A Message from the School System Medical Officer

 

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ከጁላይ 1፣ 2023 ጀምሮ አዲሱ የሜሪላንድ ህግ እድሜያቸው 21 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ አዋቂዎች ትንሽ መጠን ያለው ካናቢስ (አደንዛዥ እፅ) ለግል መጠቀም፣ ለመዝናኛ፣ እንዲይዙ ይፈቅዳል።

ከመድሀኒት-ነጻ የስራ ቦታን በተመለከተ፤ የ1988 የፌደራል ህግ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፖሊሲ IGN ድንጋጌ መሠረት፣ አልኮል፣ ትምባሆ እና ሌሎች መድሃኒቶችን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ፣ መጠቀም፣ ይዞ መገኘት ወይም ትምባሆ፣ አልኮል ወይም ሌሎች እጾችን በትምህርት ቤት ንብረት ውስጥ ማከፋፈል የተከለከለ መሆኑ አሁንም ህጉ በሥራ ላይ ይውላል። በማንኛውም ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች፣ የሥራ ተቋራጮች፣ በጎ ፈቃደኞች ወይም የማህበረሰብ አባላት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ንብረት ውስጥ ካናቢስ/አደንዛዥ እፅ መያዝ፣ወይም ለመዝናኛ መጠቀም፣ ወይም ማሰራጨት፣አይፈቀድም/የተከለከለ ነው።

እባክዎ ያስታውሉ፥ አንድ ንጥረ ነገር ህጋዊ ስለሆነ ብቻ ጤናማ ወይም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ማለት አይደለም። አልኮሆል፣ የትምባሆ ምርቶች እና ካናቢስ/አደንዛዥ እፅ ጉዳቱን ገና በቅጡ ማገናዘብ በማይችሉበት የወጣትነት እድሜ በወጣቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ነገሮች ናቸው። ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆች/ወጣቶች በአደገኛ ሁኔታ መጠቀማቸው በሚያስከትለው ጉዳትና አደጋ ምክንያት እነዚህ ምርቶች ከ21 አመት እድሜ በታች ለሆኑ ግለሰቦች እንዳይጠቀሙ የተከለከሉ ህገወጥ ሆነው ይቆያሉ።

ለሰራተኞች፣ አልኮል እና ካናቢስ/አደንዛዥ እፅ መጠቀም የስራ አፈጻጸምን ወይም ሚዛናዊ አስተሳሰብን ሊያዛባና ሊጎዳ ይችላል፥ ስለዚህ በስራ ቀን ወይም በመደበኛ መርሐግብር ከስራ ቀን ውጭ የሚካሄዱ በትምህርት ቤት ስፖንሰር የተደረጉ እንቅስቃሴዎች እና ሁነቶች ላይ አልኮል እና ካናቢስ/አደንዛዥ እፅ መጠቀም የተከለከለ ነው። ይህ ባህሪ MCPS የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለከፍተኛ የሙያ ብቃት ማዳበር ካለው ቁርጠኝነት ጋር የማይጣጣም ከመሆኑም በላይ የሰራተኛ የስነምግባር ህግን መጣስ ነው። የፌዴራል ሕግ ከፌደራል ገንዘብ የሚቀበሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ከመድኃኒት/እፅ ነፃ እንዲሆኑ ይደነግጋል፣ እና ስለ አደንዛዥ እፅ አጠቃቀም በንግድ ተሽከርካሪ ነጂዎች ላይ የተላለፉት ተጨማሪ የፌዴራል ህጎችና መመሪያዎች በትራንስፖርት ሰራተኞቻችን ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።

MCPS ከአደንዛዥ እፅ ነጻ የሆነ የመማሪያ አካባቢን ለመጠበቅ፣ ለተማሪዎቻችን እና ለሰራተኞቻችን ደህንነት እና ስኬት ቁርጠኛ ነው።
ለትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰብ ጤና እና ደህንነት ከካውንቲ አጋሮቻችን ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን።

 

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሜሪላንድ ካናቢስ ኮሚሽን፡ ለአዋቂዎች የካናቢስ አጠቃቀምን ሕጋዊ ማድረግ
SAMHSA፡ ስለ ማሪዋና አደገኛነት ይወቁ
የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ፡ ካናቢስ ለልጆች እና ለወጣቶች ጎጂ ነው?
¿El cannabis (marihuana) es dañino para niños y adolescentes?

Dr. Patricia Kapunan
MCPS School System Medical Officer

Mr. Brian Hull
MCPS Chief of Operations



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools