ሐሙስ፣ ጁን 9 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ለሐሙስ ሰኔ 9 መታወቅ የሚገባቸው ሰባት ጉዳዮች እነሆ! ስለ ኮቪድ-19፣ ነፃ የክትባት ክሊኒኮች፣ ከትምህርት ቤት ውጪ ስለሚያሳልፉት ጊዜ የሚደረግ ጥናት፣ የፀረ-ዘረኝነት ትኩረት ቡድኖች እና ሌሎች ማሳሰቢያዎችንም ያካትታሉ።

 1. ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታዎች እየቀነሱ ናቸው
  በዚህ ሳምንት፣ የካውንቲው የጤና ጥበቃ እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) የመረጃ ሠሌዳ (ዳሽቦርድ) የኮቪድ ሁሙማን ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን ያሳያል። ይህም የሆነበት ምክንያት ጭምብል በመጠቀም፣ እጅ በመታጠብ እና በምርመራ ረገድ በተደረጉት ጥንቃቄዎች መላው ህብረተሰብ ባደረገው ጠቃሚ ጥረት ነው። የፖዚቲቭ ሁኔታ እየቀነሰ ቢሆንም፣ በ CDC እና DHHS የተላላፊ በሽታዎች መቆጣጠሪያ መሠረት አሁንም የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮቪድ ተላላፊ በሽታ መጠን በመካከለኛ ደረጃ መሆኑን ያሳያሉ። DHHS አሁንም ጭንብል እንዲለብሱ፣ የበሽታ ምልክቶች ሲታዩዎት እንዲመረመሩ፣ የእጅ ማጽጃ/እጅን መታጠብ፣ እና ሲቻል የአካል ርቀት እንዲጠብቁ ያበረታታል። የኮቪድ በሽታ ወረርሽኝ ባለበት ወቅት በክፍል ውስጥ ወይም በየክፍሉ ጭምብል/ማስክ መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዳይዛመት በምናደርገው የጋራ ትግል ታላቁን ስራችንን አብረን እንቀጥል።
 2. ልጄ ኮቪድ ከያዘው/ከያዛት ሪፖርት ማድረግ ያለብኝ የት ነው?
  የእኛን የመከላከል ጥረታችን ውጤታማ የሚሆነው በወረርሽኙ የተያዙትን መከታተል ስንችል እንደሆነ ይታወቃል። አንዳንድ ቤተሰቦች ኮቪድ ሲያዙ የት እና እንዴት ሪፖርት ማድረግ እንደሚችሉ እንደማያውቁ ገልጸዋል። በኦንላይን የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጹ አገናኝ/ሊንክ MCPS በይነመረብ መነሻ ገጽ "homepage" እና በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት በይነመረብ የመነሻ ገጽ ላይ ይገኛል።
  ኮቪድ-19 ጉግል ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ "COVID-19 Google Reporting Form"
 3. የኮቪድ-19 ክትባቶች በነጻ የሚወሰዱ ናቸው
  የ DHHS አጋሮቻችን ቅዳሜ፣ ጁን 11 በፓይንት ብራንች 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና እሁድ፣ ጁን 12 በሼዲ ግሮቭ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የክትባት መስጫ ክሊኒክ ይኖራቸዋል። ይምጡ እና ቡስተር ክትባት፣ የመጀመሪያ ክትባት ወይም ሁለተኛውን ክትባት ይውሰዱ! ክትባቶቹ በነፃ የሚሰጡ ናቸው! የኮቪድ-19 ክትባት እና ቡስተር መውሰድ በቫይረሱ እንዳይታመሙ በጣም አስተማማኝ እና የተሻለ አማራጭ ነው። እዚህ ቀጠሮ ያዙ።
 4. ትምህርት ቤት በማይኖርበት ጊዜ ለተማሪዎች መሰጠት/መዘጋጀት ስላለባቸው ዕድሎች ያለዎትን ሃሳብ ያካፍሉ።
  ተማሪዎች በትምህርት ላይ ባልሆኑ ቀናት ለተማሪዎች አስደሳች እንቅስቃሴዎች እና እድሎች እንዳሉ ያውቃሉ? MCPS ከተሳተፉት እና ተሳትፈው ከማያውቁት ምን አይነት ልምድ እንዳላቸው እና የትኞቹን እድሎችን እንደተጠቀሙ ማወቅ ይፈልጋል። ከ 4ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ተማሪዎች ያሏቸው ወላጆች እና አሳዳጊዎች የሚቀጥለውን አመት ፕሮግራም ለማሻሻል እንዲረዳ ይህን ዳሰሳ እንዲሞሉ ተጋብዘዋል። የዳሰሳ ጥናቱ እስከ ጁን 30 ድረስ ክፍት ይሆናል።

MCPS ትምህርት ቤት ባልነበረባቸው ቀናት ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ተማሪዎችን የሚያሳትፉ አማራጮችን ለመስጠት ከትምህርት ውጭ በሆኑ ጊዜያት ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ሞክሮ ነበር። እነዚህ በአካል እና/ወይም ቨርቹወል እንቅስቃሴዎች አካዴሚያዊ ክህሎቶችን፣ አካላዊ እና ስሜታዊ ደህንነትን፣ የስነ ጥበብ እና ዲጂታል የመማር ችሎታዎችን ይደግፋሉ።
ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ ስለሚኖር ፕሮግራም ይበልጥ ይወቁ

 1. በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ ከዘር እና ዘረኝነት ጋር ያለዎትን ልምድ ያካፍሉ።

እባኮትን ለወላጆች፣ ለአሳዳጊዎች እና ለተንከባካቢዎች በተዘጋጁት የትኩረት ቡድኖች ውስጥ ይሳተፉ። ይህ ድምጽዎን ለማሰማት እድል ይሰጣል! የፀረ-ዘረኝነት ስርዓት ኦዲት አካል እንደመሆኑ፥ MCPS ከተለያዩ ዘር እና ባህላዊ ዳራ የተውጣጡ ወላጆችን እና አሳዳጊዎችን ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ይፈልጋል። ይህ በዙም የሚካሄድ ስለሆነ ከ 60 እስከ 90 ደቂቃ ይወስዳል። ውይይቶቹ ሙሉ በሙሉ በምስጢር የሚጠበቁ ናቸው።

አሁንም ለሚከተሉት ክፍለ ጊዜያት ወላጆችን፣ አሳዳጊዎችን ወይም ተንከባካቢዎችን እንፈልጋለን። እባክዎን ለእርስዎ በጣም በሚስማማዎት ክፍለ ጊዜ ይመዝገቡ።ለመመዝገብ እዚህ ጠቅ ያድርጉ

ኤዥያዊ

እሮብ፣ ጁን 15 ከ 6፡00-7፡30

ጥቁር/አፍሪካን አሜሪካን

ሰኞ፣ ጁን 13 ከ 6፡00-7፡30

ላቲኖ/ሂስፓኒክ/ላቲንክስ

እሮብ፣ ጁን 15 ከ 6፡00-7፡30

መካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ

ሰኞ፣ ጁን 13 ከ 6፡00-7፡30

አሜሪካዊ የአገሬው ተወላጅ

እሮብ፣ ጁን 15 ከ 6፡00-7፡30

አምስት ዓመት ወይም ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ያሏቸው ወላጆች

ማክሰኞ፣ ጁን 14 ከ 6፡00-7፡30

ነጭ

ማክሰኞ፣ ጁን 14 ከ 6፡00-7፡30

 1. ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በጀት ጸድቋል። ይህም / ለትምህርት ማስፋፊያ እና ጠቃሚ የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት ባጀት ይኖራል
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ማክሰኞ፣ ጁን 7, 2022 ለበጀት ዓመት 2023 የ $2.92 ቢሊዮን ዶላር የስራ ማስኬጃ በጀት አጽድቋል። ይህ ማለት ከአሁኑ የ 2022 በጀት ዓመት $137.9 ሚሊዮን (5 ፐርሰንት) ጭማሪ ነው። በጀቱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቁልፍ አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ፣ ለተማሪዎች የአእምሮ ጤንነትና ደህንነት ወሳኝ ድጋፍ እንዲሰጡ እና ወረርሽኙ በሥራ ማስኬጃ ላይ ያስከተለውን ተጨማሪ ወጪዎች ይሸፍናል።

FY 2023 የስራ ማስኬጃ በጀት ውስጥ ሌሎች አስፈላጊ ቁልፍ ኢንቨስትመንቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

 1. በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የሰራተኛ ልማት የሙሉ ጊዜ መምህር
 2. በእያንዳንዱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የንባብ ባለሙያ ስፔሻሊስት የሙሉ ጊዜ መምህር
 3. ለአዳዲስ ትምህርት ቤቶች እና ለተጨማሪ የትምህርት ቦታ ድጋፍ ወሳኝ የሰው ኃይል አቅርቦት
 4. ወደ MCPS አዲስ የሚመጡ ተማሪዎችን መቀበል
 5. የህጻናት ትምህርት እድሎችን ማስፋፋት።
 6. ለሰራተኞች የሙያ ማጎልበቻ መንገዶችን ማጠናከር

ስለፀደቀው በጀት የበለጠ ያንብቡ

 1. የአእምሮ ጤንነትና ደህንነት መርጃዎች/ሪሶርሶች በ MCPS ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ
  ስለ አእምሮ ጤንነትና ደህንነት ለተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ጠቃሚ የዲስትሪክት መረጃ እና የማህበረሰብ ምንጮችን MCPS ድረገጽ መነሻ ገጽ (MCPS homepage) ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  1. MCPS ዋናው የበይነመረብ መነሻ ገጽ
  2. MCPS በትምህርት ቤቶች የሚገኙ የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መርጃ ሪሶርሶች
  3. ብሔራዊ የአእምሮ ጤና ተቋም እነዚህን ቀላል ምክሮች ይሰጣል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools

###Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools