ከሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክኒት፡ ስለ አትሌቲክስ ደህንነት እቅድ የተላለፈ መልእክት

September 28, 2022

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የማህበረሰብ አባላት 

ይህንን የምጽፈው በአትሌቲክስ ዝግጅቶቻችን ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ አካባቢ መኖሩን ለማረጋገጥ ባለፈው ሳምንት ያሳወቅናቸውን ድርጊቶች ክትትል ለማድረግ ነው። እነዚህን እርምጃዎች ስናስታውቅ፣ ትምህርት ቤቶቻችንን እና የአትሌቲክስ ፕሮግራሞቻችንን በመወከል ህብረተሰቡ ደህንነታቸው የተጠበቀ ሠላማዊ እና ምቹ እንዲሆኑ እንደሚጠብቅ በመገንዘባችን ነው።

football ባለፈው አርብ፣ በጥሩ መንፈስ የተገነቡ፣ ከፍተኛ አቅም የሚጠይቁ፣ ተማሪ-አትሌቶች በከፍተኛ ደረጃ የሚወዳደሩበት እና ተመልካቾችን የሚያስደስቱ ጨዋታዎችን አይቻለሁ። ይህ አዎንታዊ ውጤት በአጋጣሚ የተከሰተ አይደለም። ተማሪዎቻችን እኩዮቻቸው ጥሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን እና መከባበርን እንዲጠብቁ ጥሪ አድርገዋል፣ ሰራተኞች፣ ወላጆች እና በጎ ፈቃደኞች የመልካም ባህሪ ሞዴል አሳይተዋል፣ ሁሉም ሰው አስተማማኝ እና አስደሳች ተከታታይ የአትሌቲክስ ዝግጅቶች ላይ ያለምንም ስጋት ተዝናንቷል፣ እነዚህ የት/ቤቶቻችን ባህሎች አስፈላጊ አካል ናቸው።

ያንን የመሰለ ውጤት ለማግኘት ባለፈው ሳምንት ተግባራዊ ካደረግናቸው ዋና ዋና ለውጦች መካከል፡-

  • ያሉትን የጨዋታ አመራር ፕሮቶኮሎችን ማሻሻል እና ከፍ ማድረግ ተመልካቾችን በመለየት፣ ተማሪዎች እና ተመልካቾች በቆሙበት እንዲቀመጡ ማድረግ፣ ከወጡ በኋላ እንደገና ወደ ጨዋታዎች እንዳይገቡ መከልከል፣ ሜዳውን በተሻለ ሁኔታ መቆጣጠር እና ህዝቡን በተሻለ ሁኔታ ማስተናገድን ያካትታል፥
  • የአንደኛ ደረጃ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ እንዲሁም በሁለቱ ተሳታፊ ትምህርት ቤቶች ያልተመዘገቡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ በአዋቂ ሰዎች/ቻፕሮኖች እንዲጠበቁ ማድረግ፥
  • ከጨዋታው በፊት የተማሪዎችን መታወቂያ ማረጋገጥ፥
  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ደህንነት ጥበቃን ከፖሊስ እና ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር መተባበርን ጨምሮ ለእግር ኳስ ጨዋታዎች በተሻሻለ የደህንነት ጥበቃ እቅድ እንዲዘጋጁ ማድረግ፥
  • የተማሪዎች ድምጽ ተሰሚነት እንዲኖር ማድረግ፥ በዚህ ሳምንት መጨረሻ በጠዋት ማስታወቂያዎች ላይ በሚሰራጭ የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ በኩል።

footballእነዚህ ፖሊሲዎች በጣም ልንመለከታቸው የሚገቡን ተግባሮች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን እናምናለን። ተማሪዎች እና ወላጆች ትምህርት ቤታቸው በማይሳተፍባቸው ጨዋታዎች ላይ አዋቂ ሰው አብሯቸው ከሌለ መከታተል አለመቻላቸውን በተመለከተ አንዳንድ ስጋቶችን ሰምተናል። ተማሪዎች የሌሎች ትምህርት ቤቶችን ውድድር የማየት ፍላጎት ሊኖራቸው እንደሚችል ብንገነዘብም፣ በዝግጅታችን ላይ ካሉ ተማሪዎች ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖረን ፖሊሲዎቹ በሥራ ላይ መዋላቸውን ማስረዳት አስፈላጊ ነው። ለማንኛውም ክስተቶች ምላሽ ለመስጠት መልካም ግንኙነቶች በጣም አስፈላጊው መሳሪያ ናቸው። የአትሌቲክስ ደህንነት ፕላን ላይ በተገለጹት የውሳኔ መመሪያዎች መሰረት ፕሮግራማችንን እና

ክስተቶችን መከታተል እና መገምገም እንቀጥላለን። ሌሎች የአካባቢ ዲስትሪክቶች ተመሳሳይ እቅዶችን በመተግበር ላይ ሲሆኑ በእኛ በኩል ደህንነትን ለማረጋገጥ የተሻሉ ልምዶችን በማሳየት ረገድ ግንባር ቀደም ነን። 

የበለጠ መረጃ ለማግኘት፥ እባክዎ ወቅታዊ R.A.I.S.E ሪፖርት ይመልከቱ።

MCPS ወቅታዊ የአትሌቲክስ ጋዜጣ

ስለቀጣይ ድጋፍዎ እናመሰግናለን። 

ከልብ
Monifa B. McKnight 
Superintendent of Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools