ሐሙስ፣ ኤፕሪል 28 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ ኤፕሪል 28 ማወቅ ያለብዎት ስድስት ጉዳዮችን እነሆ!።
ይኼውም፦ ስለ ኮቪድ-19 መመሪያ መሻሻል፣ ከዶክተር ማክኒት ጋር ውይይት ስለሚደረግባቸው መጪዎቹ የማህበረሰብ ተሳትፎ ዝግጅቶች፣ የሠመር ፕሮግራም ምዝገባ እና ሌሎችም ናቸው።

 1. ዛሬ ማታ በቀጥታ ስርጭት! 6፡30 ፒ.ኤም. የ MCPS የአመቱ ምርጥ መምህር ማን እንደሚሆን ይመልከቱ

ይህንን የታላቅ ዝግጅት ማስታወቂያ በ MCPS ድረ-ገጽ MCPS YouTube ቻናል ወይም በኬብል MCPS-TV (Comcast 34፣ Verizon 36፣ RCN 88)መመልከት ትችላላችሁ።
በ 6፡30 p.m. ላይ በሚጀመረው ዓመታዊ የህፃናት ሻምፒዮንሺፕ መርሃ ግብር ላይ ሶስት የመጨረሻ እጩዎች እውቅና ይሰጣቸዋል።

 • ኢርማ ናጃሮ (Irma Najarro)፣ በዋሽንግተን ግሮቭ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአራተኛ ክፍል የመድብለ ቋንቋ መምህር
 • ማይክል ኤድዋርድስ (Michael Edwards)፣ በጁሊየስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የስድስተኛ ክፍል የአለም ጥናቶች እና አለምአቀፍ ሰብአዊነት መምህር
 • ጆናታን ደን (Johnathan Dunn) በሼርዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመዘምራን አሰልጣኝ/አስተማሪ ናቸው።
 1. በ MCPS ትምህርት ቤቶች ውስጥ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለግ ተግባር ከእንግዲህ አይኖርም
  በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) እናየሜሪላንድ የጤና መምሪያ በተሰጠው መመሪያ መሰረት (MDH)፣ ከአሁን በኋላ በትምህርት ቤቶች እና በልጆች እንክብካቤ ፕሮግራሞች ውስጥ የአጠቃላይ ግንኙነቶችን ንክኪ ዱካ ማፈላለግ አስፈላጊ አይሆንም።

ይህም ከሜይ 2፣ 2022 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

 • MCPS ከአሁን በኋላ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ተማሪዎች ወይም የስራ ባልደረቦች ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦችን በመለየት ወይም በግል ስለነበራቸው ንክኪ ማሳወቅ አይኖርበትም።
 • በተናጠል ለትምህርት ቤቶች በበሽታው የተያዙ ፖዚቲቭ ጉዳዮችን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ እንደአግባቡ በመማሪያ ክፍል፣ ወይም በትምህርት ቤት ደረጃ መልዕክቶች ይላካሉ።
 • ዕለታዊ ሁኔታዎችን በትምህርት ቤት የኮቪድ-19 ዳሽቦርድ ላይ ሪፖርት ማድረጉ ይቀጥላል።

በተጨማሪ እዚህ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ።

 1. ለአብዛኛዎቹ የ MCPS የሠመር ፕሮግራሞች ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።

MCPS በዚህ ሠመር ለአንደኛ ደረጃ፣ ለመካከለኛ ደረጃ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነፃ ፕሮግራሞችን ይሰጣል። አብዛኛዎቹ ፕሮግራሞች በጁላይ ውስጥ ይከናወናሉ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የክሬዲት ኮርሶች እና የተራዘመ የመማር ፕሮግራሞች (ELO) Title I አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጁን፣ ጁላይ እና ኦገስት ላይ ይከናወናሉ። አጠቃላይ በአካል መገኘት ያለባቸው ፕሮግራሞች ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ይከናወናሉ። በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች በካውንቲ እና በከተማ አስተዳደር ኤጀንሲዎች እንዲሁም በውጭ አገልግሎት ሰጪዎች የሚደገፉ ከሰዓት በኋላ የሚካሄዱ ፕሮግራሞች ይኖራሉ።እዚህ የበለጠ ይወቁ ወይም የሠመር ፕሮግራሞችን ድረገጽ ይጎብኙ።

 1. ወደ 400 የሚጠጉ ተሳታፊዎች በማህበረሰብ ተሳትፎ ዝግጅት ከዶክተር ማክኪኒት ጋር በተደረገው ውይይት ላይ ተገኝተዋል። ቀጣዩ ዝግጅት ሜይ 7 ይካሄዳል።

tableከሦስቱ ሁነቶች ውስጥ ሁለተኛው "ሁላችንም በአንድ ላይ ተማሪዎቻችንን ማስቀደም" በተሰኘ ርእስ የተካሄደ ሲሆን፡ ረቡዕ፣ ኤፕሪል 27 በዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተደረገ ሲሆን አንድ ተጨማሪ ዝግጅት ሜይ 7 ይካሄዳል። እነዚህ ውይይቶች ቤተሰቦችን፣ ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና ማህበረሰቡን በማሰባሰብ MCPS ተማሪዎቹን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማገልገል እንደሚችል ስለ ዲስትሪክቱ ጥንካሬዎች፣ ቅድሚያዎች ትኩረት የሚሹ ነገሮች እና እድሎችን በሚመለከት ለመወያየት ነው።

የመጨረሻው ዝግጅት የሚካሄደው፦

 • ቅዳሜ፣ ሜይ 7፣ 11 a.m., ጥዋት፣ በፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካፍቴሪያ ነው። አድራሻው፦ 14121 Old Columbia Pike, Burtonsville (በዚህ ዝግጅት በነጻ የሚሰጥ የኮቪድ-19 ክትባት ይኖራል።)

በቅድሚያ እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።
የተወሰነ የ MCPS አውቶቡስ መጓጓዣ ይቀርባል።

 1. ሜይ 2 እለቱን ያስታውሱ፡ ከትምህርት ቤት ውጪ ስለ ጤንነት ትኩረት የሚሰጥበት ቀን ነው

ለዲስትሪክት አቀፍ የጤና ጥበቃ የተመደበ ቀን እንደመሆኑ ተማሪዎች በአካላዊ፣ አእምሯዊ እና ስሜታዊ ደህንነት ላይ በሚያተኩሩ ከትምህርት-ቤት-ውጪ በሚደረጉት በርካታ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲሳተፉ ይበረታታሉ። እንቅስቃሴዎቹ የአካል ብቃት፣ ዮጋ፣ ዳንስ፣ ስነጥበብ እና ሙዚቃን ያካትታሉ። ቨርቹወል እና በአካል የመሳተፍ እድሎች ይኖራሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ ይህንንድረ-ገጽ ይጎብኙ።

 1. ሜይ 21 በጌትስበርግ የመፅሃፍት ፌስቲቫልን በንባብ ያክብሩ

ሜይ 21 የሚካሄደው የ 2022 የጌትስርበርግ መጽሐፍት ፌስቲቫል እየተቃረበ ነው። ይህንን ዓመታዊ የመጻሕፍት፣ የደራሲያን እና የሥነ-ጽሑፍ ልህቀትን ለማክበር በዚህ አድራሻ፦ Bohrer Park, 506 S. Frederick Avenue in Gaithersburg ከ10 a.m. እስከ 6 p.m. እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ለመሣተፍ እና የመኪና ማቆሚያ ነጻ ነው።ይህን ድረገጽ ይጎብኙ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools