16 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ከጃንዋሪ 20 ጀምሮ ወደ ቨርቹወል ትምህርት ይገባሉ

January 18, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ከበርካታ ቁልፍ ሁኔታዎች ግምገማ በኋላ፣16 ትምህርት ቤቶች ለ10 የካለንደር ቀናት ወደ ቨርቹወል ትምህርት ይሸጋገራሉ። ጠቅላላ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ጤንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ፣ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ከጃንዋሪ 20 እስከ ጃንዋሪ 29 ድረስ የቨርቹወል ትምህርት ጊዜ ያካሄዳሉ። ሰኞ ጃንዋሪ 31 በአካል ወደ ት/ቤት ይመለሳሉ።

የትምህርት ቤቶቹ ዝርዝር፦

ብኤል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
(Beall Elementary School)
ብሪግስ ቼኒ መካከኛ ደረጃ ት/ቤት
(Briggs Chaney Middle School)
ብሩክሄቨን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
(Brookhaven Elementary School)
ክሎፐር ሚል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
(Clopper Mill Elementary School)
ካፒቴን ጄምስ ኢ. ደሊ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Captain James E. Daly Elementary School)
ጌትስበርግ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
(Gaithersburg Elementary School)
ግሌንአለን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
(Glenallan Elementary School)
ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
(Dr. Martin Luther King, Jr. Middle School) ሌክላንድስ ፓርክ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Lakelands Park Middle School)
ኒልስቪል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
(Neelsville Middle School)
ፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
(Paint Branch High School)
ሪካ ጆን ጊልድነር የልጆች እና የወጣቶች ሪጅናል ኢንስቲትዩት (RICA – John L. Gildner Regional Institute for Children and Adolescents)
ሳርጀንት ሽራይቨር አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Sargent Shriver Elementary School)
ትዊንብሩክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
(Twinbrook Elementary School)
ዋትኪንስ ሚል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
(Watkins Mill Elementary School)
ዊትስተን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
(Whetstone Elementary School)

በአካል የሚሰጠውን ትምህርት ለአፍታ ለማቆም ውሳኔ የሚሰጠው በርካታ ቁልፍ ነገሮችን በመመርመር/በመገምገም ሲሆን፦ እነዚህ ቁልፍ ነገሮች እያንዳንዱን ፕሮግራሞች እስከ ተግባራዊ ዝግጁነት ያሉትን ሁኔታዎች እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የሚገኝበት ልዩ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። በተናጠል የትምህርት ቤት ማህበረሰቦች የተደረገውን ለውጥ እና ለዚያ ትምህርት ቤት ውሳኔ ለማሳወቅ አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ዝርዝር የሚገልጽ ደብዳቤ ይደርሳቸዋል።

ወደዚህ ውሳኔ ለመድረስ ዋነኞቹ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦

  • የተማሪዎች ት/ቤት የመገኘት ሁኔታ (በአማካይ ሶስት ቀን ብቻ ሆኖ ሲገኝ)
  • የሰራተኞች ከሥራ የመቅረት ሁኔታ (በአማካይ ከሶስት ቀን ያልበለጠ ሲሆን)
  • በጠዋት እና ከሰአት በኋላ አገልግሎት መስጠት የማይችሉ የአውቶቡስ መስመሮች ብዛት (በአማካይ ሶስት ቀን ከሆነ)
  • በቅድሚያ ያልቀረቡ የተተኪ ጥያቄዎች ብዛት (በአማካይ የሶስት ቀን እየታየ)
  • ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ በተማሪዎች እና በሰራተኞች ላይ የተከሰቱ የ COVID-19 ሁኔታዎች
  • ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ብዙ ባለድርሻ አካላት የተሰጠ ምክረሃሳብ

ለዚህ የአሠራር ለውጥ ለመዘጋጀት መምህራን ተማሪዎችን በርቀት ትምህርት የሚያሳትፉበት አንድ ቀን የዝግጅት ጊዜ ይኖራቸዋል። ከዚያ ቀጥሎ ሙሉ በሙሉ በአስተማሪ የሚመራ የቨርቹወል ትምህርት ይሰጣል። ቤተሰቦች በቨርቹወል ትምህርት ጊዜ ስለሚጠበቁ ነገሮች መረጃ፣ መመሪያ እና ሪሶርሶችን ያገኛሉ።

Montgomery County Public Schools
የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools