ምንም ዓይነት የርቀት ትምህርት አካል ሳይኖር በክፍል ውስጥ በአካል የሚሰጥ ትምህርት ያገኛሉ።

 • ወደ ሕንጻዎች ከተመለስን በኋላ የአቅም ውስንነት እና የሠራተኞች በበቂ ሁኔታ መገኘትን አስመልክቶ ለተማሪዎች እንዴት ትምህርት መስጠት እንደሚቻል የአሠራር ልዩነት ሊኖር ይችላል። ጃኑወሪ ላይ የእነርሱን ትምህርት ቤት የተለየ ሞዴል በሚመለከት ወላጆች ይበልጥ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። የዳሰሳ ግብረመልሶቹ ለእያንዳንዱ ማህበረሰብና በየደረጃው የተለየ ሞዴል ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ ይውላሉ። እንደገና፥ ሁሉም ተማሪዎች ሙሉበሙሉ ቨርቹወል ሞዴል ላይ ብቻ የመቆየት አማራጭ የሚኖራቸው ሲሆን ቨርቹወል ሞዴል የምንሰጠው ትምህርት ወደፊት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው እናውቃለን።

የወላጅ ዳሰሳውን እስከ ዲሰምበር 3 ያጠናቁ

ከዛሬ ኖቨምበር 11 ጀምሮ፥ ወላጆች ይህንን አጭር ዳሰሳ እንዲሞሉ ይጠየቃሉ ልጃቸው/ልጆቻቸው በተለይ በ ቨርቹወል ትምህርት እንዲቆይ/እንድትቆይ/እንዲቆዩ የሚፈልጉ ከሆነ ወይም የሚሳተፍ/የምትሳተፍ/የሚሳተፉ ከሆነ በአካል እና በቨርቹወል ጣምራ ትምህርት በሁለተኛ ሴሚስተር ወቅት። ሁለቱም አማራጮች ተማሪዎች አትሌቲክስ እና ከከሪኩለም ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች ላይ በአካል እንዲሳተፉ ይፈቅዳሉ። ለተማሪያቸው MCPS መጓጓዣ እንዲያቀርብ ይፈልጉም እንደሆነ ለማወቅ ወላጆችን እንጠይቃለን። ቤተሰቦች ልጃቸውን (ልጆቻቸውን) ወደ ትምህርት ቤት ህንጻ መልሰው መላክ የሚያስቸግራቸው ከሆነ ሙሉ በሙሉ በ ቨርቹወል ሞዴል ለመቆየት ምርጫ እንዳላቸው በድጋሚ ለማረጋገጥ እንፈልጋለን። አንዴ ምርጫዎን ካሳወቁ በኋላ፥ ለውጥ ሊደረግ የሚቻለው ልዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ብቻ መሆኑን እባክዎ ልብ ይበሉ። በተጨማሪ፦ በቂ ሠራተኞች እና የቦታ ማብቃቃትን ለማረጋገጥ ማናቸውንም ምርጫ ያላደረጉ ቤተሰቦች በቀጥታ ወደ ቨርቹወል ትምህርት ብቻ ይመደባሉ። ዳሰሳው ዲሰምበር 3 የሚዘጋ ሲሆን ቤተሰቦች ስለቀጣዮቹ እርምጃዎች እና ትምህርት ቤቶችን በተናጠል የሚመለከቱ መረጃዎችን ያገኛሉ።

ስለ ኮቪድ-19 የመረጃ ቋት ሠሌዳ (ዳሽቦርድ)

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በጥንቃቄ በአካል ወደትምህርት ስለመመለስ ለምናደርገው ውይይት ግንዛቤ የሚሰጥ በጉልህ የሚታይ የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ ሜትሪክስን ለማህበረሰቡ ስለ ኮቪድ-19 መግለጫ የሚሰጥ ሠሌዳ (ዳሽቦርድ) በሥራ አውሏል። በተጨማሪም ምን ያህል የ MCPS ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት እንዳደረጉ፣ በአሁኑ ጊዜ ምን ያህል ተገልለው እንደሚገኙ እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን (FAQs) መረጃ ይሰጣል።

የልዩ ትምህርት ምዘና ማዕከላት

የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ ሜትሪክሱ የሚፈቅድ ከሆነ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዲሰምበር 3 በ "Hallie Wells, Sligo and Julius West" መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (ሚድል ስኩልስ) የልዩ ትምህርት ምዘና ማዕከላት የሚከፈቱ ሲሆን ቤተሰቦች ከሰኞ እስከ ዓርብ ባሉት ቀናት በቀጠሮ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። እነዚህ የምዘና ማዕከላት ለስፔሻል ትምህርት ጀማሪዎች እና መቀጠል የሚችሉትን ብቁ መሆናቸውን ለመለየት በሚደረግ የአካል ትምህርት እና ስነልቦናዊ ምዘናዎች ላይ ቤተሰቦች በቀጥታ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣል።


ቦርዱ ኖቨምበር 17 በሚኖረው የሥራ ስብሰባ በዚህ ማእቀፍ ላይ ውይይቱን የሚቀጥል ሲሆን ዲሰምበር 3 የማጠቃለያ ውሳኔ ድምጽ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል። ቤተሰቦች ለተማሪዎቻቸው የትኛው ሞዴል የተሻለ እንደሚሆን ለመወሰን በርካታ ጥያቄዎች እንደሚኖሯቸው እንገነዘባለን። የጥያቄዎቻችሁን እና ግብረ መልሳችሁን ምላሽ ለማግኘት ኖቬምበር 12 ቨርቹወል ውይይት ላይ እንድትሳተፉ እናበረታታችኋለን። ቨርቹወል ውይይት በ 6:30 p.m. ይጀመራል እና በ MCPS ድረገጽ፣ MCPS TV (Comcast 34፣ Verizon 36 እና RCN 89) እና YouTube ላይ ይተላለፋል። በዚህ በይነመረብ ጥያቄዎችን በቅድሚያ ያቅርቡ www.mcpssubmitquestion.org ስለ ዳሰሳው ጥያቄ ያላቸው ወላጆች በ mcpsinfo@mcpsmd.net ማቅረብ ይችላሉ።

ዘወትር ለሚደረግልን ድጋፍ እናመሰግናለን።

ከሰላምታ ጋር
Montgomery County Public Schools