ከሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክኒት የተላከ ደብዳቤ

October 21, 2022

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች፦

ይህን ደብዳቤ የጻፍኩበት ምክንያት ስለ ት/ቤቶቻችን ዲስትሪክት ደህንነት እና የደህንነት ፕሮቶኮሎች እንዲሁም ድንገተኛ ሁኔታዎችን በሚመለከት ማድረግ ስላለብን ቀጣይ ጥረት ለማሳወቅ ነው።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ርእሰ መምህራን እና ረዳት ርእሰ መምህራን በተሻሻለው የደህንነት ፕሮቶኮል ስልጠና ላይ ሲሳተፉ ቆይተዋል። በዲስትሪክቱ ውስጥ ከሚደረጉት የደህንነት ሂደቶች ጋር ማጣጣም/ማሳለጥ እንድንችል ይህ ተመሳሳይ ወቅታዊ መረጃ ለሁሉም የትምህርት ቤት ሰራተኞች ተላልፈዋል።አሠራሮቻችንን መገምገማችንን እየቀጠልን አብረን ስንሰራ፣ በድንገተኛ ሁኔታ ወቅት ምን መደረግ እንዳለበት እና መቼ እንደሚደረግ ለማወቅ ት/ቤቶች ስለማንኛውም የተሻሻሉ አሰራሮች ከቤተሰቦች ጋር ይገናኛሉ። ኖቬምበር ላይ፣ ርእሰ መምህራን ስለ ደህንነት እና የደህንነት ፕሮቶኮሎች PTAs እና ከሌሎች የማህበረሰብ ቡድኖች ጋር መረጃ ይለዋወጣሉ።

እንደ እኛ 210 ትምህርት ቤቶች፣ ከ160,00 በላይ ተማሪዎች እና ከ25,000 በላይ ሰራተኞች ባሉበት ዲስትሪክት ከባድ አደጋዎች መከሰታቸው የማይቀር ነው። እነዚህን ሁኔታዎች ስንጋፈጥ፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት የአደጋ ጊዜ አመራር እና የግንኙነት ሂደቶችን እንደሚያውቁ ማረጋገጥ አለብን።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጅ እንደመሆኔ፣ ከልጄ ትምህርት ቤት የድንገተኛ ሁኔታን ጥሪ ለቤተሰቦች የማሳወቅ፣ ጽሑፍ ወይም ኢሜይል መቀበል ምን እንደሚመስል አውቃለሁ። ሱፐርኢንተንደንት እንደመሆኔ፣ ቤተሰቦች፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች ከትምህርት ቤታቸው ከልጄ ትምህርት ቤት እንደምፈልገው አንድ አይነት ማሳወቂያ፣ ግልጽነት እና ማረጋገጫ እንዲያገኙ ለማድረግ ወስኛለሁ። መምህር በነበረኩበትም ጊዜ፣ ርእሰ መምህርት በነበርኩበትም ወቅት በዚህ ዲስትሪክት ውስጥ ይሄ እንዲደረግ እፈልግ ነበር። ድንገተኛ ሁኔታ/አደጋ ሲከሰት የማናውቀው ብዙ ነገር አለ። ነገር ግን ጭንቀትን ለመቅረፍ አንዱ መሳሪያ መረጃውን ማረጋገጥ እስከምንችል ድረስ የምናውቀውን ማካፈል ነው።

ለእነርሱ የሚጠቅመውን አሰራር እስከምንረዳ ድረስ ከትምህርት ቤት ማህበረሰቦች ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን።

በቀጣይነት ስለሚደረግልን ድጋፍ እናመሰግናለን።

ከአክብሮት ጋር

Monifa B. McKnight, Ed.D.
Superintendent of Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools