ሐሙስ ሜይ 5 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ ሜይ 5 መታወቅ ያለባቸው ስድስት ጉዳዮችን እነሆ!
እነርሱም፦ የላቀ አገልግሎት ላበረከቱ መምህራኖቻችን እውቅና መስጠት፣ ስለ አዕምሮ ጤንነት መረጃ፣ ሜይ 7 ከዶክተር ማክኒት (Dr. McKnight) ጋር የሚካሄድ የማህበረሰብ ተሳትፎ፣ እና የሠመር ፕሮግራም ምዝገባን ያካትታሉ።

 1. መምህራን አድናቆት የሚሰጣቸው ሳምንት ነው።

በ MCPS ለተማሪዎቻችን አገልግሎት የሚሰጡትን በሙሉ እናከብራለን፤ ነገርግን በዚህ ሳምንት የመምህራኖቻችንን አገልግሎት በደመቀ ሁኔታ እናከብራለን። መምህራኖቻችን ተማሪዎች ለስኬት የሚያስፈልጋቸውን ክህሎቶች እና እውቀት በማዳበር ላይ ያተኩራሉ፣ አካዳሚያዊ፣ ችግር ፈቺ የፈጠራ ክህሎቶች እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ብቃታቸውን በማዳበር ላይ በማተኮር ይሠራሉ።
(ጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ማክነይት (Dr. McKnight) ለ MCPS ሰራተኞች የላኩትን መልእክት ይመልከቱ።)
የዘንድሮው የአመቱ ምርጥ መምህር የ 2022-2023 የመጨረሻ እጩዎችን እና አሸናፊውን የሼርዉድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የአመቱ ምርጥ አስተማሪ ጆናታን ደንን (Johnathan Dunn) ይህን ቪዲዮ በመመልከት መምህራኖቻችን የሚሰሩትን ታላቅ ስራ መገንዘብ ይችላሉ። (ቪዲዮውን ለማጫወት ምስሉን ጠቅ ያድርጉ ወይም ይህን አገናኝ ይጠቀሙ።)

champions

 1. በ MCPS ክብርና አድናቆት የሚሰጣቸው ጊዜ ነው።
  በምረቃ ሥነ ሥርዓት፣ ፕሮም፣ የሽግግር ስነ-ስርዓቶች እና የትምህርት አመቱን ልዩ ልዩ የመዝጊያ ዝግጅቶችን በማክበር የምናሳልፍበት ወቅት ነው። እንደዚህ በቅጽበት በሚያልፍ ጊዜ “በንቃትና በጥንቃቄ እንድንጠበቅ” እና ኮቪድ-19 እንዳይሰራጭ የምንችለውን ሁሉ ጥንቃቄ እንድናደርግ ያስፈልጋል። በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ ጭንብል መጠቀም ያስፈልጋል፣ ዝግጅቶችን ከቤት ውጭ እና ማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅ ያከናውኑ። ቫይረሱ አሁንም በማህበረሰባችን ውስጥ ስላለ የሁላችንን ጤንነት እና ደህንነት ማረጋገጥ የሁላችንም ድርሻ ነው።
 2. mental healthየአእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መርጃዎችን በኦንላይን ያግኙ
  MCPS ከ160,000 ለሚበልጡ ተማሪዎቹ እና 24,000 ሰራተኞቹ አካላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ደህንነት ቁርጠኛ ነው። በ MCPS ዋናው ደረገጽ ላይ ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች ጠቃሚ የዲስትሪክት አቀፍ መረጃ እና የማህበረሰብ ሪሶርሶችን ማግኘት ይችላሉ። በተለይ አእምሯዊ፣ ስሜታዊ እና አካላዊ ጤንነታችንን መንከባከብ በጣም አስፈላጊ ነው። ለትምህርት ቤትዎ፣ ለስራዎ፣ ለቤትዎ እና ለግል ጉዳዮችዎ ድጋፍ እንደሚያገኙ ተስፋ እናደርጋለን። በ MCPS ውስጥ የአእምሮ ጤንነትን እና ደህንነትን ስራ ለመደገፍ ስለሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች እንዲሁም ጠቃሚ የስራ መደቦችን የበለጠ ይወቁ።

  MCPS ዋናው የበይነመረብ ገጽ
  MCPS የበይነመረብ ዳሰሳ
  MCPS የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መርጃ ሪሶርሶች በየትምህርት ቤቱ
 3. tableበዚህ ቅዳሜ ሜይ 7 ከዶክተር ማክኒት (Dr. McKnight) ጋር የማህበረሰብ ተሳትፎ ሁነት ይካሄዳል
  "አሁን ሁላችንም በአንድ ላይ" የተሰኘው ተማሪዎቻችንን የማስቀደም የመጨረሻው የማህበረሰብ ተሳትፎ ዝግጅት ሜይ 7 ይካሄዳል። እነዚህ ውይይቶች ቤተሰቦችን፣ ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና ማህበረሰቡን በማሰባሰብ MCPS ተማሪዎቹን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማገልገል እንደሚችል ስለ ዲስትሪክቱ ጥንካሬዎች፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እና ያሉትን እድሎች በሚመለከት ለመወያየት ነው።

ዝርዝሩን እነሆ:

 • ቅዳሜ፣ ሜይ 7 ጠዋት 11 a.m. በፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ካፊቴሪያ፣ 14121 Old Columbia Pike፣ Burtonsville (ይህ ዝግጅት ነፃ የኮቪድ-19 ክትባቶችን እና የጤና ምርመራን ያካትታል። በራሪ ወረቀት - Flyer English / Spanish)

በቅድሚያ እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።
ከሚከተሉት ቦታዎች የአውቶቡስ መጓጓዣ ይሰጣል፡


የአውቶቡስ ቁጥር Bus#1

 የአውቶቡስ ቁጥር Bus#2

 1. ታኮማ ፓርክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Takoma Park ES) 9:45
 2. ዋይት ኦክ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (White Oak MS) 10:05
 3. ክሎቨርሊ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Cloverly ES) 10:15
 4. ፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ካፍቴሪያ (Paint Branch HS cafeteria) 11:00 am
 1. ውድሊን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Woodlin ES) 9:30
 2. አርግይለ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Argyle MS) 9:50
 3. ብሩክ ግሮቭ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Brooke Grove ES) 10:05
 4. ፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Paint Branch HS cafeteria) 11:00 am

 

 1. አብዛኛዎቹ የ MCPS የሠመር ፕሮግራሞች ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።
  MCPS በዚህ ሠመር ለአንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነፃ ፕሮግራሞችን ያቀርባል። አብዛኛዎቹ ፕሮግራሞች በጁላይ ውስጥ ይከናወናሉ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የክሬዲት ኮርሶች እና የተራዘመ የመማር ፕሮግራሞች (ELO) Title I አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጁን፣ ጁላይ እና ኦገስት ላይ ይከናወናሉ። አጠቃላይ በአካል መገኘት ያለባቸው ፕሮግራሞች ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ይከናወናሉ። በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች በካውንቲ እና በከተማ አስተዳደር ኤጀንሲዎች እንዲሁም በውጭ አገልግሎት ሰጪዎች የሚደገፉ ከሰዓት በኋላ የሚካሄዱ ፕሮግራሞች ይኖራሉ።እዚህ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ ወይም የሠመር ፕሮግራሞችን ድረገጽ ይጎብኙ።
 2. ሜይ 21 በጌትስበርግ የመፅሃፍት ፌስቲቫልን በንባብ ያክብሩ
  ሜይ 21 የሚካሄደው የ 2022 የጌትስርበርግ መጽሐፍት ፌስቲቫል እየተቃረበ ነው። ይህንን ዓመታዊ የመጻሕፍት፣ የደራሲያን እና የሥነ-ጽሑፍ ልህቀትን ለማክበር በዚህ አድራሻ፦ Bohrer Park, 506 S. Frederick Avenue in Gaithersburg ከ10 a.m. እስከ 6 p.m. እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ለመሣተፍ እና ለመኪና ማቆሚያ ነጻ ነው። ይህንን ድረገጹን ይጎብኙ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools

###Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools